የዕለቱ ዜናዎች
·
የቆንጆ
እና
የፍቱን
መጽሔት አዘጋጆች ከአገር የተሰደዱ መሆናቸውን ኢትዮ ምህዳር የተባለው ጋዜጣ ባወጣው እትሙ ገልጿል። የቆንጆ መጽሔት ማኔጅንግ
ኤዲተር አቶ ቴዎድርስ ካሳ እና የፍቱን መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ፍቃዱ በርታ በተከታታይ ከአገር የተሰዱ መሆናቸውን ጋዜጣው
ገልጾ ከአገር የተሰደዱበት ምክንያት የገቢዎችና ጉምሩክ መሥሪያ ቤት ጫናና የፍርድ ቤት ክስ መሆኑን ዘግቧል። የቆንጆና የፍትህ
መጽሄቶች ህትመታቸውን ካቆሙ ሁለት ሳምንት ያለፋቸው ሲሆን ከፍርድ ቤቱ ክስና ከጉምሩክ መስርያ ቤቱ ጫና በተጨማሪ የወያኔ
ባለስልጣኖች በተዘዋዋሪ የሚታተሙበትን ማተሚያ ቤት በማስፈራራት ከገበያ ምንጭ ሊያደርጋቸው ይሞክር እንደነበር ሁለት ግለሰቦች
የገለጹለት መሆኑን ጋዜጣው አስፍሯል። የቆንጆ መጽሄት አዘጋጅ አቶ ቴዎድርስ ካሳ ከዚህ በፊት በመጽሄቱ ምክትል አዘጋጅ በወ/ት
መልካም ሞላ ላይ የወያኔ ባለስልጣኖች ክስ በመመስረት ከአገር
እንድትወጣ ካደረጉ በኋላ ማእከላዊ ድረስ በመጥራት ወደ አገር እንድትመለስ አግባባት ብለውት እንደነበር አቶ ቴዎድሮስ ካሳ
የተናገረ መሆኑን ጋዜጣው ዘግቧል።
·
የጣሊያን
የወደብ
ጠባቂዎች
በሜዲትራኒያን
ባህር
በሊቢያ
ጠረፍ
አካባቢ
ባህሩን
ለማቋረጥ
በሞከሩ
ጀልባዎች
ላይ
ተጭነው
የነብሩ
ከ3700
በላይ
የሚሆኑ
ስደተኞች
ህይወትን
ያዳኑ
መሆናቸውን
አስታውቀዋል።
የተረፉት
በሙሉ
ወደ
ጣሊያን
ወደቦች
እንደተወሰዱና
አንዳንዶቹ
ላምፓዱሳ
ከተባለቸው
የጣሊያን
ደሴት
እንደደረሱ
ተዘግቧል።
ምቹ
የሆነው
የጸደይ
ወቅትና
በባህሩ
ላይ
የነፋስ
ሁኔታው
ጸጥ
ማለት
በፈረንጆቹ
ዓመት 2015
ብቻ
እስከ
ሁለት
መቶ
ሺ
የሚደርሱ
ስደተኞች
ባህሩን
ሊያቋርጡ
እንደሚችሉ
ተገምቷል።
በነፍስ
ማዳኑ
ተግባር
ላይ 13
የሚሆኑ
የጣሊያን
ጀልባዎች
የተሰማሩ
ሲሆን
አንድ
የፈረንሳይ
መርከብም
በአውሮፓው
የጠረፍ
ቁጥጥር
ተቋም
ስም
በቦታው
እንደነበር
ታውቋል።
ስደተኞቹ
ከየት
ከየት
አገሮች
እንደመጡ
የታወቀ
ነገር
የለም።
ሊቢያ
መንግስት
አልባ
መሆኗና
በአገርቷ
ውስጥ
ቁጥጥር በመጥፋቱ
ስደተኞችን በአንድ
ጀልባ
ለማጓጓዝ
80
ሺ
ዩሮ
ወይም 90
ሺ
ዶላር ትርፍ የሚያገኙት ህገ ወጥ ነጋዴዎች ቁጥር እየበረከተ ሊሄድ እንደሚችል ብዙዎቹ ይገምታሉ።