Finote Democracy: The Voice of Ethiopian Unity!    
Finote Democracy: Voice of Ethiopian Unity!

                


ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ በሳተላይት
የሚተላለፍ የራዲዮ ፕሮግራም
(EPRP's Satellite Radio transmissions to Ethiopia and Horn of Africa.)
 ||Home || About Us  || Contact Us  || Links  ||   ||
   
   
   
   
   
   
   

ሚያዚያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø ቦኮ ሃራምን ለመቋቋም የተቋቋመው የአምስት አገሮች የጋራ መከላከያ ኃይል አዛዥ ሚያዚያ 19 ቀን 2008  በሰጡት መግለጫ የጋራው ወታደራዊ ኃይል ውጤት ያለው ስራ እንዲሰራ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለዋል። በመጨረሻው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ረጅዎች ለጋራ ኃይሉ 250 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት መመደባቸው የተገለጸ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ገንዘቡ ለጋራው ኃይል ያልደረሰ መሆኑኑ አዛዡ ተናግረዋል፡፡ ገንዘቡ ይሰጣል ተብሎ ቃል የተገባ ከመሆኑ ባሻገር እስካሁን የጋራው ኃይል የደረሰው የተወሰኑ የመገኛኚያ መሳሪያዎችና 11 ወታደራዊ መኪናዎች ብቻ ነው ብለዋል። 8500 ወታደሮችን የያዘው የጋራ ወታደራዊ ኃይል ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሰንዝሮ ቦኮ ሃራምን አዳክሟል ቢባልም ውጤት ያለው ስራ ለመስራት እርዳታ ያስፈልገዋል ተብሏል፡፤

 

Ø ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓም. በደቡብ አፍሪካ በሚገኙት በጆሃንስበርግ፤ በኬፕ ታውንና በደርበን ከተሞች በርካታ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ፕሬዚዳንት ዙማ ከስልጣን እንዲነሱ በመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፎች አካሄደዋል። ሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንት ዙማ በሙስናና እና በዝምድና ስራ ውስጥ የተዘፈቁ በመሆናቸው አገራችውን ለመምራት ብቃት የላቸውም የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ታውቋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በአገሪቱ ምክር ቤት ውስጥ  ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ተካሄዶ የነበረውን እንቅስቃሴ በድል ያሸነፉት ፕሬዚዳንት ዙማ በደቡብ አፍሪካ ነጻ ምርጫ የተካሄደበትን 22 አመት ለማክበር በተዘጋጀ ስነስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የአገሪቱ መሪዎች የሚለወጡት በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንጅ በአቋራጭ እና በመፈንቅለ መንግስት አይደለም ብለዋል። በዴሞክራሲ ውህዳን የአብዛኛውን ሕዝብ ውሳኔ ተቀብሎ የመሄድ ግዴታ አለባቸው ብለዋል። በደቡብ አፍሪካ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱ እየታየ ያለ ክስተት ሲሆን ከተወሰኑ ወራቶች በኋላ የሚደረጉት የከተሞች አስተዳድር ምርጫዎች የሕዝቡን ስሜት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊያሳዩ ይችላሉ በማለት ታዛቢዎች አስተያየታችውን ይሰጣሉ። በሚቀጥሉት የከተሞች አስተዳደር ምርጫዎች ገዥው ፓርቲ ከተሸነፈ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በአገሪቱ ላይ ባለው የስልጣን ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ብዙዎች ይተቻሉ።

 

Ø በግብጽና በሊቢያ ወሰን ከሕገ ወጥ ስደተኞች ጋር በተደረገ ግጭት 16 የሚሆኑ ግብጻውያን ስደተኞች የተገደሉ መሆናቸውን ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ገልጿል። ግድያው የተፈጸመው ባኒ ዋሊድ በተባለችው ከተማ ውስጥ ሲሆን  ከአስተላላፊዎች ጋር በተነሳ ግጭት ስደተኞቹ የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። በሊቢያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ተልእኮ መስሪያ ቤት መሪ በሰጡት መግለጫ  12 ግብጻዉያን እና ሶስቱ ሊቢያውያን መገደላቸውን ተናግረው ድርጊቱን በጽኑ ኮንነዋል። በሊቢያ በተለያዩ ወገኖች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ከተጀመረና አለመረጋጋት ከተፈጠረ ወዲህ አገሪቱ ከልዩ ልዩ አገሮች የመጡ ስደተኞች ወደ አውሮፓ የሚሰደዱባት ማዕከል ሆና የቆየች ስትሆን የስደተኛ ማስተላለፍ ንግድም ደርቶ የሚገኝባት ቦታ ናት።  በሊቢያ በኩል ከሚተላለፉ ስደተኞች መካከል በወያኔው ዘረኛና አምባገነን ስርዓት አፈናና ብዝበዛ ተማረው አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ኢትዮጵያን የሚገኙበት መሆኑም ይታወቃል። በዚህ አጋጣሚ ባለፈው አመት አይሲስ በሚባለው የአክራሪና የአሸባሪ ቡድን አባላት ግፍ በተሞላበት መንገድ በስለት የታረዱ  ኢትዮጵያን ሰማዕታት ወገኖችን የምናስታውሰው በከፍተኛ ሀዘን ነው።  

 

 

Ø ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓም. በሱዳን ካርቱም የዩኒቨርስቲ የተማሪዎችን ሰልፍ ለመበተን ፖሊሶች በተኮሱት ጥይት አንድ ተማሪ ተመቶ የሞተ መሆኑ ተነገረ። በኦምዶርማን የሚገኘው የአህሊያ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች ቀደም ብሎ በተደረገ ሰልፍ ተይዘው በቁጥጥር ስር የነበሩት ተማራዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ ሲያካሂዱ የነበረውን ሰልፍ ለመበተን ነጭ ለባሽ ፖሊሶች በፈጠሩት ግርግር አንድ ተማሪ በጥይት ተመቶ ወዲያውኑ የሞተ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል። ረቡዕ ማታ የገዥው ፓርቲ ቃል አቀባይ ተማሪው ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውጭ በሽጉጥ ተመቶ መሞቱን አምኗል። የሟቹን ተማሪ አስከሬን በርካታ ተማሪዎች ተሸክመው ወደ መኖሪያው አካባቢ በመውሰድ እንዲቀበር ያደረጉ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ተማሪ መግደል አገርን እንደመግደል ይቆጠራል ብለዋል። የዩኒቨርስቲው አስተዳደር የተማሪውን መገደል አውግዞ ዩኒቨርስቲው ላልተወሰነ ጊዜ የዘጋ መሆኑን ገልጿል። የካርቱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየጊዜው ከጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስባችውም አገዛዙን በመቃወም ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ሲያደርጉ መቆየታቸው  ይታወቃል።

 

Ø በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት ተልእኮ መሪ በሰጡት መግለጫ የአይሲስ አሸባሪዎች በየጊዜው በአገሪቱ የነድጅ ማውጫ አካባቢዎች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። የአሸባሪዎቹ ጥቃት የነዳጅ ምርቱን የሚያስተጓግለው መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ጥቃቱም የአገሪቱን ኢኮኖሚና በነዳጅ ምርቱ ገቢ በሚተዳደሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሊቢያ ዜጎችን የኖሮ ሁኔታ ይጎዳል በማለት ኃላፊው ተናግረዋል።

Ø በተያይዘ ዜና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ከሊቢያ የአማጽያን አካባቢ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ነዳጅ ጭኖ መንቀሳቀሱ በተደረሰበት በአንድ በህንድ የተመዘገበ የጭነት መርከብ ላይ ማዕቀብ እንዲደርግ የወሰነ መሆኑ ታወቀ። ከሁለት ዓመት በፊት የጸጥታው ምክር ቤት በሊቢያ አማጽያን ቁጥጥር ስር ካሉ የነዳጅ ማምራቻ ቦታዎች ነዳጅ እንዳይጫን መከልከሉ የሚታወስ ሲሆን ይህንን  ህግ በመተላለፍ ነዳጅ ጭኖ ወደ ማልታ አቅንቷል የተባለው የጭነት መርከብ ማዕቀብ የተጣለበትና ጉዞው የቅርብ እየተደረገበት መሆኑ ተነግሯል። መርከቡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለማይታወቅ ሰው የተሸጠ ሲሆን ስሙም የተቀየረ መሆኑ ተነግሯል።

 

 

 

ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø የዓለም አቀፉ ህብረተሰብ በኢትዮጵያ ለገባው ድርቅና ረሃብ እንደ ችግሩና መጠንና ስፋት አስፈላጊውን እርዳታ ባያቀርብም ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታ መስጠቱ ይታወቃል። የወያኔ መሪዎች የእርዳታ እህሉን ከወደብ ለማንሳት እግራቸውን እየጎተቱ የራሳቸውን ማዳበሪያ እያጓጓዙ ሲሆን ወደ መሀል አገር የገባውን የእርዳታ እህልና ሸቀጣ ሸቀጥን ደግሞ በየመደብሩ በመውሰድ መቸብቸብ ጀምረዋል፡፤ በረሃብተኛ ሕዝብ ስም በተማጽኖ የመጣውን የእርዳታ እህል የወያኔ መሪዎችን ኪስ ማደለቡና የዘርና የቋንቋ ፖለቲካው ማራመጃ የፖለቲካ መሳሪያ እንደሆነ ተገልጿል፡፤

 

Ø በአሜሪካ የሚረዳው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል በሶማሊያ በየጊዜው ከአልሸባብ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑና አሜሪካንም በድሮንና በጦር አውሮፕላን በአልሸባብ መሪዎችና የጦር አበጋዞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ስትፈጽም መቆየቷ ይታወሳል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህም በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበሩ ከተሞችና የገጠር መንደሮች በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል በሚታገዙ የሶማሊያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይዘገብ እንጅ አልሸባብ ከተሞቹን እንደገና በጦርነትና ያለ ጦርነት እየወሰደ መሆኑ ከሶማሊያ የሚመጣው ዜና አስረድቷል። ከታችኛው  ሸብሌ ግዛት ከሞቃዲሾ ደቡባዊ ምዕራብ በ 110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ጃናሌ ከተማ በአልሸባብ እጅ የወደቀች ስትሆን ከተማዋን ይቆጥጠሩ የነበሩ የኡጋንዳ ወታደሮች ያለ ምንም ጥቃት ከተማዋን ለቀው መውጣታችው ታውቋል። ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጃናሌ ከተማ በርካታ የኡጋንዳ ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል።

 

Ø ተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ልኡክና የቀድሞ የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ሚስተር ቺሳኖ ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ባሰሙት ንግግር በምዕራብ ሳህራ ያለውን ችግር አስመልክቶ  ተገቢ እርምጃዎች ካልተወሰዱ  ከፍተኛ ችግር ሊከተል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። በአሁኑ ጊዜ ችግር አነስተኛ ቢመስልም ትልቁን የደን እሳት የምታቀጣጥለው ትንሽ እሳት መሆኗን በማወቅ ለችግሩ ተገቢ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል ብለዋል። ከጥቂት ወራት በፊት የተመድ ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን የምዕራብ ሳህራን ግዛት በሞሮኮ የኃይል ቁጥጥር ስር ያለ ግዛት ነው በሚል ንግግር ማድረጋችውን ተከትሎ ሞሮኮ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ ከ 20 የሚበልጡ የተመድ የሰላም አስከባሪ ሉኡካን ከምዕራብ ሳህራ ግዛት እንዲወጡ መደረጋቸው ይታወሳል። በ1983 ዓም በምዕራብ ሳህራ የተመደበው የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይል የልዑካን ቡድን የአገሪቱን የወደፊት እድል አስመልክቶ ሕዝቡ በምርጫ እንድወስን የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ለማደራጀት ኃላፊነት ቢሰጠውም  ድምጽ መስጠት የሚችለው ማነው በሚለው ላይ ልዩነት በመፈጠሩ እስካሁን ምርጫው ሳይካሄድ ቆይቷል። የሞሮኮ መንግስት ግዛቱ የሞሮኮ ነው ሲል ከ1967 ዓም. ጀምሮ የትጥቅ ትግል ሲያካሄድ የቆየው የፖሊሳሪዎ ድርጅት ደግሞ ሕዝቡ በውሳኔ ህዝብ መወሰን አለበት ሲል ቆይቷል። የአፍሪካ ህብረት የሳህራዊ አፍሪካ ሪፕብሊክ ግዛትን አባል አገር አድርጎ በመቀበሉ ሞሮኮ የአፍሪካ ህብረት እንደ ገለልተኛ አካል አታየውም። በምዕራብ ሳህራ የተመድ ተልእኮ ስለመቀጠል እና አለመቀጠሉ የጸጥታው ምክር ቤት በሚቀጥለው ሳምንት ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን የምክር ቤት አባላት የተከፋፈሉ መሆናቸው ታውቋል። ፈርንሳይ ስፔን ግብጽ እና ሴኒጋል ሞሮኮን ሲደግፉ ሌሎች ይቃወማሉ ተብሏል። የምዕራብ ሳህራ ጉዳይ ተገቢ መልስ ካላገኘ የማያባራ ጦርነት ሊከተል እንደሚችል ብዙዎች ይጠቁማሉ።

 

Ø በምዕራብ አፍሪካ በምትገኘው የኬፕ ቬርዴ ደሴት 8 ወታደሮችና ሶስት ሰላማዊ ሰዎች በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። ግድያውን የፈጸመው አንድ ከስራ ገበታው ላይ ተሰውሮ የነበረ ወታደር ነው የሚል ጥርጣሬ ያለ ሲሆን ድርጊቱን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው ግን የታወቀ ነገር የለም። ከሞቱት ሰዎች መካከል ሁለቱ የስፔን ዜግነት ያላቸው ቴክኒሺያኖች ሲሆኑ አንዱ የደሴቷ ዜግነት ያለው ነዋሪ መሆኑ ታውቋል። መንግስት በሰጠው መግለጫ ሕዝቡ እንዲረጋጋ ጥሪ ያደረገ ሲሆን አውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ በዋና ከተማዋ አንዳንድ ቦታዎች ዝግ ሆነዋል በሚል የተስፋፋው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው በማለት አስተባብሏል። የግድያው መነሻን ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን ገልጾ እስካሁን ድረስ ያሉት መረጃዎች የሚያመለክቱት ግድያው የተካሄደው በግል ችግር ምክንያት ነው ብሏል። የቀድሞ የስፔን ኮሎኒ የነበረቸውና ከሴኒጋል ወደብ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የኬፕ ቬርዴ ደሴት  ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ የሚኖርባት አገር ነች ነው።

 

Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሚስተር ማቻር እንደተጠበቀው  ሚያዚያ 18 ቀን 2008 በአገሪቱ ዋና ከተማ  የገቡ ሲሆን ለምክትል ፕሬዚዳንትነቱ ስልጣን ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ በተናገሩት ቃል በሁሉም ወገን ላይ የተፈጠረው ቁስል ባስቸኳይ እንዲድን አድርገን ሕዝባችንን ወደ አንድነት ማምጣት አለብን ብለዋል። የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ ልብ እንደሚሰሩና የእርቁ ሂደት ባስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጥሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።  ሬክ ማቻርን ለመቀበል በተደረገው የአቀባበል ስን ስርዓት ላይ የደቡብ ሱዳን ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኬር በበኩላቸው “ ወንድሜን ማቻር ስቀበል ደስታ ይሰማኛል ካሉ በኋላ የአሳቸው ወደ ጁባ መመለስ የጦርነቱን ማብቃትና የሰላሙ ሁኔታን መጀመር እንደሚያበስር ጥርጥር የለኝም”  ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን የማቻር መመለስ ለሰላሙ ጥረት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ገልጸው የአንድነቱ መንግስት ባስቸኳይ ተመስርቶ ስራ መጀመር አለበት ብለዋል። ሁኔታው በሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ባለመሆኑ የሰላሙን ጥረት ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። በየካምፑ ያሉት የሁለቱ ወገኖች ወታደሮች ከኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ ማድረግ  ቀላል ስራ አይደለም።  ለሁለቱም ወገኖች ታዛዦች ያልሆኑ የሚሊሺያ ኃይሎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አሁንም ጦርነት እያካሄዱ ነው። በአንድነት መንግስቱ ውስጥ የሚነሱ ልዩነቶችንም በተገቢው መንገድ የማስተናገድ ኃላፊነትም ይኖራል። በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች በአገሪቱ ውስጥ ውጥረቱ ከፍተኛ ውጥረት የሚታይ ሲሆን የሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ወሳኝ ይሆናሉ በማለት አስተያየታቸው የሚሰጡ ወገኖች ብዙ ናቸው።

 

 

Ø በግብጽ በሲና ባህረሰላጤ መንገድ ውስጥ በተቀበረ ፈንጅ ሶስት የፖሊስ ሰራዊት አባላት የተገደሉ መሆናቸውን የግብጽ መንግስት የዜና ወኪል ገለጸ። ረቡዕ ሚያዚያ 19 ቀን 2008 ዓም በሲና ባህረ ሰላጤ የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ ወታደራዊ መኪና የፈንጅው ጥቃት ደርሶበት የተገለበጠ ሲሆን ከሞቱት በተጨማሪ  8 ወታደሮች በጽኑ የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል።  የቆሰሉት ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ለድርጊቱ ኃላፊነትን የወሰደ አካል የለም። ላለፉት ሁለት ዓመታት በአካባቢው ጥቃት ሲፈጽም የቆየው የአይሲስ ቅርንጫፍ የሆነው ቡድን ድርጊቱን ሳይፈጽም አይቀርም ተብሎ ተጥርጥሯል።

በተያያዘ ዜና በግብጽ ዋና ከተማ በካይሮ ተገድሎ አስከሬኑ እንዳልነበር ሆኖ ተጥሎ የተገኘውን የጣሊያን ተወላጅ ጉዳይ አስመልክቶ የእንግሊዝ መንግስት ሰኞ ሚያዚያ 17 ቀን ባወጣው መግለጫ ላለፉት ሶስት ወራት የግብጽ መንግስት  ስለግለሰቡ ገዳዮች ያካሄደው ምርመራ ምንም ውጤት አለማስገኘቱ የእንግሊዝ መንግስትን ቅር ያሰኘ መሆኑን ገልጿል። መግለጫው የጣሊያን መንግስት ከግብጽ መንግስት የሚፈለገውን ትብብር አለማግኘቱ የእንግሊዝ መንግስትን ያሳዘነ መሆኑን ገልጾ ምንም እንኳ የግብጽ የጸጥታ ክፍሎች በግድያው ላይ አሉበት የሚለው ግምት የተረጋገጠ ባይሆንም ትክክለኛውን ገዳይ ለማወቅ ማናቸውም ጥረት እንዲደረግ ለዓለም አቀፍ ማህበርሰብ ጥሪ አስተላልፏል፡፤

 

 

 

ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø ጋምቤላ 18 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለው የደቡብ ሱዳን የጀዊ ስደተኞች ሰፈር የፈነዳው ግጭትና ግድያ ትላንትም ቀጥሎ እንደነበር በቦታው ያሉ ምስክሮች ገልጸዋል በቦታው የሰፈሩት ስደተኞች መቶ በመቶ የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ የሪያክ ማሻር ተከታዮችና የኑዌር ተወላጆች ሲሆኑ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሾፌር የነበረው ኢትዮጵያው ሁለት ስደተኛ ህጻናትን በመኪና ገጭቶና ገድሎ በመሰወሩ ኑዌሮቹ በሰፈሩ ያሉትን ኢትዮጵያውያን ለመግደል ተነስተው ብዙዎችን እንደገደሉ ይታወቃል ከተገደሉት ውስጥ የስደተኛው ኮሚሽን ኢትዮጵያዊ ሰራተኞችም እንዳሉበት ታውቋል። ጀዊ የአንዋኮች አካባቢ ስትሆን ወያኔ ኑዌሮችን በዚያ ያሰፈረው ለተንኮል ነው ተብሎም ተጋልጧል። ወያኔ ከግድያው በኋላ ዜጎችን ለመከላከል ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ ኢትዮጵያውያኑ ተደራጅተው የስደተኛውን ሰፈር ማጥቃታቸው ታውቋል። የሟቹ ቁጥርም ቀላል አልሆነም የተባበሩት መንግስታት የስድተኛ ኮሚሽን ሰራተኞቹን ከጀዊ አካባቢ አሽሽቷል። ግጭቱ ገና አልበረደም ሲል ዛሬም የደረስ ዜና ያረጋግጣል

 

Ø ወያኔ ለዘረፋና ለስርቆት እንዲያመቸው ከ 100 ሺ ሄክታር በላይ የጋምቤላ መሬትን ለጥጥ እርሻ በማለት ለንግድ ሸሪኮቹ በመስጠትና ለልማትም በማለት 3 ቢሊዮን ብድር በመፍቀድ የጥጥ ምርትን እናሳድጋለን በማለት ፕሮፓጋንዳውን ካሰራጨ ወዲህ የጥጥ ምርቱም ሳይኖር ልማቱም ሳይካሄድ ደን ተጨፍጭፎ ከቆየ በኋላ በብድር የተሰጠው ገንዘብ ለምን ተግባር እንደዋለ እንኳ ለማወቅ አለምቻሉ ተገልጿል። ለጥጥ ልማት በማለት መሬት ወስደው ደን መንጥረው ገንዘብ ተበድረው ጠፉ የተባሉ ሰዎችና ኢንቬስተሮች እነማን እንደሆኑ ባይገለጽም  ወያኔ ምርመራና ማጣራት ጀምሬያለሁ ብሏል። ጉዳዩን የተከታተሉ ወገኖች ግን ዘረፋውና  የተፈጥሮ ወድመቱ በወያኔ አባላትና በንግድ ሸሪኮቻቸው መፈጸሙን ይናገራሉ።

 

 

Ø በአባይ ወንዝ ግድብና አጠቃቀም ዙሪያ ወያኔና ግብጽ የገቡበትን የፖሊቲካና የዲፕሎማሲ ውዝግብ ለማብረድ በወያኔ ፓርላማ አፈጉባዔ የሚመራ አንድ የልኡካን ቡድን ግብጽንና ሱዳንን መጎብኘቱ ይታወሳል። የጉብኝቱ ዓላማ የታሰበለትን ግብ ይምታ አይምታ ባይታወቅም በወቅቱ የነበረውን የዲፕሎማሲ ውጥረት ግን ሳያለዝበው እንዳልቀረ ተገምቷል፡፤ ወያኔ ከሱዳን ጋር መልካም ወዳጀነት ፈጥሮ በድንበር አካባቢ ለም መሬቶችን አሳልፎ ከሰጠና ሱዳንም በአገሩ የሚገኙ የወያኔ ተቃዋሚዎችን እያፈነ ለወያኔ ለመስጠት ጥረት በሚያደርግበትና በሁለቱ አገሮች መካከል የድንበር ጥበቃ ውል ተፈርሞ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሱዳን ሕዝብ ዲፕሎማሲ የተባለ ቡድን የወያኔን ባለስልጣኖችን እንደሚያነጋግር ተገልጿል። ጉብኝቱ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓም የሚጀመር ሲሆን የዲፕሎማሲው ቡድን ከወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ጀምሮ ከሌሎች የወያኔ ባለስልጣኖችን ያናገጋራል ተብሏል፡፤

 

Ø መጭውን የትንሳዔ በዓል አስታኮ የወያኔ አገዛዝ ሱቆችን በማደራጀት አባ ወራዎችን በቡድን እየመደበ እንደሚያሰማራ ታውቋል። ከአስራ አምስት እስከ ሃያ የሚደርሱ አባወራዎች በአንድና በሁለት ሱቆች ሸቀጦች እንዲሸጡ በማደራጀትና በማስገደድ ነዋሪዎንና የነጋዴው ህብረተሰብን ለማጋጨት እየተሞከረ መሆኑ ተገልጿል። ሱቆቹ በዋናነት ስኳርና ዘይት የሚያቀርቡ ሲሆን ሌሎች ሸቀጦችንም ሊጨምሩ እንደሚችሉ ተነግሯል። የወያኔ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ ላንሳራፋው የኑሮ ውድነት ተጠያቂ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም የችግሩ መነሻና ምንጭ የነጋዴው ህብረተሰብ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ነጋዴዎችን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሸማቾች ማህበራትን ማቋቋሙ ይታወቃል። የፋሲካ በዓልን ተንተርሶ እንደ ቅቤ እንቁላል ዶሮ በግና በሬዎች የመሳሰሉ የምግብ አቅርቦቶች ዋጋ ጭማሪ እያሳየ መሆኑ ታውቋል።

 

Ø ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለወያኔ ማስረከብ የለመደበት የኬንያ መንግስት የታይዋን ተወላጅ ሆነው በህገወጥነት የወነጀላቸውን የታይዋን ተወላጆች አስሮ ለሀገራቸው ሳይሆን ለቻይና ማስረከቡ ተጋለጠ ቻይና ታይዋን ግዛቴ ናት ብትልም ቻይናና ታይዋን ሁለት የተለያዩ ሀገሮች ሆነው እንድሉ ይታወቃል። ወያኔ በበኩል ኬንያ እንደ የመን የሚመጡ ተቃዋሚዎችን አግታ እንድታስረክብ ዝርዝር ስሞችን ሰጧል ተብሎም መረጃ አለ

 

 

 

Ø ከጥቂት ቀናት በፊት በብሩንዲ አንድ የጄኔራል ማእርግ ያላቸው ከፍተኛ ባለስልጣን ከነባለቤታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን  ገዳዮችን አፈላልገው እንድይዙ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለወታደሮቻቸው የአንድ ሳምንት የጊዜ ገደብ ያለበት ጥብቅ መመሪያ የሰጡ መሆናቸው ታውቋል።  ፕሬዚዳንቱ ለሟቾቹ ቤተሰቦች ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን የአገሪቱ የጦር ኃይልም አንድነቱን አጠናክሮ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር እንዲያደርግ ተማጽነዋል። የፕሬዚዳንቱ ትእዛዝ በብሩንዲ እየተካሄደ ያለውን ግድያ ያፋፍማል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የብሩንዲ የእርስ በርስ ግጭት ከጀመረ ወዲህ የመንግስት ባለስልጣኖች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ሲገደሉ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎ ደግሞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ እያካሄዱ ከመሆናቸውም በላይ በርካታ ሰዎችን አስረው ሰቆቃዊ ድርጊት እየፈጸሙባቸው መሆኑ ይነገራል። 

 

Ø በሱማሊያ ከዋናዋ ከተማ ከሞጋዲሾ ሰሜን ምዕራብ 250 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከባይደዋ ከተማ አጠገብ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት እና የሱማሊያ መንግስት የጦር ካምፕ ላይ አልሸባብ ጥቃት ሰንስዝሮ ቢያንስ 20 ወታደሮችን የገደለ መሆኑ ከስፍራው የተገኘው ዜና ይገልጻል። ከተወሰነ የተኩስ ልውውጥ በኋላም የአፍሪካ ህብረት የሰላም አሰከባሪ ሃይሎች እና የሱማሊያ ወታደሮች የጦር ሰፍሩን መልሰው መቆጣጠራቸው ተነግሯል።  የአልሸባብ አጥቂዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቢገልጽም ከአልሸባብ በኩል የተሰማ ዜና የለም።

 

Ø መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ በሱማሊያ የገባውን ከፍተኛ ድርቅና ረሃብ ለመቋቋም አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ድርጅቶቹ በጋራ መግለጫቸው ላለፉት አራት አመታት በሱማሊያ ዝናም በመጥፋቱ ምክንያት ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ መሰደዱን ገልጸው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ከፍተኛ እልቂት ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል። ከስድስት ዓመት በፊት በሱማሊያ በገባው ድርቅ ምክንያት ከ250 ሺ ሰው በላይ የሞተ መሆኑን አስታውሰው ተመሳሳይ የሕዝብ እልቂት እንዳይደርስ ከፍተኛ እርዳታ መሰብሰብ አለበት ብለዋል።

 

Ø ከጥቂት ቀናት በፊት ከአንድ የቱርክ የንግድ መርከብ ላይ በባህር ላይ አፋኞች ተጠልፈው ተወስደው የነበሩ ስድስት የመርከቡ ሰራተኞች የተለቀቁ መሆናቸውን የንግድ መርከቡ ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ሚያዚያ 3 ቀን 2008 ዓም. ማንነታቸው ያለታወቀ የባህር ላይ አፋኞች መርከቧ ላይ በመውጣቱ ካፕቴኑ የሚገኝበትን ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን ማክሰኞ ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ለቀዋቸዋል ተብሏል። የተለቀቁት የመርከቧ ሰራተኞች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸው ቢነገርም ለመለቀቃቸው ካሳ መከፈሉ እና አለመከፈሉ የተገለጸ ነገር የለም። በዚህ ዓመት ብቻ በናይጄሪያ ወደብ አካባቢ ከ32 በላይ የመርከብ ጠለፋዎች የተካሄዱ መሆናቸው ከተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አካባቢ የተገኙ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

 

Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሪክ ማቻር ለአንድ ሳምንት ያህል ጉዟቸው ካዘገዩ በኋላ በዛሬው ቀን ጁባ ገብተዋል። የአማጽያኑ ድርጅት ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ሚስተር ማቻር ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን  ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ጁባ የሚገቡ መሆናቸውን ገልጾ የነበረ ሲሆን  በታቀደው መሰረት ለምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦታ ለመያዝ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ተብሏል። ሚስተር ማቻር ጁባ ይገባሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረው ሚያዚያ 10 ቀን የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ በታቀዱት ቀናት ወደ ጃባ ባለመለሳቸው  በዓለም አቅፉ ህብረተሰብ በሌሎች ላይ ከፍተኛ  ስጋት ፈጥሮ እንድነበር አይዘነጋም።

 

 

 

 

ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø የእንግሊዙ ዕለታዊ ጋዘጣ ዘ ቴሌግራፍ የእርዳታ ድርቶችንና በመስክ ላይ ያሉ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ያለው ድርቅና ረሃብ ከ18 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን እያጠቃ መሆኑን ግልጽ አድርጓል። እስከ አሁን ድረስ በወያኔና በዕርዳታ ድርጅቶች በኩል የረሃብና የድርቁ ተረጅ ወገኖች ቁጥር እስከ 12 ሚሊዮን ይገመት እንደነበር ይታወቃል። በአዲሱ አሀዝ መሠረት ከኢትዮጵያ ሕዝብ 20 ከመቶ የሚሆነው በአሁኑ ጊዜ የእርዳታ ፈላጊ አድርጎታል። የወያኔ ባለስልጣኖች የተረጅውን ሕዝብ ቁጥር መጨመር ደፍረው ባያናግሩትም የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ  ለረሃብና ለድርቁ የሚሰጠው ዕርዳታ ከተረጅው ቁጥር ጋር አይመጣጠንም በማለት አድበስብሰው ለማለፍ ሙከራ እያደረጉ መሆኑ እየተነገረ ነው።

Ø በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች በመቶ የሚቆጠሩ ገድለው በመቶ  በሚቆጠሩ ህጻናት አፍነው ከወሰዱና በሺ የሚቆጠሩ ከብቶችን ከነዱ ወዲህ በጋምቤላ ያለው ዘግናኝ እልቂት የዓለም ሕዝብ ዓይንና ጆሮ እየሳበ ነው።  በጃዊ ስደተኛ ጣቢያ አቅራቢያ አንድ ኢትዮጵያዊ አሽከርካሪ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ላይ የመኪና አደጋ በማድረሰ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል በሚል ምክንያት በካምፕ ውስጥ የነበሩት  ስደተኛች አብዛኞቹ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን  በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው የሚታወስ ሲሆን ድርጊቱን ለመቃወም አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ የወያኔ ፖሊሶችና ወታደሮች  በወሰዱት እርምጃ ግድያና የመቁሰል አደጋ ማድረሳችው ታውቋል። ለተቃውሞ ከወጡት መካከል 5 መገደላቸውና ከ 15 በላይ መቁሰላቸው ተገልጿል። በጋምቤላ ውጥረቱ እየከረረ ሲሆን ቁጣውም እየባሰ መምጣቱ ይነገራል ወያኔ በስደተኞቹ ስም የሚሰጠው ገንዘብ እንዳይጓደልበት ጥቃቱን ችላ ከማለቱም በላይ እያባባሰው ይገኛል።

Ø በግብጽ በተለያዩ ቡድኖች የተድራጀና የተቀናጀ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ስልፍ መታቀዱን ተከትሎ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ሲሲ ሰልፉን ለማስቆም በቴሌቪዥን ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።  የግብጽ ሕዝብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ መዳከምና እንዲሁም የጸጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ በሚወስዱት አፈና ምክንያት መማረሩን በመግለጸ ተቃውሞ እያሰማ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት በግብጽ ቁጥጥር ስር ያሉ ደሴቶችን የሲሲ መንግስት ለሳኡዲ አረቢያ መስጠቱ ደግሞ ምሬቱ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጎታል። የተለያዩ ቡድኖች የተቃውሞ ስልፍ ለማድረግ መወጣናቸው በመታወቁና ሰልፉም ሊያስከትለው የሚችለው ከፍተኛ ችግር ስጋት ስለፈጠረ ፕሬዚዳንት ሲሲ በይፋ ማስጠንቀቁያ መስጠት ተገደዋል። በንግግራቸው ላይ “የግብጽን መጥፋት የሚፈልጉ ኃይሎች እንደገና ጸጥታዋን ለማድፍረስ እየተዘጋጁ ነው ካሉ በኋላ የኛ ተግባር የህዝቡን ደህንነትና ጸጥታ መጠበቅ ስለሆነ አስፈላጊውን ርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል። የጸጥታ ኃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የተሰማሩ ሲሆን ሰላማዊ ስልፎችን ያደራጃሉ፤ ግለሰቦችን ይቀሰቅሳሉ ብለው የሚገምቷቸውን ግልሰሰቦችን ጋዜጠኞችንና የህግ ባለሙያዎችን ከየቤታቸው በመልቀም ያሰሯቸው መሆኑ ታውቋል።  በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሲሲ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከ 1000 ሰዎች በላይ የተገደሉ ሲሆን ወደ 40 ሺ የሚገመቱ ሰዎች መታሰራቸውም ይነገራል።

 

Ø በብሩንዲ የተናጠል ግድያው እየቀጠለ መሆኑ ተገለጸ። ሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ..ም የብሩንዲ ምክትል ፕሬዚዳንት የጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄኔራል ካሩዛ እና ባለቤታቸው በመኪና ልጃቸውን ትምህርት ቤት ካደረሱ በኋላ ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ተነግሯል። ለድርጊቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም። ባለፈው ነሐሴ ወር የፕሬዚዳንቱ የግል የጸጥታ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች መገደላቸው አይዘነጋም። እሁድ ሚያዚያ 15 ቀንም የብሩንዲ የሰብአዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከቤተክርስቲያን ሲወጡ ቦምብ ተወርውሮባቸው ሳይጎዱ በህይወት ሊያመልጡ ችለዋል።  በብሩዲ በተለይ በከፍተኛ ባለስልጣኖችና የጦር መኮንኖች ላይ የሚካሄደው የተናጠል ግድያ የብሩንዲን ፕሬዚዳንት አስተዳደር እያናጋው ነው ተብሏል። የብሩንዲ የውስጥ ችግር ከጀመረ ጀምሮ ከ400 በላይ የሆኑ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል።

በተያያዘ ዜና ሄግ የሚገኘው የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በብሩንዲ እየተካሄዱ ባሉ ወንጀሎች ላይ ክስ ለመስረት አቃቤ ህጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናትና ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል።  የመጀመሪያ ደረጃው ጥናት እንደተጠናቀቀ ሙሉ የሆነው የምርመራና ማስረጃ የማሰባብ ስራ የሚጀመር መሆኑና  ጥፋተኛ ናቸው ተብለው የሚከሰሱ ሰዎችም ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተነግሯል።

 

Ø በዳርፉር ለሶስት ተከታታይ ቀኖች በተካሄደ የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ አብዛኛው ሕዝብ ዳርፉር  በአምስት ክልሎች መከፋፈሏን መደገፉን የሱዳን መንግስት ገልጿል። በመንግስቱ መግለጫ መሰረት በተካሄደው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገበው መካከል በምርጫው የተሳተፈው 97 በመቶ የሚሆነው እንደሆነ ሲነገር ድምጽ ከሰጠው መካከል ደግሞ 98 በመቶ የሚሆነው መራጭ ዳርፉር ለአምስት ክልሎች መከፋፈሏን መርጧል ተብሏል። በርክታ ተፈናቃዮች ድምጽ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታና  ኃይልና ማስፈራሪያ በሰፈነበት ሁኔታ የሚካሄድ የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ እውነተኛ የሕዝብ ፍላጎት አያንጸባርቅም በማለት አማጽያኑ ኃይሎች ምርጫው እንዳይካሄድ አድማ ያደረጉ ሲሆን የምዕራብ አገሮችም የጸጥታው ሁኔታ ለነጻና ርቱዓዊ ምርጫ ምቹ ባለመሆኑ ምርጫው መካሄድ የለበትም ማለታቸው ይታወሳል። የሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ምርጫው የአረብ አገሮችና ሌሎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ባሉበት የተካሄደ በመሆኑ የሕዝቡን እውነተኛ ስሜትና ፍላጎት ያንጸባርቃል እያሉ ናቸው።

 

 

 

ሚያዚያ 15 ቀን 2008 ዓ.ም

Ø በጋምቤላ ንጹሃን ዜጎች ድንበር ተሻግረው በመጡ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች እልቂት ከተፈጸመባቸው አንድ ሳምንት ባስቆጠረበትና በታጣቂዎቹ ታግተው የተወሰዱ ህጻናት ጉዳይ አሁንም ምንም ምላሽ ባላገኘበትና እንዲሁም ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ድርጊቱን አውግዞ ህጻናቱ አለምንም ቅደመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረበ ባለበት ሰዓት ደቡብ ሱዳናውያን አሁንም 14 ኢትዮጵያውያንን መግደላቸው ታውቋል። ግድያው የተፈጸመው ከጋምቤላ ከተማ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ጃዊ የስደተኞች ካምፕ አቅራቢያ መሆኑ የተነገረ ሲሆን መንስኤው አንድ ኢትዮጵያዊ ሹፌር በአንድ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ላይ የመኪና አደጋ በማድረሱ ነው ተብሏል። በአራቢያው የነበሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ለአደጋው ምላሽ በአቅራቢያው የነበሩ 14 ኢትዮጵያውያንን በጭካኔ ገድለዋል። በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚገኙት ደቡብ ሱዳናውያን ግድያውን የፈጸሙት በገጀራ በድንጋይ በቢላዋ መሆኑ ሲታወቅ አንድም የወያኔ ፖሊስ ሆነ ወታደራዊ ኃይል ወደ አካባቢው አለመላኩ ብዙዎችን አስገርሟል።

Ø ከአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በተገኘው መረጃ በመንግስት ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ሲያገለግሉ የነብሩ 1500 የአዲስ አበባ መምህራን የስራ መልቀቂያ አስገብተው 700 ያህሉ መሰናበታቸው ተገልጿል። መምህራኑ በሚደርስባቸው የፖሊቲካ ጫና የደሞዝ ማነስና ዓይን ያወጣ የዘር መድልዎ የተነሳ በመማር ማስተማሩ ሂደት መቀጥል ባለመቻላቸው ሥራውን ለመልቀቅ መገደዳቸው ታውቋል። መምህራን ወያኔ ባሰማራቸው የደህንነት መስርያ ቤት ባልደረባ ምመህራንና በወያኔ ስር በተደራጀ የወጣት ማህበራት ሰላዮች ክትትል እንደመደረግባቸው ታውቋል።

Ø የታንዛኒያ ባለስልጣኖች በታንዛኒያ የእስር ዘመናቸውን የጨረሱትን 74 ኢትዮጵያውያን በኬኒያ ድንበር ላይ በመጣላቸው በኬኒያ እና በታንዛኒያ መካከል ውዝግብ የቀሰቀሰ ከመሆኑ በላይ የኬኒያ ፖሊስ ስድስት ኢትዮጵያውያንን በህገ ወጥ መንገድ አገር ውስጥ ገብተዋል በማለት ማሰሩን አርብ ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ.ም.በሰጠው መግለጫ ገልጿል።  እንደ ኬኒያ ፖሊስ ከሆነ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሞምባሳ በኩል አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊጓዙ ሲሉ በጥቆማ መያዛቸው ሲታወቅ ከስደተኞቹ ጋር አንድ የኬኒያ ሹፌርም አብሮ ተይዟል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ ያለ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ኬኒያ በመግባት ወንጀል ሲከሰሱ የኬኒያው ሾፌር ደግሞ ስደተኞችን በማስረግ ወንጀል እንደሚከሥ ተጠቁሟል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በብዙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የከፋ መከራና ስቃይ ይደርስባቸው እንደነብር የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ስደተኛነታቸው እንደ ጥፋት እየተቆጠረ መታሰር እየተለመደ በመጣቱ ድምጽ አልባ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁሉም ወገን በሚችለው አቅሙና መንገድ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ኤጄንሲ እንዲያሳውቅ ሀገር ወዳድ ዜጎች ጥሪ ያቀርባሉ።

Ø የሶማሊያው አልሸባብ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓም ስድስት የወያኔ ወታደሮችን መንገድ ላይ በተቀበረ ፈንጅ መግደሉን አስታውቋል። የፈንጅ አደጋውን በደቡባዊ ባይ ግዛት ውስጥ አውደሊን ከተማ አቅራቢያ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በጥቃቱ ወቅት የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ ያሰማራቸው ሰላም አስከባሪ በወታድር አጀብ ይጓዝ እንደነበረና ከሞቱት የወያኔ ወታደሮች ውስጥ ከፍተኛ አዛዦች እንደሚገኙበት አብራርቷል። በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል አልሸባብ አደረስኩ ስለሚለው ጥቃት የተናገረው ነገር የለም። የወያኔ አገዛዙም እንደተለመደው የተነፈሰውና ያለው ነገር አልተመዘገበም።

Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሚስተር ሪክ ማቻር ቅድሜ ሚያዚያ 15 2008 ዓ.ም.  ጁባ እንዲገቡ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሰጠውን ቀነ ቀጠሮ አሁንም ያልተከበረ መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ዓመት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ሚስተር ማቻር ጁባ እንዲገቡ ታቅዶ የነበረው ሚያዚያ 10 ቀን 2008 መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አጅበው በሚገቡ ወታደሮች ብዛት ላይ እና ሊይዟቸው በሚችሉ የመሳሪያ ዓይነቶች ላይ ከሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ጋር ስምምነት ባለመደረሱ ጉዟቸው የዘገየ መሆኑ ተነግሯል፡፤ ትናንት አርብ ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓም በነፍስ ወከፍ ኤኬ 47 አውቶማቲክ መሳሪያ ከታጠቁ 190 አጃቢዎች  እና 20 መትረየሶችና ከ20 አርፒጂ ጋር እንዲገቡ ስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር እንደገለጹት ሚስተር ሪካ ማቻር የሚጓዙበት አውሮፕላን ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚፈቀድለት ከጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ከመነሳቱ በፊት የሚመጡት ሰዎች ቁጥርና የያዙት መሳሪያ በስምምነቱ መሰረት መሆኑን የዓለም አቀፍ ድርጅት አባላት ማረጋገጫ ከሰጡ በኋላ ብቻ ነው ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እንዲሁም አሜሪካ እንግሊዝ እና ኖርዌይ ሚስተር ሪክ ማቻር እንዲመለሱ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸው ተነግሯል።

 

Ø በግብጽ የቀድሞው ፕሬዚዳንት መሀመድ ሞርሲ የካታር መንግስት ሰላይ ናቸው በሚል ቀርቦባቸው የነበረው ክስ ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን ሊታይ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ዝግጅት ያስፈልጋል በሚል ለሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም.  ያስተላለፈው መሆኑ ተነግሯል። ካታር የሚስተር ሞርሲን አስተዳደርና የግብጽን የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበር ስትረዳ መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን  የፕሬዚዳንት ሲሲ አስተዳደር ካታር በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች በሚል ክስ ትታሰማ መቆየቷም ይታወቃል። በፕሬዚዳንት ሲሲ እና በተባባሪዎቻቸው አማካይነት በተካሄደ ወታድራዊ መፈንቅለ  መንግስት በስልት ከስልጣናቸው የተነሱት ሞርሲ ከዚህ ቀደም በሶስት የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የሞት ፍርድ፤ የእድሜ ልክ እስራትና የሃያ አመታት እስራት የተበየነባቸው መሆኑ ሲታወቅ ይህኛው ክስ አራተኛው መሆኑ ነው። ሞርሲ እና ሌሎች አስር ሰዎች የግብጽ የጸጥታ ሁኔታን የሚመለከቱ ሚስጥራዊ ሰነዶች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብለው ከካታር ሸጠዋል የሚል ክስ አቃቤ ህጉ ያቀረበባቸው መሆኑ ታውቋል።

 

Ø በዚህ ሳምንት በማሊ በአማጽያን ታግተው የነበሩ ሶስት የቀይ መስቀል ሠራተኞች አለምንም ቅደመ ሁኔታ የተለቀቁ መሆናቸው ተነገረ። በሰሜን ማሊ የሚንቀሳቀሰውና ከአልካይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው አንሳር ዲን የተባለው ድርጅት ባለፈው ሐሙስ በሰጠው መግለጫ ሰራተኞቹን ያገተው ድርጅቱ መሆኑንና ሊፈቱ የሚችሉት በፈረንሳይ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ያለው ሚያቴን አግ ማያሪስ የተባለው የድርጅቱ አባል ሲፈታ ብቻ መሆኑን ገልጾ እንደነበር ይታወሳል። አርብ ዕለት ታግተው የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች መለቀቃቸው የተነገገረ ሲሆን ሊለቀቁ የቻሉትበፈረንሳይ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው ግለሰብ ስለተለቀቀ ይሁን አይሁን አልታወቀም። ሰላም በማስከበር ስም ፈረንሳይ በሰሜን ማሊ ከ3500 በላይ የሆኑ ወታደሮች እንዳላት ይታወቃል።

 

Ø በምስራቅ ሊቢያ ራሱን መንግስት ነኝ የሚለው ክፍል ፓርላማ በተመድ አማካይነት የተቋቋመውን መንግስት ለመደገፍ ውደ ኋላ ሲል መቆየቱ ይታወሳል። ባለፈው ሐሙስ 198 ከሆኑት የምክር ቤቱ አባላት መካከል 108 የሚሆኑት የአንድነት መንግስቱን መደገፋቸውን በመግለጽ መግለጫ ያወጡ ቢሆንም በዙዎቹ በግል ማስፈራሪያ ስለደረሳቸው ድምጽ ሊሰጥበት የሚችል ስብሰባ ማካሄድ ያልቻሉ መሆኑ ተገልጿል። አርብ ሚያዚያ 14 ቀን የምዕራብ መንግስታት አምባስደሮች በሰጠቱ መግለጫ ማስፈራሪያውን በጽኑ አውግዘው አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት የተደረገባቸውን ተጽእኖ ተቋቁመው ድምጻቸውን ለማሰማት መቻላቸውን አወድሰዋል። ምከር ቤቱ ተሰብቦ ውሳኔዎችን በህጋዊ መንገድ እንድያስወስንም ተማጽነዋል።

 

 

 

ሚያዚያ  14 2008 ዓ ም

Ø በጋምቤላ የደረሰውን አሰቃቂና ዘግናኝ እልቂት በመቃወም ዜጎች በተለያዩ መንገዶችና ዘዴዎች ተቃውሟቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሰንጋ ተራ በሚባለው አካባቢ ተማሪዎች ፊታቸውን ጥቁር ቀለም በመቀባት በጋምቤላ የደረሰውን ፍጅት በመቃወወም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ እየጠየቁ ባለበት ሰዓት ከሆቴል ደ  አፍሪክ ከሚባለው ሆቴል አካባቢ የነበረው የወያኔ የፖሊስ ኃይል ተማሪዎቹን በዱላ በመደብደብ ማባረሩን በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል። እነዚህ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና  በራሳቸው ፍላጎት ለወገኖቻቸው ሞትና መታፈን የቆሙ ወገኖች መደብደባቸው ብቻ ሳይሆን ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል።

 

Ø በጋምቤላ የተፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት ተከትሎ ልዩ ልዩ አገራትና ድርጅቶች የውግዘት ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት ፍጅቱን በማውገዝ የታገቱት ህጻናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መጠየቁን የዘገብን ሲሆን ሀሙስ ዕለትም የአውሮፓው ህብረት በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱት ህጻናት እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል። የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣኖች ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተው የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት በአስቸኳይ የታገቱት ልጆች ወደ ቤተሰባቸው እንዲመለሱ ጥረታቸውን እንዲጨምሩና ፍጅቱን ያካሄዱት ለህግ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።

 

 

Ø የጋምቤላውን እልቂት ተከትሎ ደቡብ ሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች እርስ በርስ መካሰስ መጀመራቸው ታውቋል። የሱዳኑ ዕለታዊ ጋዜጣ ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና ጀኔራሎች ለጋምቤላው ፍጅት የቦማ ግዛት ኃላፊዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ግዛት ገዥ ባባ ሜዳ ለጥቃቱ ጀርባ እንደሆ የመርሌ ጎሳ አባል የሆኑት /ጄኔራል ዲቪድ ዋዩ ተናግረው መረጃውን ከአካባቢው መሰብሰባቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ግዛት ኃላፊዎች ለእልቂቱ የጦር መሳሪያ በማቀበል በኑር ጎሳ አባላት ላይ ጥቃቱ ንዲፈጸም አስተባብረዋል በማለት የቦማ ባለሥልጣኖች የያገተቱን ህጻናት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። የቦማ ግዛት ኃላፊዎች ግን የተሰነዘረባቸውን ክስ በማስተባበል በጋምቤላው ጥቃት እጃቸው እንደሌለና በግዛቱ ያሉ ታጣቂዎችም የደቡብ ሱዳን ጦር አባል ሆነው መካተታቸውን ተናግረዋል።

 

Ø ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓም አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ባወጣው ዘገባ ባለፈው ታህሳስ ወር የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም  350 የሚሆኑ የሺያ እስላም ተከታዮችን ገድሏል፣ አስከሬናቸውን በአንድ ጉድጓድ ውስጥ በጅምላ ቀብሯል፣ እንዲሁም ድርጊቱን ለመሸፈን የተለያይ እርምጃዎችን ወስዷል በማለት ወንጅሎታል። የሰብአዊ ድርጅቱ በመግለጫው ላይ ሟቾቹ የተገደሉት የአንድ ወታደራዊ ክፍል መሪ የነበሩትን ጄኔራል ለመግደል ሙከራ ሲያደርጉ ነው በሚል ከናይጄሪያ መከላከያ ተቋም የተሰጠውን ምክንያትም መሰረተ ቢስ ነው በማለት አጣጥሎታል። የናይጄሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል  በአምነስቲ የቀረበው ዘገባ ነጻና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ አለመሆኑን ገልጾ ዘገባውን ከማውጣቱ በፊት ስለዝርዝሩ ሊያሳውቀንና አስተያየታችንን ሊጠይቅ ይገባው  ነበር ብሏል። ትክክለኛ መረጃ አለን ካሉ ያቅርቡና ያሳምኑን የሚል ቃልም አሳምቷል።  ባለፈው ታህሳስ ወር የኢስላሚክ ሙቭመንት ኦፍ ናይጄሪያ የተባለው የሺያ ሙስሊም ድርጅት  አባላት በሰሜን ናይጀሪያ ውስጥ በጸሎት ላይ እያሉ በነበረት ወቅት የወታደራዊ ተቋም መሪ የየሆኑት ጄኔራልን አጅቦ የነበረው ኮንቮይ በአካባቢው እንዳያልፍ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ በማሰማታቸው  ወታደሩ በወሰደው የበቀል እርምጃ ከ350 ሰዎች በላይ ለመግደል ችሏል ተብሏል። ይህንንም ሀቅ ባለፈው ሳምንት አንድ የናይጄሪያ ከፍተኛ ባለስልጣን የመሰከረ  መሆኑ ተገልጿል። አምነስቲ ኢንተናሽናል በዘገባው ላይ ፕሬዚዳንት ቡሃሪ በጉዳዩ ላይ ምርመራ ተካሄዶ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ብለው ቃል ቢገቡም እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም ሲል  ዘግቧል። እንዲያውም በተጻራራው  የናይጀሪያ የዜና አውታሮች ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን  በዘገቡት ዜና ካዱና በተባለችው ከተማ 50 የሚሆኑ የሺያ እምነት ተክታይ አባላት አንድ ወታደር ገድለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው እየተጠየቀ መሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቤት ንብረታቸውን ጥለው በተሰደዱ ዜጎች ካምፕ አጠገብ አንዲት የቦኮ ሃራም  አጥፍቶ ጠፊ ባፈነድችው ቦምብ ሰባት ሰዎች የተደሉ መሆናቸውን የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቃል አቀባይ ሐሙስ ዕለት ከሰጠው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። የቦምቡ ፍንዳታ የደረሰው ባለፈው ረቡዕ ሚያዚያ 12 ቀን 2008 ዓም በንጋቱ ላይ ሲሆን ማይዱጉሪ ከተባለው ከተማ 130 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ የናይጄሪያና የካሜሩን ወሰን ላይ ነው። ቦምቦችን ለማፈንዳት  ቦኮ ሃራም ከላካቸው ሁለት ሴቶች መካከል አንደኛዋ የያዛቸውን ቦምብ ሳታፈንዳ እጅ ከፍንጅ ተይዛለች ተብሏል። ቦኮሃራም አእምሮ የሚመረዝ እጽን እየሰጠ ቦምብ እንዲያፈነዱ የሚልካቸው ሴቶችና ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ ይታወቃል።

 

Ø ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ይፋ ባደረገው ዘገባ በግብጽ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ያሉ እስረኞች ሰቆቃዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው መሆኑን አጋልጧል። ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ህጻናት መሆናቸውንም ገልጿል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቱ ይፋ ባደረገው ዘገባ ባለፈው የካቲት ወር ህገ ወጥ በሆኑ የተቃዋሚ ስልፎች ላይ ተሳትፋችኋል፤ የንብረትና መዝረፍና የማቃጠል ወንጀል ፈጽማችኋል ተብለው  በአሌክሳንድሪያ የታሰሩ ዜጎች በእስር ላይ እያሉ ከፍተኛ ድብደባና የአካል ስቃይ የደረሰባቸው መሆኑን ለቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ዘግቧል። ድርጅቱ ከ20 በላይ በሚሆኑ እስረኞች ላይ ድብደባ እንደተፈጸመ መረጃ የደረሰው መሆኑን ገልጾ የግብጽ መንግስት ከፍተኛ ድብደባ የፈጸመባቸው እስረኞች በቁጥጥር ስር መደረጋቸውን በመጀመሪያ ክዶ የነበረ መሆኑን የሰብአዊ መብት ድርጅት መግለጫ ያጋልጣል። የግብጽ ባለስልጣኖች ዘገባው የፈጠራ መረጃው የያያዘ ነው በማለት አጣጥለውታል።  ወታደራዊ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ በዜጎች ላይ የሚወስደው አሰቃቂ እርምጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በየጊዜው የተገለጸ ሲሆን ባለፈው ዓመት በቁጥጥር ስር የሚገኙ እስረኞችን በድብደባ  ገድላችኋል ተብለው በርካታ የግብጽ ፖሊሶች ክስ ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸው መሆኑ ይታወሳል።

 

Ø የቻዱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዲቢ ለአምስተኛ ጊዜ በምርጫ አሸንፈው ስልጣን የተቀዳጁ መሆኑ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ተነገረ። ኢድሪስ ዲቢ  የድምጹን 60 ከመቶ በማግኘት  17 የሚሆኑ ተወዳዳሪዎቻቸውን አሸንፈው ነው ድል ተቀዳጅተዋል የተባለ ሲሆን ያገኙት ከድምጹ 50 ከመቶ በላይ በማግኘታቸው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ማካሄድ አላስፈለጋም። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫው የተጭበረበረ ስለሆነ አንቀበለውም ብለዋል። በርካታ የምርጫ ሳጥኖች የተሰረቁ መሆናቸውንና ፤ ወታደሮችን ጨምሮ ኢድሪስ ዲቢን  በመቃወም ድምጽ የሰጡ ግለሰቦች መታሰራቸውና መዳረሻቸው መጥፋቱን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎች ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ነው ቢሉም በርካታ ሰዎች ያልተዋጠላቸው መሆኑ ታይቷል። በምርጫው ወቅት የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በሞባይል ስልኮች መልክቶችን መለዋውጥ ሳይቻል ቀርቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት አራት የሲቪል ማህበራት መሪዎች ሕዝቡን ለስላማዊ ስልፍ አነሳስታችኋል በማለት መታሰራቸው ይታወሳል። ምርጫው የተካሄደው የሆስፒታል ሰራተኞች የትምህርት ቤት አስተማሪዎችና የዩቢቨርስቲ ፕሮፈሰሮች የተወዘፈ ደሞዛቸው እንዲከፈል የስራ ማቆም አድማ ባደረጉበት ወቅት ነው። ቻድ በ1995 ዓም በአገሪቱ የተገኘውን የነዳጅ ምርት መጠቀም ብትጀምርም 13 ሚሊዮን የሚሆነው የአገሪቱ ዜጋ ከድህነት በታች በሆነ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚኖር ሲሆን  ከቻድ ዜጎች መካከል ከ 10 ሩ  ሰባቱ መጻፍ እና ማንበብ እንደማይችሉ መረጃዎች ይፋ አድርገዋል።

 

 

Ø 36 የጋምቢያ  የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና አባላት ሐሙስ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው በልዩ ልዩ ወንጀሎች የተከሰሡ መሆናቸው ተገለጸ፡፤ የዩናይትድ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሚስተር ዳርቦይ ከተከሰሱት መካከል አንዱ ሲሆኑ ተካሶቹ በስድስት የተለያዩ ክሶች የተከሰሱ መሆናቸውና በዋስ ለፈቱ መቻላቻውና አለመቻላቸው በሚቀጥለው ሳምንት እስከሚወሰን ድረሰ በእስር ቤት እንዲቆዩ የተደረገ መሆኑም ተነግሯል። የዩናይትድ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ጸሐፊ ሚስተር ሳንዴንግ እና ሌሎች ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ያልተፈቀደ ሰላማዊ ስልፍ አደራጅታችኋል በሚል ሰበብ የታሰሩ መሆናቸው ሲታወቅ ግለሰቡና ሌሎች ሁለት ሴቶች በእስር ቤት በድብደባ ህይወታቸው ያለፈው መሆኑ ተነግሯል። የፓርቲው መሪ ሚስተር ዳርቦይ እና ሌሎች ተከሳቾች የታሰሩት ባለፈው ቅዳሜ ቀደም ብለው የታሰሩት አባሎቻቸው የታሰሩበት ምክንያት አለአግባብ አለመሆኑን ለመግለጽ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያደርጉ ነው ። የአፍሪካ የሂውማን ራይትስ ኮሚሽን እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የታሰሩትን  ለመጎብኘት እንዲችሉ ፈቃድ የጠየቁ መሆናቸው ታውቋል። 

 

 

 

ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø ስድስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የጋምቤላ እልቂት በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ ሕጻናት ሊገኙ አለመቻላቸው አጠያያቂ እየሆነ ነው። ዓለም አቀፍ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሲኤፍም ከጋምቤላ የተጠለፉ ሕጻናት አለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አድርጓል። በጋምቤላው እልቂት ከ200 ሰው በላይ ተገድለው በመቶ የሚቆጠሩ ቆስለው ከ20 ሺ በላይ ከቀየው ተፈናቅሎ መሰደዱም ታውቋል። የወያኔ መሪዎች ከቀያቸው ለተፈናቀሉት ዜጎች የሚያደርጉት እንክብካቤ በጋምቤላ ካሉት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በጣም ያነሰ እንደሆነ እየተገለጸ ሲሆን የወያኔ ወታደራዊ አለቆች ህጻናቱን ለማስለቀቅ ፍንጭ አግኘተናል አካባቢውን እየከበብን ነው ይበሉ እንጅ ዝርዝር ጉዳዮችን ግን አላብራሩም።

Ø የአባይን ግድብ አስመልክቶ በወያኔ በግብጽና በሱዳን መካከል የሚደረገው የዙር ንግግር ባለበት እርገጥ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት የወያኔ የግብጽና የሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች ካርቱም ላይ አንድ ዝግ ስብሰባ ማድረጋቸውን የሱዳን ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዋናነት የአባይ ግድብን በሚመለከት መምከራቸው ታውቋል።

 

Ø ባለፈው ሳምንት በምዕራብ አፍሪካ በምትገኘው ጋምቢያ ውስጥ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ አደራጅታችኋል በሚል ወደ 40 የሚጠቁ ዜጎች ተከሰው ፍርድ ቤት የቀረቡ መሆናቸው ተገለጸ። ባለፈው ሳምንት በጋምቢያ ውስጥ ሀገሪቱ የምርጫ አሰራርና ህግ እንዲሻሻል ለመጠየቅ በተቃዋሚ ፓርቲዎች አደራጀነት ከፍተኛ የተቃውሞ ስልፍ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ፖሊስ ስልፉን ለመበተን ጥያት የተኮሰ መሆኑና በርካታ ሰዎችም ይዞ ተነግሯል። ተይዘው ከነበሩት መካከል ሶስት የተቃዋሚው ፓርቲ ነባር አባላት በእስር ቤት ውስጥ መገዳላቸው ይታወቃል። ጋምቢያ በሚቀጥለው ዓመት ታህሳስ ወር ውስጥ ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ ማቀዷ ታካሄዳለች ተብሏል።

 

Ø በብሩንዲ ዋና ከተማ በብጁምብራ አንድ የኮሎኔል ማዕረግ ያለው ወታደራዊ መኮንን ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ የአገር ውስጥ የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ኮሎኔል አማኑኤል ቡዙቦና የተባለው መኮንን የተገደለው ከአንድ ሌላ ሰው ጋር በሞተር ቢስክሌት እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ላይ ሲሆን አብሮት የነበረውም ሰው የተገደለ መሆኑ ታውቋል። በብሩንዲ ውስጥ የርስ በርስ ግጭት ከተጀመረ ወዲህ   ወታደራዊ መኮንኖች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በተደጋጋሚ እየተገደሉ መሆናቸው ሲታወቅ የመንግስቱን ስልጣን በያዘው ኃይልና በተቃዋሚዎች መካከል እርቅ እስካልሰፈነ ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ።

 

Ø ባለፈው ማክሰኞ ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓም ለረቡዕ አጥቢያ  የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች  በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ዳማቱሩ ከተማ በሚገኝ አንድ መንደር ውስጥ በፈረስ ሆነው ወረራ ከአካሄዱ በኋላ 11 ሰዎች የገደሉ መሆናቸው በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ለዜና ምንጮች ገልጸዋል። ከሁለት ሳምንት በፊትም ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽመው 20 ሰዎች መግደላቸው ተነግሯል። የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች እኩለ ሌሊት ላይ ወደ መንደሯ ገብተው የእሩምታ ተኩስ ሲከፍቱ ነዋሪዎች በመደናገጥ ቤታቸው እየጣሉ የወጡ ሲሆን በነበረው ተኩስ አስራ አንድ ሰዎች መገደላቸውና እና ሌሎች ቀጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ነዋሪዎቹ ተናግርዋል፡፤  አጥቂዎቹ እህል ንብረትና ከብቶች ከዘረፉ በኋላ መንደሩን አቃጥለው የሄዱ መሆናቸው ታውቋል፡፤ አሸባሪዎቹ  የድብቅ ካምፖችን በመስራት የጦር ስፈር አድርገው ከቆዩበት ሳምቢሳ ከተባለው ጫካ ሳይመጡ አልቀረም የሚል ግምት አለ። የናይጀሪያ ወታደራዊ ተቋም ቦኮ ሃራምን ማጥቃቱንና ማዳከሙን በመግለጽ በተደጋጋሚ መግለጫ የሰጠ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ቡድኑ  ጎላ ያለ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚያካሂዳቸው ጥቃቶች አለመዳከሙን ያሳያል የሚሉ በርካታ ናቸው።

 

Ø በደቡብ አፍሪካ ላለፉት አራት ዓመት ከመስሪያ ግዥ ጋር ተያይዞ ፕሬዚዳንት ዙማ እና ሌሎች ባለስልጣናት ከፍተኛ ሙስና ፈጸመዋል በሚል ቀርቦ የነበረው ክስ ሲያጣራ የነበረው ኮሚሽን ስራውን መፈጸሙንና ፕሬዚዳንቱን ነጻ ማውጣቱን ፕሬዚዳንት ዙማ በሰጠቱ መግለጫ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ሐሙስ ሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በሰጡት መግለ ኮሚሽኑ ዘገባውን ያቀረበው ከአራት ወራት በፊት ቢሆንም አሁን ለሕዝብ ይፋ ሆኗል ካሉ በኋላ ባደረገው ምርመራ መሰረት በእሳቸውም ሆኖ በሌሎች ላይ ምንም ጥፋት ያላገኘ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ዙማ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በነበሩበት ወቅት እሳቸውና አማካሪዎቻቸው ከዓለም አቀፍ የመስራሪያ ሻጭ ድርጅቶች በርካታ ገንዘብ ወስደዋል ተብለው ተከሰው የነበሩ ሲሆን አማካሪያቸው በተመሳሳይ ክስ የአስራ አምስት ዓመት እስራት የተፈረደባቸው መሆኑና ተቃዋሚዎች በአቃቤ ህጉ ላይ ያልሆነ ተጽእኖ አምጥተዋል በሚል ምክንያት በዙማ ላይ የነበረው ክስ እንዲነሳ ተድርጎ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ዙማ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ጉዳዩን እንዲመረምር አዲስ ኮሚሽን ቢያቋቁሙም፤ አካሉ ኃይል እና ስልጣን ኖሮት አለተጽእኖ  ስራውን ሊያከናውን የሚችል አይደለም በማለት አንዳንድ ወገኖች  ሲያጣጥሉት እንደነበር አይዘነጋም።

 

 

 

 

ሚያዚያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø የወያኔ መሪዎች የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ዘመን እያሉ በሚጠሩት የህልም እቅድ ሰባትና ከዚያም በላይ ስኳር ፋብሪካ እንገነባለን፤ ስኳር ከእኛ ፍላጎት በላይ አምርተን ወደ ውጭ እንልካለን በማለት ፕሮፓጋንዳ ሲነፉ የቆዩ መሆናቸውና  የወያኔም የፕሮፓጋንዳ ወፍጭዎች ይህን ተቀብለው ማስታጋባታቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የስኳር እጥረት በመኖሩ ስኳር ከውጭ ለማስገባትና ዋጋውን ለማናር ዝግጅት መደረጉ እየተነገረ ነው። የወያኔ መሪዎች የስኳር ፋብሪካ ይገነባበታል የተባለውን በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከመዘበሩ ወዲህ አሁን ደግሞ ስኳር ከውጭ በማስመጣት ና በመቸብቸብ ትርፍ ለማግኘት ያቀዱ ሲሆን የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋ አሁን ባለበት 18 ብር ከ60 ሳንቲም ወደ 21 ብር ከፍ እንደሚል ታውቋል። የዋጋ ጭማሪው ስኳሩ ከውጭ ስለሚመጣ የውጭ ምንዛሬ ማጣጫ ነው ተብሏል።

Ø በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱና የነዳጅ ማዳያዎችም በመኪናዎች ስልፍ መጨናነቃቸው ታውቋል። የነዳጅ ዕጥረቱ በተለይ በናፍታ ላይ የበረታ ሲሆን ይህን ተከትሎ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተደርሶበታል። በአሁኑ ወቅት  የነዳጅ ዕጥረቱ ለምን እንደተከሰተ የወያኔ መሪዎች የሰጡት ይፋ ማብራሪያ የሌለ ሲሆን አንዳንድ ከፍተኛ ካድሬ ነን ባዮች በቅርብ በጣለው ኃይለኛ ዝናም  በጂቡቲ መስመር የሚገኙ መንገዶችንና ድልድዮች ከጥቅም ውጭ በማድረጉ የመጫኛ ቦቴዎች እንደልብ መንቀሳቀስ ባለማቻላቸው በማለት ለመግለጽ ይሞክራሉ።

Ø በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የመኪና ብዛትና በመኪና ግጭት ምክንያት የሚሞተው ሰው ተመጣጣኝ አለመሆኑና በትራፊክ አደጋ የሚሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ሪፖርት በሚደረግበት ሰዓት በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓም. በሰሜን ወሎ በቆቦ ከተማ እጅግ አሳዛኝ የመኪና አደጋ የደረሰ ሲሆን በዚህ አደጋ በትንሹ የ 25 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ታውቋል። አደጋው ከጠዋቱ አስር ሰዓት መድረሱን የገለጸው መረጃ  ሸቀጣ ሸቀጦችን ጭኖ ከመቀሌ ይመጣ የነበረ አንድ ከባድ ካሚዮን 16 ተሳፋሪዎችን ይዞ ከቆቦ ወደ አላማጣ ይጓዝ ከነበረ ሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ሲታወቅ በግጭቱ አቅራቢያ የነበሩ በእግርና በብስኪሌት ይጓዙ የነበሩም ህይወታቸው መጥፋቱ ታውቋል።

Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሪክ ማቻር በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ በጁባ እገባለሁ ባሉበት ቀን ባለመግባታቸው በደቡብ ሱዳን ሰላም ሊወርድ ይችላል የሚለውን ተስፋ ያጨለመ  መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። ማቻር ጁባ ይገባሉ ተብሎ የነበረው ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን ላለመሄዳቸው የሎጂስቲክስ ችግር እንደ ምክንያት ሆኖ ሲገለጽ ቆይቷል። የደቡብ ሱዳን መንግስት ማክሰኞ ዕለት ከሰጠው መግለጫ ለማወቅ እንደተቻለው ለጉዞው መዘግየት ምክንያት የሆነው ጉዳይ ማቻር ከስምምነቱ ውጭ በርካታ መሳሪዎችን የፀረ ታንክ የሆኑኑ በሌዘር የሚመሩ ሚሳየሎችና እንዲሁምከባድ መሳሪዎችን ይዘው ለመምጣት በመፈለጋቸውና በመከልከላቸው ነው ተብሏል።  እርቁን በማስተባበር  በኩል ግምባር ቀደም ሚና የነበራቸው የቀድሞ የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን የፈረሙበትን መንፈስ እንዲጠብቁና እንዲያከብሩ ተማጽነዋል። አሜሪካ እና ሌሎች የምእራብ አገሮች ሚስተር ማቻር ቃል በገቡት መሰረት ወደ ጁባ አለመሄዳቸው በሰላሙ ሂደት ላይ ከፍተኛ አደጋ ፈጥሯል ብለዋል። የአማጽያኑ ቃል አቀባይ ለሚስተር ማቻር ጉዞ መዘግየት አሁንም የሎጂስቲክስ እና የአስተዳደር ችግር መሆኑን ገልጾ ረቡዕ ዕለት ወደ ጁባ ይገባሉ የሚል ቃል ሰጥቷል።

 

Ø ሳምንቱ መጀመሪያ ጀምሮ በዛምቢያ ዋና ከተማ በሉሳካ በውጭ ዜጎች በተለይም በሩዋንዳ ዜጎች ላይ ሲካሄድ የነበረው ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሎ ቢያንስ ሁለት ሰዎች በህይወታቸው መቃጠላቸው ታውቋል። ችግሩ የጀመረው  በዛምቢያ የሚኖሩ የሩዋንዳ ዜጎች ባህላዊ ተግባራቸውን ለመወጣት በሚል ሰባት የሚሆኑ ዛምብያውያንን ገድለውና  የአካሎቻቸውን አንዳንድ ክፍሎች ወስደው፣ አስከሬናቸውን መንገድ ላይ ጥለዋል በሚል በተነሳ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነው። ዜጎችን ገድለዋል የተባሉ 10 ሩዋንዳውያን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ቢደረጉም ተቃውሞ ቀጥሎ የሩዋንዳ ስደተኞች  ሱቆች የተዘረፉ መሆናቸውና ብዙዎችም በድንጋይና በሌሎች መሳሪያዎች ጥቃት ሲደርስባቸው የቆየ መሆኑ ተገልጿል። እስከማክሰኞች ሚያዚያ 11 ቀን ድረስ ከ62 በላይ ሱቆች የተዘረፉና የወደሙ ሲሆን መኪኖችና ሌሎች ንብረቶች ተቃጥለዋል። ፖሊስ ግጭቱን ለማብረድ በወሰደው እርምጃ በውጭ ዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ተገኙ ያላቸውን ከ200 ሰዎች በላይ በቁጥጥር ስር ያደረገ መሆኑን ገልጿል። በ1986 ዓም ከሩዋንዳው እልቂት ያመለጡ ከ6500 በላይ የሚሆኑ ሩዋንዳውያን በዛምቢያ የሚገኙ መሆናቸው ይታወቃል።

 

 

Ø በሰሜን ማሊ በእርዳታ መስጠት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይሰሩ የነበሩ ሶስት የቀይ መስቀል ሰራተኞች ከቅዳሜ ጀምሮ ግንኙነት ያቋረጡ መሆናቸው ተነገረ። የእርዳታ ሰጭው ድርጅት ሠራተኞች መዳረሻቸው የጠፋው በሰሜን ማሊ ከአንድ መንደር ተነስተው ኪዳል ወደ ተባለው ከተማ በመገዝ ላይ እያሉ ሲሆን ምናልባት በአካባቢው ባሉ አማጽያን ኃይሎች ተጠልፈው ሳይወሰዱ አይቀርም የሚል ስጋት ፈጥሯል። የጠፉት ሰዎች ዜግነት ምን እንደሆን ባይታወቅም በደፈናው አፍርካውያን መሆናቸውን የቀይ መስቀል ቃል አቀባይ ገልጿል። በሰሜን ማሊ ከአልካይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባል የአማጽያን ቡድን የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት ቡድኑ የጠለፋቸው  አራት የቀይ መስቀል ሰራተኞች በፈረንሳይ ወታድሮች አማካይነት ሊለቀቁ የቻሉ መሆናቸው ይታወሳል።

 

Ø የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ማክሰኞ ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓም ሞሮኮ ያስወጣቻቸው የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ባስቸኳይ እንዲመለሱ ጠይቀው ይህ ካልተደረገ ሁኔታውን አክራሪ ኃይሎች ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አስጠንቀቀዋል። ባንኪ ሙን ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን ለተመድ የጸጥታ ምክር ቤት በላኩት ዘገባ የተባበሩት መንግስታት አካል ከምዕራብ ሳህራ ግዛት እንዲወጣ መደረጉ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተጥሶ ጦርነቱ እንደገና የሚጀመርበትን እድል ያጎለብተዋል ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሚያዚያ 20 ቀን 2008 በምዕራብ ሳህራ ግዛት የተመድ ተልእኮ ስለመቀጠሉና አለመቀጠሉ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የባንኪ ሙን ዘገባ በጉዳዩ ላይ ሞሮኮን ደግፈው በሚገኙት በፈረንሳይና በስፔን ላይ ተጽእኖ ሊያደርግ ይችላል የሚል ግምት ተወስዷል። በምዕራብ ሳህራ የስፔን ቅኝ ግዛት ሲያበቃ ሞሮኮ ግዛቱ የኔ ነው ብላ ለመጠቅለል ያደረገችውን ሙከራ በመቃውሞ ፖሊሳሪዮ የተባለ ነጻ አውጭ ድርጅት ለረጅም ዓመታት የትጥቅ ትግል ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወሳል። በ1983 ዓም በተመድ አካማካይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላ የግዛቱን ህልውና በውሳኔ ሕዝብ ለማስወሰን የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ወደ ግዛቱ መላኩ ይታወሳል። ድምጽ ሊሰጥ የሚችለው ማን ነው በሚለው ላይ ስምምነት ሊደረስ ባለመቻሉ እስካሁን ድረስ በውሳኔ ሕዝብ የአገሪቱን እድል ለመወሰን አልተቻለም። በቅርቡም የፖሊሳሪያ ድርጅት መሪ ተመድ ጠንከር ያለ እርምጃ ካልወሰደ ጦርነቱ እንደገና ሊጀመር እንደሚችል የሚገልጽ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው አይዘናጋም።

 

 

 

ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በኢኩዌዶሮ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 413 የደረሰ ሲሆን ከ2500 በላይ የሚሆኑት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። ሰው የማዳኑ ፍለጋ  አሁን የቀጠለ ሲሆን ጊዜው እየጨመረ በሄደ መጠን የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል ተገምቷል። በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የፈረሰውን እንደገና ለመጠገን በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጭ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ላለፍት ሰባ አመታት በአገሪቱ ላይ ከደረሱት አደጋዎች መካከል ይህኛው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን  በምዕራባዊ ግዛት የተለያዩ አነስተኛ የመሬት መንቀጥቀጦች መድረሳቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከፍተኛው ኃይል 5.1  ነው ተብሏል።

 

Ø ዛሬ ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓም በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል አንድ አንድ መኪና ላይ የተጫነ ቦምብ ከፈነዳ በኋላ ታጣቂዎች በአደረጉት የተኩስ ጥቃት 28 ሰዎች የሞቱ መሆናቸውና 329 ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል። የታሊባን ቃል አቀባይ ድርጊቱን መፈጸሙን አምኗል። ጥቃቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ጠዋት ላይ በከተማዋ መኖሪያ ቤቶች መስጊዶች ትምህርት ቤቶች እና የንግድ ሱቆች በብዛት በተከማቹበት አካባቢ ከሆነው ከመከላለክያ ሚኒስቴር ቢሮ አጠገብ ነው። ከተገደሉትና ከቆሰሉት መካከል ወታደሮችና የጸጥታ ኃይል አባላት እንደሚገኙበት ተገልጿል። ያልተረጋገጡ ምንጮች አጥቂዎቹ የብሔራዊ ጸጥታ መስርያ ቤትን እንዳጠቁ የተገለጸ ሲሆን ከፍንዳታው ቦታ በጥቂት ርቀት ላይ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተመንግስትም ለጥቃቱ የተጋለጠ መሆኑ ተነግሯል። ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ በተሰጠ መግለጫ የአፍጋኒስታን መንግስት ድርጊቱን የኮነነ ሲሆን “ይህ ዓይነቱ የፈሪዎች ተግባር ጽናታችንንና ቁርጠኛነታችንን አይበግረውም” ብሏል።

 

Ø በኮንጎ ብራዛቪል ፑል ተብሎ በሚጠራው ደቡባዊ ግዛት ከሶስት ሳምንት በፊት የመንግስት ወታደሮች በሄሊኮፕተር አማካይነት ባካሄዱት የአየር ድብደባ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉ መሆናቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት አጋልጧል።  የአየር ጥቃቱ ኒንጃ የተባሉት የቀድሞ የሚሊሺያ ቡድን አባላት ቀደም ብሎ በሰነዘሩት ጥቃት 17 ሰዎችን መግደላቸው ተከትሎ የተደረገ መሆኑን የመንግስት ቃል አቀባይ ቢገልጽም ሄሊኮፕተሮቹ የአየሩን ድብደባ ያካሄዱት በመኖሪያ ቤቶች፤ በትምህርት ቤቶች በአብያተ ክርስቲያን እና በህክምና አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ላይ በመሆኑ ከሰላሳ የበለጡ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል በማለት አምነስቲ አጋልጧል።

 

Ø ባለፈው እሁድ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓም በመካከለኛው አፍሪካ ረፐብሊክ በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ተሰማርቶ የነበረ የሞሮኮ ዜግነት ያለው ግለሰብ በአልታወቀ ሰው የተገደለ መሆኑ ተነግሯል። ግለሰቡ የተገደለው በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ራፋይ በተባለችው ከተማ ሲሆን በኡጋንዳ ውስጥ መሰረት ያደረገው የሎርድ ረዚስታንስ አርሚ የሚባለው ቡድን አባላት ሲያካሄዱ የነበርውን ጥቃት ለመከላከል ሙከራ ሲያደርግ ነው ተብሏል። የተመድ ዋና ጸሐፊ ድርጊቱን ኮንነው ገዳዩ ተይዞ ለፍርድ እንዲቀርብ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማሳሰቢያ ልከዋል፡፤

 

Ø ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ በጁባ ይገባሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የደቡብ ሱዳን የአማጽያን መሪ ሪክ ማቻር እስከማክሰኞ ሚያዚያ 11 ቀን ድረስ ያልገቡ መሆናቸው ታውቋል። ቀደም ብሎ አንዳንድ የሎጂስቲክስ ችግር ጉዟቸውን ያዘገየ መሆኑን ተጠቅሶ ሰኞ ወደ ማታ ገብተው ቃለ መሀላ ይፈጻማሉ የሚል መግለጫ ቢሰጥም እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል። በዛሬው ዕለት የደቡብ ሱዳን አማጽያን ቃል አቀባይ ከጁባ እንዳስታወቀው አሁንም ቢሆን የሎጂስቲክስ ችግሩ ያልተፈታ መሆኑን ገልጾ መች ሊመጡ ይችላሉ የሚለውን መናገር እንደማይችል አስታውቋል። የተባለው የሎጂስቲክስ ችግር ምን እንደሆነ ባይታወቅም ችግሩ ከሳልቫ ኬር መንግስት ባለስልጣኖች ጋር ያለመስማማት ሳይሆን አይቀርም የሚል ሀሳብ በመስጠት ታዛቢዎች ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ።

 

 

Ø በሊቢያ ምስራቃዊ ክፍል ያለውና ራሱን መንግስት ነኝ የሚለው ክፍል ፓርላማ   ትሪፖሊ በገባው የአንድነት መንግስት ላይ አቋም ለመውሰድ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዚያ 11 ቀን ስብሰባ ለማካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም በአባላቱ መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ በመሆኑ ስብሰባው ሳይካሄድ የቀረ መሆኑ ተገልጿል። በውይይትና በድርድር የጋራ የሆኑ ስምምነቶች ላይ ለመድረሰ የአንድነት መንግስቱን የሚደግፉና የሚቃወሙ የምክር ቤት አባላት የወከሏቸው ግለሰቦች የሚገኙበት ኮሚቴ  የተቋቋመ ሲሆን ይህ ኮሚቴ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ሀሳብ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በምክር ቤቱ አባላት መካከል የአቋም መሸጋሸግ ሊኖር ይችላል ከሚል ተስፋ ስብሰባውን ረቡዕ ሚያዚያ 12 ቀን ለማድረግ የታቀደ ቢሆንም እስከዚያው ድረስ ምን ያህሉ አቋማቸውን ሊለውጡ እንደሚችሉ ግልጽ አይደለም።

 

 

 

ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø  ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ጋምቤላ ውስጥ 140 ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። እሁድ ዕለት የወያኔ ባለሥልጣኖች እንደገለጹት በጋምቤላው ፍጅት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 208 መድረሱን 108 ደግሞ ታፍነው መወሰዳቸውን ና 75 የሚሆኑት ቆስለው ህክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የድቡብ ሱዳን ታጣቂዎች 2000 ከብቶችንም መዝረፋቸው ተገልጿል። የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ወደ ጋምቤላ በመግባት በሕዝብ ላይ እልቂት መፈጸማቸው ተራ የጎሳ ግጭት እንደማይመስል የተገመተ ሲሆን ትክክለኛው ምክንያት ግን እስካሁን እንዳልተገኘና የመላ ምት ሀሳቦች እየተወረወሩ መሆናቸው ታውቋል። በጋምቤላ የወያኔ አገዛዝ ሕዝብን ለማሸበርና ለማስጨነቅ በርካታ ጦር ያስፍር እንጅ ድንበር ዘለል ታጣቂዎችን ለማስቆምና ሕዝብን ከእልቂት ለማዳን አለመቻሉ የወያኔ ጦር በጋምቤላ የተቀመጠው የሕዝብን ደህንነትና ድንበር ለማስጠበቅ ሳይሆን የአገዛዙን ህልውናና የአንድ ዘር የበላይነት ለመጠበቅ ብቻ ነው በማለት የሚተቹ ወገኖች ብዙ ናቸው። የወያኔ ጦር ከእልቂቱ በኋላ ታጣቂዎችን እየተከታተልኩና እየደመሰስኩ ነው በማለት መግለጫ አውጥቷል።

 

Ø  የወያኔ አገዛዝ ለመምህራን የመኖሪያ ቤትና ነፃ ትራንስፖርት ሊያቀርብ መሆኑን የወያኔው ትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው የመምህራን ፍልሰትና እጥረትን ለመቋቋም መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቅርቡም የደሞዝ ማስተካከያ የደረጋል ተብሏል። በዕቅዱ መሠረት በከተማና በገጠር ያሉ መምህራን በትምህርት ቤታቸው አካባቢ ቤት እንዲሰጣቸው፣ በገጠር ያለ ሊዝ ክፍያ መሬት እንዲሰጣቸው የሚደረግ ሲሆን በከተማ ደግሞ በአነስተኛ ወይንም በመነሻ ሊዝ መሬት እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለመምህራን ለማከራየት ጊዜያዊ መፍትኄ እንደተባለና በዘላቂነት ግን መምህራኑ በኅበረት የቁጠባ ቤት እንዲሰሩ ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪ የአዲስ አበባ መምህራን በተዘጋጀላቸው ልዩ መታወቂያ በአንበሳ አውቶቡስ በአዲስ አበባ ውስጥ በነጻ ይጓጓዛሉ። ይህ ዕቅድ ከሚቅጥለው ወር ግንቦት ወር ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። ወያኔ ለመምህራኑ የደሞዝ ጭማሪና ጥቅማ ጥቅም ለመስጠት የተገደደው በመምህራኑ  ግፊትና ተጽእኖ መሆኑ ታውቋል።

 

 

Ø  የወያኔ አገዛዝ መሪዎች የሕዝብና የአገር ሀብትን ለመዝረፍና ለመክበር ልዩ ልዩ ፕሮጀክት ነደፍን የልማት ዕቅድ አወጣን በማለት ገንዘብ መሰብሰብና ገንዘብ መዝረፉ በየወቅቱ የተጋለጠና የተዘገበ መሆኑ ይታወሳል። የወያኔ መሪዎች ለዓባይ ግድብ በማለት ገንዘብ በመሰብሰብ ቦንድ በመሸጥ የራሳችውን ኪስ እንደሚያዳብሩ ለትግራይ ተወላጅ ብቻ ተቋራጭና የንግድ ድርጅቶች ኮንታራት እንደሚሰጡ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለአባይ ግድብ የተዋጣ 400 ሺህ ብር መድረሻው አለምታወቁ ተገልጿል። ገንዝቡ ከቦሌ መድኃኒ ዓለም ቤተክርሲትያን ካህናትና ሠራተኞች በወር በወር ከደሞዛቸው የተቆረጠ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በምን ዓይነት ሁኔታ እንደጠፋና የት እንድደረሰ አልታወቀም። ይህ ከአራት ዓመት በፊት የተሰጠ የግድቡ መዋጮ የት ደረሰ ብሎ ሲጠየቅ እስከዛሬ ድረስ ምላሽ ያላገኘው ጉዳይ የወያኔ መሪዎች ከራሳችው ካባ ለባሽ ካድሬዎቻቸውና ከድርጅት ሰዎች ጋር የዘረፉት መሆኑ የታወቀ ሲሆን የበላይ ባለስልጣኖችም ስርቆቱን እያድበሰበሱት ይገኛሉ።

 

Ø  በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ሁኔታን ያከረዋል የተባለ የጦር ሠፈር አሰብ ላይ መቋቋሙን ወታደራዊ ጉዳይን የሚከታተሉ ምንጮች አስታውቀዋል። ሻዕቢያ በአሰብ ወደብ አቅራቢያ ያለውን የአውሮፕላን ማረፊያ ለተባበሩት አረብ ኤምሬት የጦር ሰፈር አገልግሎት የሰጠ ሲሆን የተባበሩት አረብ ኤምሬትም በአሰብ ወደብ ላይ አንድ የባህር ኃይል የጦር ሠፈር እየገነባች መሆኗ ታውቋል። የባህር ኃይሉ የጦር ሰፈር ለ30 ዓመት ኮንትራት የተገነባ ሲሆን ለሻዕቢያ የተሰጠው ክፍያ ግን አልተገለጸም። ሻዕቢያ በየመን የእርስ በርስ ጦርነት ከአረብና ከገልፍ አገሮች ጎን በመቆም 400 ወታደሮቹን በሁቲዎች ላይ ማዝመቱ ይታወቃል። ሳኡዲ አረቢያም ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጎን በመሆን ቀይ ባህርን ሙሉ በሙሉ በአረብ አገሮች ቁጥጥር ስር በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ የፖሊቲካና ወታደራዊ ተጽእኖዋን ለማጠናከር ጥረት እያደረገች ናት ተብሏል። የአረብና የገልፍ አገሮች በተለይም ሳኡዲ አረቢያና የአረብ ኤምሬት የኢራን ፖለቲካዊና ወታደራዊ እንቅስቃሴን ለመገደብ የአሰብ ወደብን እንደመንደረደሪያ እየተጠቀሙበት መሆኑ ተገልጿል።

 

Ø  ቅዳሜ ሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢኩዌዶር በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት እስካሁን ድረስ 278 ሰዎች መሞታቸውና ከ2000 በላይ የአካል ጉዳተኞች መሆናቸው ሲታወቅ ቁጥሩ ከዚህ በላይ ከፍል ሊል እንደሚችል በጣሊያን አገር ጉብኝታቸውን አቋርጠው የተመለሱት የኢኳደር ፕሬዚዳንት በቴለቪዥን ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።  መጠኑ 7.8 የሆነው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የኢኳደርን የወደብ አካባቢዎች በሙሉ ያጠቃ ሲሆን አንዳንድ ከተሞችን ክፉኛ የጎዳ መሆኑ ተነግሯል።  የሰው ህይወትን ለማዳን 10 ሺ ወታደሮችና 3 ሺ አምስት መቶ ፖሊሶች ወደ አካባቢ የተላኩ መሆኑም ተነግሯል። ከመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል አጠገብ የምትገኘው ፔዴርናሌስ በምትባለዋ ከተማ ውስጥ በርካታ ህንጻዎች የተደረመሱ ሲሆን ከ 400 ሰዎች በላይ ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። 300 ሺ ሰው የሚኖርባት ፖርቶቪየጆ በተባለችው ከተማ ውስጥም ህንጻዎችና መንገዶች የተደረመሱ ሲሆን የሰው ህይወትን ለማትረፍ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ተገልጿል። በኢኩዌዶር በደረሰውና ቅዳሜ ጠዋት በጃፓን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ መካከል ግንኙነት የሌለ መሆኑ ሳይንቲስቶች ይናገራሉ።

 

Ø  እሁድ ሚያዚያ 9 ቀን ከግብጽ ወደብ ወደ አውሮፓ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በሚዴትራኒያን ባህር ላይ የሰጠመች መሆኑ ተነግሯል። ጀልባዋ 400 ስደተኞችን ጭና የነበረ ሲሆን ከስደተኞች አብዛኞች የሱማሌ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። በህይወት ከዳኑት መካከል ጥቂቶቹ ወደ ግሪክ ደሴት የተወሰዱ መሆናቸውም ታውቋል። ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 180 ሺ የሚሆኑ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት ጥረት ማድረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ምንጮች ሲናገሩ  ከ800 በላይ የሆኑ ስደተኞች ባህር ውስጥ በመስጠምም ሆነ በሌላ ምክንያት  ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን  ገልጸዋል።

 

 

Ø  በሱማሊያ ውስጥ የአፍሪካ አንድነት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን በመግደላቸው ነዋሪው ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማቱን ከአካባቢው የሚገኘው ዜና ያስረዳል።  የሰማንያ ዓመት አሮጊትና ዘጠኛ አመት ያላት የልጅ ልጃቸው ታመው በአንድ መኪና ወደ ሞቃዲሾ ሲወሰዱ የአፍሪካ አንድነት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ወታደሮች በመንገድ ላይ ተኩስ ከፍተው አሮጊቷንና የልጅ ልጃቸውን እንዲሁም በመኪና ውስጥ የነበሩትን ሌሎች ሁለት ሰዎች የገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። የታችኛው ሸብሌ ግዛት ነዋሪዎች ድርጊቱን በማወገዝ ተቃውሞ አሰምተዋል። የሰላም አስከባሪው ኃይል ባለስልጣኖች ድርጊቱ የተፈጸመ መሆኑን ያመኑ ቢሆንም ወታድሮቹ ተኩስ ሊከፍቱ የቻሉት መኪናው እንዲቆም ቢጠየቅ ለማቆም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው ብለዋል። ከስደስት አገሮች የተወጣጣ 22 ሺ ጦር በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ስም  በሶማሊያ ውስጥ እንደሚገኝ ይታወቃል።

 

Ø  ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቅ በሚገኘው በቦርኖ ግዛት ውስጥ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች የናይጀሪያን ወታደሮች ያጠቁ መሆናቸው ተነግሯል። ውጊያው የተካሄደው ከሜይዱጉሪ ከተማ አጠገብ በምትገኘው ካሬቶ በተባለቸው መንደር ሲሆን ታጣቂዎቹ ስላደረሱት  ሆነ ስለደረሰባቸው ጉዳት ዝርዝር መረጃ አልተኘም።

 

 

Ø  በጋምቢያ ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በእስር ላይ እንዳሉ መገደላቸው ታወቀ። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የተያዙት ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓም የጋምቢያ ወጣቶችና ሌሎች ተቃዋሚዎች በአገሪቱ ውስጥ የምርጫ ሕግና ሂደት ማሻሸያ እንዲደረግበት የሚጠይቁ ሃሳቦችን በማቅረብ ትእይንተ ህዝብ ሲያደርጉ ነው ተብሏል። በወቅቱ ፖሲሶች በተኩስ ስልፉን የበተኑት ሲሆን 25 የሚሆኑ ሰልፈኞችን ያሰሩ መሆናቸውም ታውቋል።  እሁድ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓ.ም. የተመድ ዋና ጸሐፊ ባንኪ ሙን ባወጡት መግለጫ የተቃዋሚው ፓርቲ አባላት በእስር ቤት ውስጥ መገደላቸው በእጅጉ ያሳዘናቸው መሆኑን ገልጸው ስለአገዳደላቸው አስቸኳይ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ጋምቢያ ባለፈው ታህሳስ ወር ብሔራዊ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን የሰብአዊ መብት በማፈን የሚከሰሱትና ከ1986 ዓ.ም፣ ጀምሮ በስልጣን ላይ ያሉት ሚስተር ጃሜህ ለሌላ የስልጣን ዘመን የተመረጡ መሆናቸው ይታወሳል።

 

Ø  በብሩንዲ በስልጣን ላይ የሚገኘው ፓርቲ አባላት የሆኑ አራት ሰዎች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ሰዎቹ የተገደሉት ቅዳሜ ሚያዚያ 8 ቀን በአንድ ቡና ቤት ውስጥ ተቀምጠው እየተዝናኑ ሳለ የወታደር ልብስ በለበሱ የማይታወቁ ሰዎች መሆኑን ከግድያው ያመለጠና ስሙን መጥቀስ የማይፈልግ ግለሰብ ከሰጠው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ባለፈው ሳምንት ብቻ በግድያ የሞቱት የገዥው ፓርቲ አባላት 10 መድረሱ ይነገራል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የእርቅ ውይይት ማድረግ ባለመፍቀዳቸው አገሪቱ ወደ ከፍተኛ የእርስ በርስ እልቂት እያመራች መሆኑን ብዙዎች ሲያሳስቡ ቆይተዋል።   

 

 

 

 

 

 

 

 

መጋቢት 08 ቀን 2008 ዓ.ም

Ø በዘንድ ድርቅና ረሃብ የተጎዱና ዕርዳታ ማግኘት ባለማቻላቸው ወደ አዲስ አበባ በስደት ያቀኑ ተረጅዎች አዲስ አበባ  አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸው ታውቋል። ተረጅዎቹ የመልካም ገጽታ ታበላሻላችሁ ተብሎ ከትውልድ ቀያቸው ደብረ ብርሃን ድረስ የተሰደዱና ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ሙከራ ሲያደርጉ ነው በወያኔ ፖሊስና ወታደር የተከለከሉት። ተረጅዎቹ ዜጎች ከወሎ ክፍለ ሀገር ከባቴ ከሐይቅና አቅራቢያ ካሉ ከተሞችና  ገጠሮች በድርቁና በረሃብ የተነሳ የተሰደዱ እንደነበረ ታውቋል። ቀደም ሲል ደብረብርሃን የገባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተረጅዎች በደብረ ብርሃን አውቶቡስ ተራ ግቢ ውስጥና በአካባቢው በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። የወያኔ ፖሊስ ወታደርና ካድሬ ድርቅና ረሃብን እየተቋቋመ ነው፣ ከቀየው የተሰደደም የሞተም ሰው የለም በማለት ዓለምና ሀገርን እየዋሸ ባለበት ሰዓት የድርቅና የረሃብ ተረጅዎችና ጉዳተኞቹን በነጻ እንኳን የመንቀሳቀስ መብታቸውን መንፈጋቸው የአገዛዙን ጭካኔ የሚያሳይ ነው።

Ø በመላ ኢትዮጵያ በተንቀሳቀሰው ህዝባዊ ቁጣና ተቃውሞ የተደናገጡት የወያኔ መሪዎች ከ300 በላይ ገድለው በሺህ የሚቆጠሩ ደብድበውና አስረው ተቃውሞውንና ቁጣውን አብርደናል በማለት በሚደሰኩሩበት በአሁኑ ሰዓት ሕዝባዊ ተቃውሞው አሁንም በመቀጠሉ አንዳንድ እርምጃዎች መውሰድ ጀምሯል። በተለይ በኦሮሞ አካባቢ ለነበረው አመጽ ለችግሩ መንስኤ የሆነው የመልካም አስተዳደር ጉድለት ነው በማለት ከ900 በላይ ከፍተኛ መካከለኛና ዝቅተኛ ካድሬዎችንና ኃላፊዎችን ከኃላፊነት ዝቅ በማድረግ በማባረርና በማሰር ተቃውሞን ለማብረድ እግረ መንገዱንም ለተቃውሞ ድርሻ አላቸው ያላቸውንም ማግለሉም ይታወሳል።  አሁን ደግሞ በ 2.4 ሚሊዮን ብር 800 ሺ የኦሮሞ ወጣቶችን ስራ ለማስያዝ እቅድ አውጥቻለሁ ብሏል። የኦሮሚያ ምክር ቤት የተባለው የወያኔ ታዛዥ እና አሽከር ተቋም ኃላፊዎች በዚህ ዓመት ብቻ ለ80 ሺ349 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጠር፣ ምን ምን ዓይነት ፕሮጀክት እንደሚከፈትና ምን ዓይነት ሥራ እንደሚፈጥር አብራርተዋል። በዚህ መሰረት ማኑፋክቸሪንግ ዘመናዊ እርሻና የማእድንና የግንባታ ሥራዎች ይፈጠራሉ ተብሏል። 200 ትራክተሮች 1400 የውሃ ፖምፖች 101 መሬት መቆፈሪያዎች መዘጋጀታቸውና ከሥራ ዕድሉም መካከል 60 በመቶው በምዕራብ ወለጋና በምዕራብ ሸዋ ላሉ ወጣቶች እንደሚውልና  ቀሪው ከ40 ከመቶ በሌሎች አካባቢዎች እንደሚውል ተነግሯል።

Ø 6021 ስደተኞች ካለፈው ማክሰኞ ከሚያዚያ 4 ቀን 2008 ጀምሮ አስቸጋሪውን የሜድትራኒያን የባህር ጉዞ አቁርጠው ጣልያን መድረሳቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ ም አስታቋ:: በዚህ ግዜ ውስጥ ወደ ግሪክ የተጓ ስደተኞች  174 ብቻ መሆናቸውን ጠቅሶ የአሮፓ ህብረት ከቱርክ ጋር ሰደተኞችን አስመልክቶ ያደረገው ስምምነት ስደተኞቹ በቀታ ወደ  አውሮፓ አገሮች ያመሩ ሳይገፋፏቸው ንዳልቀረ ተግምቷል::  ስደተኞቹ ለዓለም አቀፍ የስደኞች ድርጅት ንደተናገሩት ሁሉም ከሊቢያ መነሳታቸውን ገልጸው በላስቲካ ጅልባ ላይ በመሆን ጣልያን መግባታቸውና በየአንዳንዱ የላስቲክ ጀልባ ላይ 130 ስደተኞች ተጭነው አንደነበረም ተናግረዋል:: አብዛኛዎቹ ስደተኞች ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች ይሁን አንጅ ከአፍሪካ ቀንድ የመጡት ብዛት ንዳላቸውና በሻብያ ስር ካላቸው ኤርትራ የተሰደዱትን ግ ከፍተኛ  ቁጥር ንዳላቸው የስደተኞቹ ድርጅት ከሮም ቢሮ ግልጽ አደርጉዋል;; በያዝነው የፈርንጆች አመት 23 ሺ ስደተኞች ጣልያን ሲገ 153 ሺ 500 ደግሞ ግሪክ መድረሳቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኛ ድርጅት አስታውቋል:: ከስደተኛ ውስጥ ምን ያህሉ ኢትዮጵያውያን አንደሆኑ የተለሰ ነገር የለም::

Ø አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.. የደቡብ ሱዳን መንግስት ወታደሮችና ሙርሌ የተባለ ጎሳ አባላት ታጣቂዎች በአንድ ላይ በመሆን ተንቀሳቅሰው ወደኢትዮጵያ ግዛት በመግባት 10 የሚሆኑ መንደሮችን አጥቅተው 170 የኑዊር ጎሳ አባላትን የገደሉ መሆናቸውን ሱዳን ትሪቡን የተባለው ጋዜጣ በአርብ ዕለት እትሙ ዘግቦታል። ከተገደሉት ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸው ተነግሯል። የተገደሉት የኑዌር ጎሳ አባላት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በወረራው ወቅት የሚደርስላቸው ኃይል ባለመኖሩና መሳርያ አልባ በመሆናቸው ሊጠቁ ችለዋል ተብሏል። በግጭቱ ቢያንስ 51 የሚሆኑ የሙርሌ ጎሳ አባላትም የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። ከተገደሉት የሙርሌ ጎሳ አባላት መካከል ከፊሎቹ የተገደሉት ጥቃቱን ሲፈጽሙ የተወሰኑት ደግሞ ሲሸሹ ሲሆን ከአስከረኔአቸው የሙርሌ ዜጋ አባላት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል ተብሏል።

 

Ø በኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ ድገት የራሱን ከፍተኛ ድርሻና ሚና የተጫወተው የማሲንቆ ተጫዋችና ድምጻዊው ጌታ መሳይ አበበ በተወለደ 72 ዓመቱ ማረፉ ተገለጠ አርቲስ ጌታ መሳይ ከልጅነቱ አስከ ጎልምስናው የሙዚቃና የኪነት ሙያን ተቀላቅሎ የኖረ ሲሆን በአዲስ አበባ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የባህል ከል በኋላም በሀገር ፍቅር ትያትር በሙዚቀኛነት በድምጻነት አገልግሎት የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አምባሰደር በመሆንም በተለያዩ የዓለም አገሮች በመዘዋወር በማንቆ ተጫዋችነትና በድምጻነት አገልግሏል አርቲስት ጌታ መሳይ አበበ በሕይወት ዘመኑ 200 በላይ ዜማዎችን የተጫወተ ሲሆን ከአስር በላይ ትያትሮችንም በመድረክ ላይ ከውኗል በኪነት ዓለም ውስጥም በማንቆ ተጫዋችነት በድምጻነት በመህርነትና በኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ባህል በዓለም ያስተዋወቀው አርቲስ ጌታ መሳይ አበበ 966 ድምጽ ባደረበት የጭንቅላት  ህመም የተነሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ::

 

 

Ø ሀሙስ ሚያዚያ 6 ቀን በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የተመታውና ገና በማገገም ላይ የነበረው  የደቡብ ጃፓን ግዛት ነዋሪ አርብ  ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. መጠኑ 7.3 በሆኑ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመቷል። በዚህኛው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን 20 ሰዎች መሞታቸውና በመቶ የሚቆጠሩ መቁሰላቸው ተዘግቧል። በርካታ ህንጻዎች በመድርመሳቸው ከህንጻዎች ስር ብዙ ሰዎች ከእነህይወታቸው ተቀብረው ይገኛሉ የሚል ስጋት አለ።  በአካባቢው የሚገኙትን ፖሊሶችና የእርዳታ ሰጭ ሠራተኞችን ለመርዳት 20 ሺ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተልከዋል። መንገዶች የፈራረሱ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የመሬት መድርመስ የደረሰ መሆኑም ታይቷል። መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ዝናም ይዘንማል የሚል ግምት ስላለም የመሬት መደርመሱ በስፋት ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት አለ።  ከ200 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ መሆናቸውም ተነግሯል። የቅዳሜው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ሚያዚያ 6 ቀን ከደረሰው ጠንካራ ሲሆን ያጠቃቸው ክልሎችም ሰፊ እንደሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ከ2000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሆስፒታል አገልግሎት እየተሰጣቸው ሲሆን ከ92 ሺ ሰዎች በላይ ቤታቸው ለቀው በመጠለያ ካምፖች መቆየት ተገደዋል። ሰንዴ በሚባለው ቦታ ላይ የሚገኘው የኑክሊየር ቦታ የመፍረስ አደጋ ያላጋጠመው መሆኑ ተገልጿል። የቅዳሜው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ከአምስት ዓመት በፊት ከደረሰውና ሱናሚ አስነስቶ በተለይ በፉኪሽማ በሚገኘው የኑክሊየር ቦታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ የሚበልጥ መሆኑን አዋቂዎች ይናገራሉ።

 

Ø “በቤት ውስጥ ካሉ በረሮዎች ጋር የሚመሳሰሉት የቱስ ብሔርሰብ አባላት መጥፋት አለባቸው” በማለት በ 1984 ዓም ቅስቀሳ አካሄዶ ነበር የተባለው ሊዮን ሙጌሴራ የተባለው ግለሰብ ሩዋንዳ ውስጥ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት መሆኑ ታወቀ። ግለሰቡ ይህንን ቅስቀሳ ያደረገው በ1984 ዓም ሩዋንዳ ውስጥ ባለስልጣን በነበረበት ወቅት ሲሆን 1000 ለሚሆኑ የፓርቲ አባላት ባደረገው ንግግር ቱሲዎችን ገድለው ሬሳቸውን ወንዝ ውስጥ እንዲጨምሩ ቅስቀሳ አካሂዷል የሚል ተጨባጭ ማስረጃ ተገኝቶበታል ተብሏል። በሩዋንዳ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ግለሰቡ ወደካናዳ መጥቶ በኩቤክ ግዛት በአንድ ኮሌጅ ውስጥ አስተማሪ ሆኖ የቆየ ሲሆን ካናዳ ውስጥ ክስ ቀርቦበት ለ12 ዓመት ያህል ከተከራከረ በኋላ ከአራት ዓመት በፊት ወደ ሩዋንዳ የተወሰደ መሆኑ ይታወሳል።  

 

Ø አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008  በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ የፕሬዚዳንት ሲሲን አስተዳደር በመቃወም ቁጥራቸው ከ 1000 በላይ የሚሆኑ ግብጻውያን የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ሰልፉ የተጠራው ቀደም ብሎ ሁለት የግብጽ ደሴቶች ለሳኡዲ አረቢያ መሰጣቸውን ለመቃወም ቢሆንም ሰልፈኞች ያሰሙ በነበረው መፈክር ውስጥ  የሲሲ መንግስት የሚያወግዙና ሲሲ ባስቸኳይ ከስልጣን እንዲወገዱ የሚጠይቁ እንደሚገኙበት ታውቋል።  ስልፉ እስከምሽት ድረስ የቆየ ሲሆን አብዛኛው ሰልፈኛ ከሄደ በኋላ የቀሩትን ጥቂት ሰዎች ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ የተጠቀመ መሆኑ ተገልጿል። ቀደም ብሎ በሌላው የከተማው ክፍል የተደረገውን ስልፍ ለመበተን ፖሊስ እርምጃ የወሰደ ሲሆን 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውም ተዘግቧል።

 

 

 

 

 

 

መጋቢት 07 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø  በመላ ኢትዮጵያ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ አነጣጥሮ የተነሳው ስግብግብና  አልጠግብ ባይ የሆኑት መሪዎቹ የሚያካሂዱትን ዝርፊያና ቅሚያን ለመቃወም ሆኖ እያለ  የወያኔ መሪዎች ለችግሩ ሁሉ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር ነው በማለት በኦሮሞ አካባቢ የሚገኙ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ ካድሬዎችን ማባረር መጀመራቸውና አንዳንዶቹን ለማሰር መዘጋጀታቸው ታውቋል። የወያኔው የኦሮሚያ ክልል ኃላፊዎች እንደገለጹት በ 929 የስራ ኃላፊዎችና ካድሬዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገልጾ ከእነዚህም ውስጥ 829 የሚሆኑት ከፍተኛና መካከለኛ የስራ ኃላፊነት የነበራቸው መሆኑን አስረድቷል። 121 ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ የተደረገ ሲሆን 708 መካከኛና ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሥልጣናቸው የተባረሩ መሆናቸው ተገልጿል።  ገሚሶቹ በሙስና ተከሰው ወደ እስር ቤት ይወረወራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ብዙ የፖሊቲካ ታዛቢዎች ግን በኦሮሞ አካባቢ የተፈጸመው የሕዝብ በድል ስርቆትና የመ ንጥቂያ በወያ መሪዎች ፊታውራሪነት መፈጸሙ እየታወቀ የኦሮሞ ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርጎ ማባረሩ ምናልባት በሕዝባዊ ተቃውሞምና ቁጣ ወቅት ከሕዝብ ጋር የወገኑትን ለመበቀል የወሰደው እርምጃ ነው ብለው ይናገራሉ።

 

Ø  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በዓለም የሰብአዊ መብት ይዞታን አስመልክቶ የሚያወጣውን ዓመታዊ ዘገባው ይፋ አድርጓል። ሪፖርቱ በዓለም የስብአዊ መብትን በመርገጥና በማፈን በዋናነት ከጠቀሳቸው አገሮች አንዱ የወያኔ አገዛዝ ሲሆን የሲቪል ማህበራትን በማገድ በሚድያና በኢንተርኔት ላይ ቁጥጥር በማድረግና በማፈን ተቃዋሚዎችን በመግደል በማሰርና በማዋከብ ወያኔ የተጠቀሰ ሲሆን ባለፈው ዓመት አካሄድኩ ያለውን የምርጫ ድራማና ሁሉንም አሸነፍኩ ያለበትን ውጤት ዴሞክራሲያ ነበር በማለት ተችቶታል። የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በየዓመቱ የወያኔን ፀረ ዴሞክራሲያዊነትና የሰብአዊ መብት ረጋጭነት ይግለጥ እንጅ ጥርስ ያለው እርምጃ ያለመውሰዱ ይልቁንም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሳይቀሩ ወያኔን በምርጫ ስልጣን ላይ የወጣ ዴሞራሲያዊ መንግስት ነው በማለት ማወደሳቸውን የሚያስታውሱ ወገኖች ዘገባው ጉንጭ አልፋ ከመሆን አይዘልም ይላሉ። ከጥቂት ቀናት በፊት አሜሪካ ከወያ ጋር ወታደራዊ ትብብሯን ለመቀጠል ስምምነት መፈረሟንም በማስታወስ የአሜሪካው ዘገባ እና መግለጫ የሕዝብን ቁጣና ተቃውሞ ለማዘናጋት የሚደረግ  ይመስላል የሚሉ ወገኖች ሪካ ሞክራሲና ለሰባዊ መብት ከቆመች መጀመሪያ እንደ ወያኔ ባሉት አገዛዞች ላይ የፖሊቲካና የዲፕሎማሲ እርምጃ መውሰድ ነበረባት ይላሉ።

 

Ø  የእንግሊዝ መንግስት ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓም ጎቹ ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ እንግሊዛውያን በተለይም ወደ  አፋር፤ ኢትዮጵያና ሻእቢያዋ ኤርትራ ወሰን ወዳለው አካባቢ፤ በኢትዮጵያና በሱዳን ወሰን አካባቢ እንዲሁም ወደ ጋምቤላና ወደ ኦጋዴን እንዳይጓዙ ሲያስጠነቅቅ ወደ ምዕራብ ሸዋም የሚጓዙ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል። የእንግሊዙ የውጭና የኮመንዌልዝ ቢሮ ያወጣው የጉዞ ምክር መላ ኢትዮጵያን ያዳረሰና በአራቱም ማዕዘናት ያሉ ቦታዎች በሙሉ ለጉዞ ምክር የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ጠቅሷል። በየዓመቱ 20 የሚሆኑ የእንግሊዝ ዜጎች ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተጠቅሷል። 

 

 

Ø  የመጣለትን በጭብጨባና በፉጨት የሚቀበለው የወያኔ ፓርላማ በቅር የወያኔ መሪዎች የፍትህ ሚኒስቴርን አፍርሰው በጠቅላይ አቃቤ ህግ /ቤት ለመተካት ያውጡትን የህግ ረቂቅ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሚሆነውንና በምክትልነት የሚሰሩትን ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው አቅርቦ ያሾማል ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ የአቃቤ ህግ ቢሮና የወያኔው ፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ  ይሆናል መባሉና ጠቅላይ አቃቤ ህጉ በህግ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መክሮ ይስራ መባሉ በወያኔ ስርዓት ህግ አጥፍቶ የፖሊካ አሠራርን  ማስፈን የታቀደ  የወያ ሕግ ነው በማለት ብዙዎች ይተቹታል።

 

Ø  ሕዝብን ፀጥና ለጥ አድርጎ አስፈራርቶና አሸብሮ መግዛት የተለያዩ ዘዴዎችን ሲሞክር የቆየው  የወያኔው አገዛዝ የአዲስ አበባ ከተማን እንደገና ለማዋቀር በአዲስ መልክ ለማደራጀት ማቀዱን ከአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። በመረጃው መሠረት ማዘጋጃ ቤት ከዚህ በፊት ያከናውናቸው የነበሩ ተግባራት በሙሉ ወደ ወረዳ ተግባር የሚቀየሩ ሲሆን በደርግ ጊዜ ይሰራበት የነበረውና ወያኔ ያጠፋውን የቀጠና ምደባም እንደገና ሊጀምር ነው ተብሏል። ማዘጋጃ ቤት ከክዚህ ቀደም ሲያከናውናቸው የነበሩ የመሬት ጽዳት የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ የባይተዋር ቀብር ማስፈጸምና የመሳሰሉት ተግባራት ወደ ወረዳ እና ቀበሌ ዝቅ ብለው የሚሰሩ ይሆናሉ። የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ ከንቲባም ስራዎችን መከታተል ብቻ መደበኛ ስራው እንደሚሆንና የአዲስ አበባ መስተዳድር የሚለውን ስያሜ በከንቲባ ሹመት መስተዳደር ቀርቶ ወደ ርእሰ መስተዳድር ለማሳደግ መታቀዱን ምንጮች ገልጸዋል።  

 

 

Ø  ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓም በደቡብ ጃፓን ኩማማቶ ከተባለው አካባቢው በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት 9 ሰዎች መሞታቸውና 860 በላይ የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል። አብዛኞቹ ሰዎች የሞቱት ማሺኪ በምትባል ከኩማማቶ ከተማ አጠገብ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንድ የመኖሪያ አፓርትመንት በመደርመሱ ምክንያት መሆኑ ተዘግቧል። የመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ በተከተሰተበት ወቅት በአካባቢው የሚኖሩ 40 ሰዎች ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱና የአደሩ ሲሆን የመሬት መንቀጥቀጡ ርዝራዥ አሁንም እየተከሰተ ባለበት ሁኔታ ብዙዎቹ  ወደ ቤታቸው የተመለሱ መሆናቸው ተነግሯል። የአደጋ መከላከል ሰራተኞች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ከተደረመሱ ፍርስራሾች ውስጥ በህይወት ያሉ ሰዎችን የመፈለጉንና ነፍስ የማዳኑን ተግባር የቀጠሉ መሆናቸው ታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ መጠን በመጀመሪያ 6.5 ነው ተብሎ የነበረ ቢሆንም በኋላ ወደ 6.1 እንዲወርድ ተደርጓል። በኩማማቶም ሆነ በአካባቢው ባሉ ከተሞች በርካታ ከፍተኛ ርዝመት ያላቸው ህንጻዎች ያሉ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን  በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው በጣም አነስተኛ መሆናቸው የህንጻ ሥራውን ደረጃ ከፍተኛነትና ጥራት ያሳያል ተብሏል። በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች የሚሰሩት ህንጻዎች መንቀጥቀጥ ቢደርስ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ማሳሰቢያ ከአዋቂዎች ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።ንጻዎች በዝቀተኛ ደረጃ ሲምንቶና ደረጃቸውን ባልጠበቀ የህንጻ መሳሪያዎች በመሆኑ እንዲህ ዓይነት የመሬት

 

Ø  በአይቮሪ ኮስት ተይዞ በምርመራ ከሚገኝ አንድ ግለሰብ ላይ ተገኘ የተባለ ሰነድ አክራሪ እስላማውያን ጋናን ቶጎን ለማጥቃት ያቀዱ መሆናቸውን ማጋለጡ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።  ጋናና ቶጎ እስካሁን ድረስ የሽብር ጥቃት ያልተካሄደባቸው  የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ሲሆኑ  ተገኘ የተባለው ሰነድ ያጋለጠው ዜና በጋናና በቶጎ ፍርሃትና ስጋትን ያሰራጨ መሆኑ ታውቋል። የጋና ፕሬዚዳንት በህዝቡ ውስጥ የተሰራጨውን ፍርሃት ለማስወገድ በሬዲዮ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ በመገናኚያ ብዙሃን አማካይነት ለሕዝብ ሳይሰራጭ ልንቆጣጠረው ብንችል ጥሩ ነበር ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆን የጸጥታ ኃይሎች ጉዳዩን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ በመሆናቸው ሕዝቡ ፍርሃት አስወግዶ የሚሰራውን መቀጠል  አለበት ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በመቀጠልም ሽብሩ ሊካሄድ የሚችለው በአገር በቀል አሸባሪዎች አማካይነት ስለሆነ ሕዝቡ በየቦታው ነቅቶ እንዲከታተልና እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

 

 

Ø  አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ በደቡብ ሱዳን ያለፍርድ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የታሰሩ 35 ሰዎች ባስቸኳይ እንዲፈ ጠይቋል። ከታሰሩት መካከል ጋዜጠኞችና በጁባ ዩኒቨርስቲ ዲን የሆኑት ግለሰብ እንደሚገኙበት ተነግሯል። ድርጅቱ በመግለጫው ላይ ከታሰሩት መካከል ማንኛቸውም ጠበቃ እንዲቆምላቸው ያልተደረገ መሆኑን ዘርዝሮ  አብዛኞቹ በእስር ላይ እንዳሉ መደብደባቸውን ገልጿል። በደቡብ ሱዳን በመንግስት ኃይሎች በጅምላ ከታሰሩት የፖሊቲካ እስረኞች መካከል 35 ቃላይ ከታሰሩት ውስጥ ጥቂቶች መሆናቸውን ቁሞ በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎች ሁኔታ ያልታወቀ መሆኑን ገልጿል።

 

Ø  በብዙ የሚቆጠሩ የደቡብ አፍሪካ ዜጎች አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 .. በጆሃንዝበርግ ከተማ ፕሬዚዳንት ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ ትእይንተ ህዝብ ያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል። ሰላማዊ ሰልፉና ያዘጋጁት የተቃዋሚ ድርጅቶች ሲሆኑ ሰልፈኞቹ " ሙስና ይቁም" " ለለውጥ ድምጻችንን እንሰጥ የሚሉ መፈክሮችን ይዘው እንደነበር ማወቅ ተችሏል። ከጥቂት ቀናት  በፊት የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቱ ለገጠር ቤታቸው ማስፋፊያ በርካታ የመንግስት ገንዘብ መውሰዳቸው አግባብ አለመሆኑን ገልጾ ገንዘቡን እንዲመልሱ መወሰኑ ይታወሳል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዋቂ ግለሰቦችና የሃይማኖት ድርጅቶች መሪዎች ሚስተር ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ቢጠይቁም ከገዥው ፓርቲ አባላት በኩል ያላቸው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ በምክር ቤት ውስጥ እሳቸውን ከስልጣን ለማስወገድ የቀረበው ሕዝበ ውሳኔ ውድቅ መሆኑ ይታወቃል፡፤

በተመሳሳይ ዜናም ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 .. ዚምባብዌ ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲ የተደራጀና የተቀነባበረ ከፍተኛ ተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ መሆኑ ታውቋል። ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንቱ ሚስተር ሙጋቢ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ልዩ ልዩ መፈክሮችን ይዘው የነበረ ሲሆን በርካታ ሴቶችና ወጣቶች እንደነብሩበት ለማወቅ ተችሏል። ስልፉን ቀደም ብሎ የጸጥታ ኃይሎች ከልክለው የነበረ ቢሆንም ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም የዚምባብዌ ፍርድ ቤት የፖሊስ እገዳ እንዲነሳ 'እዛዝ በመስጠቱ ምክንያት ሰልፉ ሊካሄድ ችሏል። ሙጋቤ የሚመሩት የዚምባብዌ ገዥ ፓርቲ ዛሬ አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ ፕሬዚዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ ተቃዋሚዎችን የሚጠይቁትን ጥያቄ አውግዞ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ ትክክለኛው መንገድ ምርጫ ነው ብሏል። ከሶስት አመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ሚስተር ሙጋቤ በድጋሚ የተመረጡ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በወቅቱ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የምዕራብ አገሮች ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አይደለም በማለት ድምጽ ማሰማታቸው ይታወሳል። 

 

Ø  የምእራብ  ሳህራ ግዛትን አስመልክቶ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በሞሮኮ መንግስት ላይ ተገቢውን ተጽእኖ ማድረግ ካልቻ ሞሮኮ በምእራብ ሳህራ ሕዝብ ላይ የምትፈጸመው አፈናና በደል ሊፋፋም እንደሚችል የፖሊሳሪዮ ግምባር መሪ ሚስተር ሞሃመድ አብዱላዚ አስታወቁ። በሕዝብ ላይ የሚካሄድ አፈናና በደል የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ ይህን ለመቋቋም ትጥቅ ትግልን ጀምሮ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንገደዳለን በማለት ጦርነት እንደገና ሊጀመር የሚችልበትን ሁኔታ ጠቁመዋል። ማስጠንቂቂያው የተሰጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በምእራብ ሳህራ ስለሚገኘው የተመድ ተል እኮ የወደፊት እጣ እየመከረ ባለበት ወቅት ነው። ባለፈው ወር ሞሮኮ በተመድ ዋና ጸሐፊ መግለጫ በመቆጣት ከአገሩዋ ዲፕሎማቶችን ማስወጣቷ ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት 1983 ዓም የምእራብ ሳህራን ጉዳይ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ጥረቱ እስካሁን ጥረቱ ያልተሳካ መሆኑ ይታወቃል። የአገሪቱን የወደፊት እጣ ለመወሰን ውሳኔ ሕዝብ ይደረግ ቢባልም በፖሊሳርዩ ግምባርና በሞሮኮ መካከል በጉዳዩ ላይ ልዩነት በመፈጠሩ እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል። ግዛቱ የሞሮኮ ነው የሚለውን ሀሳብ ፈረንሳይና ሴኒጋል የሚደግፉት ሲሆን ሌሎች የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የሚቃወሙት መሆኑ ይታወቃል። 

 

 

 

 

መጋቢት 6 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በአየር ንብረት  መዛባትና እንዲሁም በወያኔ አስከፊ አገዛዝ ምክንያት  በኢትዮጵያ የተንሰራፋው ድርቅና ረሃብ እያየለ ሄዶ ከወር ወደ ወር፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተረጅው ቁጥር እየጨመረና የአደጋው አስጊነት ይበልጥ እየሰፋ መምጣቱን የተመድ የሰብዓዊ ዕርዳታ አገልግሎት ቢሮ አስታውቋል። እንደ ተመድ ከሆነ በኢትዮጵያ አሁን የዕርዳታ ፈላጊው ቁጥር ወደ 20 ሚሊዮን መጠጋቱና ይህ አሀዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት አንድ አምስተኛውን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጿል። በረሃብና በድርቅ የተጎዱት አካባቢዎች ከ186 ወደ 219 ክፍ ያሉ ሲሆን ተረጅዎችም በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በአንዳንድ አካባቢ ስደት መጀመሩና በዚህ ከቀጠለ የረሃብ አደጋ ዕልቂትን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመሆን በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ኢትጵያውያንና በጦርነት ለተጎዱ ሶርያውያን 2.2 ሚሊዮን ዕርዳታ እየተማጸኑ ሲሆን 480 ሚሊዮን ዶላር በድርቁና በረሃንብ ሳቢያ ጤንነታቸው ለተዛባ ኢትዮጵያውያንና በጦርነት ለተጎዳ ሶርያውያን ይውላል ተብሏል። የወያኔ ባለስልጣኖች  በወደብ የተከማቸ የእርዳታ እህል ለማንሳት ከመረባረብ ይልቅ በረሃብተኞች ህይወት ቁማር እየተጫወቱ መሆናቸው እየተጋለጠ ነው ተብሏል ።

 

Ø የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያ ደሣለኝ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሰባት ከመቶ ያድጋል ሲል አማካሪው አርከበ እቁባይ ደግም 11 ከመቶ ያድጋል ብሏል። የወያኔ የጡት አባት የሆነው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF ደግሞ የወያኔን የኢኮኖሚ እድገት ወደ 4.5 ከመቶ ያወርደዋል። የገንዝብ ድርጅቱ የወያኔ የኢኦኖሚ እድገት ያስቆለቆለው በኢትዮጵያ ባለው ድርቅና ረሃብ በዓለም አቀፉ የገበያ ዋጋ መቀነስ ነው ይበሉ እንጅ የወያኔ ኢኮኖሚ ወትሮም ቢሆን የፕሮፓጋንዳ እድገት እንጅ በተጨባጭ በሕዝብ ጥቅምና ኑሮ ላይ ያመጣው ለውጥ አለመኖሩ የተረጋገጠ ነው። ቀድሞም ቢሆን ደካማ የነበረው ኢኮኖሚ  ዛሬ  በድርቅና ረሃብ፣እንዲሁም በዓለም አቀፉ ገበያ መቀነስ ምክንያት ቀንሷል ተብሏል። ወያኔ በፕሮፓጋንዳ በሚያስፋፋው ዕድገት ስም ከ17 ቢሊዮን ዶላር በላይ በአገሪቱ ስም መበደሩና የአገሪቱ ኢኮኖሚ ሊሸከምው የማይችል ብድር መውሰዱ የኢኮኖሚው ባዶነት የሚያሳይ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

 

Ø ላለፉት ሶስት ዓመታት በወያኔ ፖሊሶች በግፍ ተይዞ በፈጠራ ወንጀል ተከሶ ወደ ወያኔው ፍርድ ቤት ይመላለስ የነበረው የሙስሊሞች ጉዳይ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዲሬክተር ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም.ከእስር መፈታቱ ታውቋል። ጋዜጠኛ ስለሞን ከበደ ለጋዜጠኛነት ሙያው ታማኝ በመሆኑና የጋዜጠኛነት ምግባሩን በተግባር በማሳየቱ በወያኔ ካድሬዎች ጥርስ ተነክሶበት ቆይቶ እንደነበርና ከሶስት ዓመት በፊት በፈጠራ ወንጀል ታስሮ ሰቆቃ ሲካሄድበት መቆየቱ ይታወሳል።  ልዮ ልዮ የጋዘጠኛ መብት አስከባሪና ተከራካሪ ድርጅቶች  ጋዜጠኛው በነጻ እንዲፈታ ሲወተውቱና ሲጠይቁ እንደነብረ ይታወቃል። የወያኔው የፖሊቲካ ፍርድ ቤት ጋዘጠኛ ሰለሞን ከበደን ሊያስቀጣውና ሊያሳስረው የሚችል ምንም ጥፋት ባለማግኘቱና ተጽእኖውና ግፊቱ ስለበረታ ከእስር ለመፈታት ተገደዱ እንጅ ዛሬም በወያኔ ወህኒ ቤት ውስጥ የጋዘጠኛነት ሙያቸውን በማክበራቸውና ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብቻ በእስር የሚማቅቁ ጋዜጠኞች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን በግፍ ለታሰሩ ጋዜጠኞችና ዜጎች ሁሉ ድምጽ ማሰማት የማይታለፍ የአገር ወዳድ ዜጋ ግዴታ ነው ነው የሚሉ በርካታ ናቸው።

 

Ø ከሚያዚያ 8 እስከ ሚያዚያ 9 2008 ዓም. ድረስ በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደውን አምስተኛ የጣና ፎረም ስብሰባን ምክንያት በማድረገ የባህር ዳር ከተማ በከፍተኛ ወታደራዊና የደህንነት ጥበቃ ስር መውደቋ ታውቋል። የወያኔ ደህንነት አባላት በባህር ዳር ከተማ በሚገኙ የእንግዳ መቀበያና የመኝታ አገልግሎት መስጭያ ቤቶች እየዞሩ ማናቸውንም ፀጉረ ልውጥ ሰው አገልግሎት በፈለገ ጊዜ አስፈላጊውን መረጃ መያዝ ግዴታቸው እንደሆነና ለወያኔ ፖሊስም ማሳወቅ እንዳለባቸው ትዕዛዝ መስጠታቸው ታውቋል። በዚህ የጣና ፎረም ጉባዔ ላይ በሥልጣን ላይ ያሉ አምባገነን የአፍሪካ መሪዎችና ከስልጣን የወረዱ ፕሬዚዳንቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለባህርዳር ደህንነት ጥበቃ የወያኔ ቡድን መሪዎች ዘርን የተንተራሰ ምርጫ ማካሄዳቸውና ጠቅም ያለ አበል የሚከፈልበት በመሆኑ የትግራይ ተወላጆችን ማሰማራታቸው ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

 

 

Ø ዛሬ ሐሙስ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓ.ም በጃፓን ኩማሞቶ በሚባለው አካባቢ መጠኑ 6.4 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ የደረሰ መሆኑን የጃፓን የሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት ገልጿል። የመሬት መንቀጥቀጡ ያደረሰው ጉዳት እስካሁን ባይገልጸም የሱናሚ ስጋት እንደሌለ ተገልጿል። ባለፈው እሁድ በደቡብ እስያ መጠኑ 6.6 የሚደረስ የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሶ በህንድ በፓኪስታን እና በአፍጋኒስታን ህንጻዎችን መጉዳቱና  በተወሰኑ ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት ማድረሱ የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን መጠኑ 6.9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሰሜን ሚያንማር (በርማ) የደረሰ መሆኑ ተዘግቧል።   

 

Ø በሰሜን ናይጄሪያ ቺቦክ ከተባለችው ከተማ 276 የሚሆኑ በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ልጃገረዶች ቦኮ ሃራም በተባለው አሸባሪ ቡድን ተጠልፈው ከተወሰዱ ሁለት ዓመት ሆናቸው ተባለ። ባለፈው ታኅሳስ ወር በተደራዳሪዎች አማካይነት ከቦኮ ሃራም ተገኘ ከሚባለውና የሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ካሳየው የቪዲዮ ቅጅ በርከት ያሉት ልጃገረዶች በህይወት መኖራቸው ታውቋል። ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም ሲ ኤን ኤን ያሳየው ቪዲዮ ተቀረጸ የተባለው ታኅሳስ 15   ቀን 2008 ዓ.ም. በፈረጆቹ የገና በዓል ዕለት ሲሆን ከተጠለፉት ልጃገረዶች መካከል 15 ቱ በቪዲዮ ላይ ታይተዋል። ቪዲዮን የተመለከቱት አንዳንድ እናቶችና በዚያን ወቅት ያመለጡና ጓደኞቻችው የተመሰቃቀለ ስሜት ያደረባቸው መሆኑንና  በአንድ በኩል ልጆቹ በህይወት መኖራቸው ሲያስደስታቸው በሌላ በኩል ያሉበት ሁኔታ በጣም እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። ቦኮ ሃራም የተባለው አሸባሪ ድርጅት ለዓመታት ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ የቆየ ቢሆንም ልጃገረዶችን በጅምላ ጠልፎ ሲወስድ በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት የደረሰበት  መሆኑ ይታወሳል፡፤ በወቅቱ የነበረው የናይጄሪው የሚስተር ጉድላክ ጆናታን መንግስት በመጀመሪያ ልጃገረዶቹ መጠለፋቸውን ቢክድም በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ግፊት ለመቀበል ተገዷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ልጆቹን ለማስፈታት  በድርድርም ሆነ በሌላ መልክ ጥረት ቢደረግም እስካሁን የተገኘ መፍትሄ እንደሌለ ታውቋል።  ባለፈው ሳምንት የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቦኮ ሃራም ከሚቆጣጠራቸው ቦታዎች 11698 ሰላማዊ ሰዎችን ነጻ ማውጣቱን ቢገልጽም ነጻ ወጡ የተባሉት ሰዎች ከቺቦክ የተያዙ ልጃገረዶችን አያካትቱም። ላለፉት ሁለት ዓመታት በቺቦክና በአካባቢው ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ምክንያት ከ20 ሺ በላይ ህጻናት የትምህርት ዕድል ተነፍገው ይገኛሉ።

 

Ø በብሩንዲ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው የሚወሰዱ ሰዎች መዳረሻቸው የሚጠፋ መሆኑ ተነገረ። የመንግስቱ ተጻራሪ ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተወሰደው ከታሰሩ የሚጠብቃቸው በእስር ቤት በምርመራ መሰቃየትና ሞት ብቻ መሆኑን በርካታ ሰዎች እየተናገሩ ይገኛሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቤታቸው፤ከስራ ቦታቸው እና ከሌሎች ቦታዎች በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው የሚወሰዱና መዳረሻቸው የሚጠፋ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውና ወገኖቻቸው ያሉበትን ለማወቅ በርካታ ገንዘብ በጉቦ መልክ እንዲከፍሉ እየተደረገ መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች እየተናገሩ ይገኛሉ። አይ ብሩንዲ የተባለ በህቡዕ የተቋቋመ የኢንተርኔት ቡድን በጸጥታ ኃይሎች ተጠልፈው መዳረሻቸው የጠፉትን ሰዎች ስም እያሰበሰበ ሲሆን እስካሁን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውና የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት የሚከፈለው ጉቦ  ከ250 ዶላር እስከ 2500 ዶላር መድረሱን ገልጾ ጉዳዩን ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ እያጋለጠ እንደሆነ አስታውቋል።  የብሩንዲ መንግስት አፈናውን ይካድ እንጅ ጸጥታውን ለማረጋጋት ማናቸውንም ዓይነት እርምጃ እንዲወስዱ ለጸጥታ ኃይሎች መመሪያ መስጠቱ ይታወቃል። በቅርቡ በዋናው ከተማ በቡጁምቡራ  ሙሳጋና ያካቢጋ በተባሉ ቀበሌዎች መሳሪያ ለማስፈታት የጸጥታ ኃይሎች የሚያካሄዱትን አሰሳ ለማምለጥ የመንደሮቹ ነዋሪዎች አብዛኞቹ ቤት ንብረታቸውን ጥለው በመሰዳዳቸው የተሰደዱትን ዜጎች ቁጥር ከ250 ሺ በላይ ያደረሰው መሆኑ ተገልጿል።

 

 

Ø ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2008 ዓም. ከፍተኛ የአውሮፓ ህብረት ቡድን ሊቢያ መግባቱና ከሊቢያ አንድነት መንግስት አባሎች ጋር መነጋገሩ ተገልጿል። የፈረንሳይ አምባሰደር እንዲሁም የእንግሊዝ እና የስፔን ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሊቢያ ወደብ በባህር ኃይል የጦር ሰፈር ውስጥ ከአንድነቱ መንግስት ባለስልጣኖች ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን የአውሮፓው ህብረት የሊቢያን የአንድነት መንግስት ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 4 ቀን የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተመሳሳይ ጉብኝት አድርገው እርዳታና ትብብር ለማድረግ ቃል መግባታቸውና ባጭር ጊዜ ውስጥ ጣሊያን ኤምባሲዋን በትሪፖሊ ልትከፍት  እንደምትችል መናገራቸው ተገልጿል። ከጥቂት ቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ የሊቢያ የአንድነት መንግስት አካል ትሪፖሊ ገብቶ በወደቡ አካባቢ ከባህር ኃይል ጦር ሰፈር ውስጥ ስራዎችን እያካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከአንዳንድ ወገኖች ድጋፍ ቢሰጠውም በትሪፖሊ የሚገኘው ራሱን መንግስት ነኝ የሚለው ክፍልና እንዲሁም በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘውና የዓለም አቀፍ እውቅናና አግኝቶ የነበረው ምክር ቤት አብዛኞቹ የአንድነት መንግስቱን እየተቃወሙ መሆናቸው   ይታወቃል።

 

 

 

 

 

ሚያዚያ 05 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø የወያኔ አገዛዝ ለስልጣኑ ተቀናቃኝ ይሆናሉ የሚሰጋባቸውን ጉዳዮች  ሁሉ መቆጣጠርና እና መከታተል ሥራዬ ብሎ ከያዘ ወዲህ ሰሞኑን ደግሞ የኮምፒውተር ወንጀል ቅጣት  በአዋጅ መልክ ህግ ሆኖ እንዲወጣ  ጉዳዩን ለፓርላማ አቅርቧል። የመጣለትን ሁሉ በጭብጨባ ብቻ የሚቀበለው  የወያኔ ፓርላማም ረቂቅ ህጉን ይቀበላዋል ተብሎ ይጠበቃል። የወያኔ መሪዎች የኮምፒወተር ረቂቅ ህግን ለማውጣት የተገደዱበት ምክንያት ተቃውሞና አመጽ ያቀዱ መልእክቶች ያለ ተጠያቂነት በብዛት ሲሰራጩ በመቆየታቸው ነው ተብሏል። በተጨማሪም በኮምፒውተር ደረጃ ወንጀል እየበረከተ መምጣቱም ለረቂቅ አዋጁ መውጣት ሌላው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል። የወያኔው ረቂቅ አዋጅ የአገዛዙን ተቋማት በተለይም ወታደራዊ መረጃዎችን የሚገኙባችው የኮምፒውተር ፋይሎች እንዳይጠፉና እንዳይሰረቁ ልዩ ትኩረት ያደርጋል የተባለ ሲሆን ወያኔን ከስልጣን ለማባረር ይንቀስቃሳሉ የሚባሉ ቡድኖችና ግለስቦችን ለመቆጣጠርም ታስቦ ነው። በዚህ የኮምፒውተር ወንጀል የተከሰሰ ሰው ከ 15 እስከ 25 ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚጠብቀው ረቂቅ ህጉ ይደነግጋል።

Ø በደቡብ ኢትዮጵያ በሻሸመኔ ከተማ ቀድሞ መጸዳጃ ቤት የነበረ ቦታ ላይ የአምልኮት መፈጸሚያ አዳራሽ ተሰርቶ አዳራሹ በመደርመሱ አስር ሰዎች መሞታቸው ታወቀ። ይህ በአሌሉ ክፍለ ከተማ ቀበሌ አስር ውስጥ ያለው መጻዳጃ ቤት መቼ እንደተቆፈረና መቼ እንደተዘጋ ባይታወቅም ህያው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የሚባል የአምልኮ ማካሄጃ ቤት ከአንድ ዓመት በፊት መገንባቱ ታውቋል፡፤ አዳራሹ በሚደረመስበት ሰዓት አስራ ስምንት ሰዎች አምልኮ ይፈጽሙ የነበሩ ሲሆን በሕዝብና በነዋሪው ትብብር ስምንት ሰዎችን ሰባት ሜትር ጥልቀት ካለው ጉድጓ ሊያወጧቸው ተችሏል። አደጋው ሰኞ ሚያዚያ 3 ቀን 2008 ዓም መድረሱ ሲታወቅ በህይወት የተረፉትን ሰዎች ለማውጣት ለሳብት ሰዓታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉ ታውቋል።

Ø አሜሪካና ወያኔ በሱማሊያ ጉዳይ ላይ ያተኮረ አንድ የትብብር ስምምነት መፈራርማቸውን የአሜሪካ መንግስት ባለሥልጣኖች  አስታውቀዋል። ስምምነቱ በጸጥታና በመከላከያ ዙሪያ ሲሆን በአሜሪካ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት በአሜሪካ ጦር ኃይል የአፍሪካ ኮማንድ አዛዥ ጄኔራል ዴቪድ ሮድሪዚግ ሲሆኑ በወያኔ በኩል የወያኔው ኤታ ማጆር ሹም የተባለው የጦር አለቃ ሳሙራ ዩኒስና የወያኔ መከላከያ ሚኒስትር ተብዬ ስራጅ ፈርጌሳ ናቸው። እአአ በ2007 ዓ.ም. በአሜሪካ ቡራኬ ወያኔ  ሱማሊያ ውስጥ ወረራ ማካሄዱ ይታወሳል።  አልሸባብን ለመዋጋት በሚል አሜሪካ ለወያኔ ጋር ከፍተኛ ወታደራዊ ትብብር ስትሰጥ መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን   ድሮን ለተባለው አብራሪ አልባ መንኮራኩሮች ማረፊያና የጦር ስፈር በገሙጎፋ አርባ ምንጭ ከወያኔ ተችራ እንደነበርም ይታወቃል። አሜሪካ የጦር ሠፈሯን ከአርባ ምንጭ ነቅላ ከወጣች ወዲህ ከወያኔ ጋር አዲስ ወታድራዊና የጸጥታ ስምምነት ስትፈርም ይህ የመጀመሪው ነው።

Ø በደቡብ ሱዳን ሁለት የእርዳታ ሰጭ ድርጅት ሠራተኞች በታጣቂ ኃይሎች የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። ዳኒሽ ዲማይኒንግ ግሩፕ (Dannish Demining Group) ለሚባለው የቦምብ አምካኝ የሰብአዊ መብት ድርጅት ይሰሩ የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች የደቡብ ሱዳን ዜጎች ሲሆኑ ወደስራ ከሚሄዱበት መኪና በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተገድደው በጥይት ተመተው የተገደሉ መሆናቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል።  እስካሁን ድረስ በደቡብ ሱዳን በታጣቂዎች የተገደሉ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች አባላት 51 የደረሰ ሲሆን ግጭቱ እስከቀጠለ ድረስ ቁጥሩ ሊቀጥል እንደሚችል ተገምቷል፡፡

Ø በተያያዘ ዜና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ኃይል ምክትል መሪ ሚስተር አልፍሬድ ላዱ ጎሬ በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የገቡ መሆናቸው ተነግሯል። በተደረገው ስምምነት መሰረት የጸጥታውን ሁኔታ የሚያስከብር 1300 የሚሆኑ የአማጽያኑ ኃይል ወታደሮችና የጸጥታ ኃይሎች ቀደም ብለው ጁባ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን ዋና መሪ ሚስተር ሪክ ማቻርም በሚቀጥለው ሰኞ ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክትል መሪው ጁባ መግባት በእርግጥም በአገሪቱ ላይ ሰላም እየሰፈነ ነው የሚለውን ግምት ከፍ አድርጎታል ተብሏል። ሚስተር ጎሬ ጁባ ሲገቡ በተናገሩት ቃል ከእንግዲህ ሰላም አይቀለበስም የሚል መልእክት ያስተላለፉ  ሲሆን 16 የአማጽያኑ ኃይል አባላት በመንግስት ኃይሎች መታሰራቸውንና ተደብድበው መለቀቃቸውን አውግዘዋል።

ከዚህ ሌላ አንድ የአፍሪካ ህብረት የመልክተኛ ቡድን በደቡብ ሱዳን የአንድነቱን የሽግግር መንግስት ለማጠናከር ጁባ የገባ መሆኑ ተገልጿል።

 

Ø በማሊ የታጠቁ ኃይሎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አሁንም ያልተዳከመ መሆኑ ተነግሯል። በቅርቡ በመንገድ ላይ በተቀበረ የፈንጅ አደጋ ሶስት የፈረንሳይ ሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት የተገደሉ መሆናቸው የፈረንሳይ መንግስት ቃል አቀባይ ገልጿል፡፡ ሶስቱ ወታደሮች የተገደሉት በሰሜን ማሊ ሽብረተኞች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወታድሮችን የጫኑ 60 ተሽከርካሪ ካሚዮኖች የሚገኙበት ኮንቮይ በሰሜን ማሊ ሲንቀሳቀስ ሟቾቹ የነበሩበት መኪና በፈንጅው በተመታበት  ጊዜ ሲሆን  ሌሎች ወታደሮችም የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ተነግሯል። ፈረንሳይ 3500 ወታደሮች በሰላም አስከባሪ ኃይል ስር በአምስት የምዕራብ አፍሪካ አገሮች   ያሰማራች ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማሊ ውስጥ የተገደሉት የፈረንሳይ ወታደሮች ከአሁኑቹ ጋር ወደ ሰባት መድረሱ ተገልጿል።  

 

Ø ሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በደቡብ ሱማሊያ ኪስማዮ በተባለው የወደብ ከተማ አሜሪካ በሰው አልባ መንኮራኩር አማካይነት ባካሄዳችው የአየር ጥቃት 12 የአልሸባብ አባላት መግደሏን ገልጻለች። የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋም የፔንታጎን ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ የተገደሉት የአልሸባብ አባላት በአሜሪካ እና በሱማሌ መንግስት ወታደሮች ላይ አደጋ ለማድረስ ሲያቅዱ የነበሩ ናቸው ብሏል።  በከተማዋ የሚኖሩ የአይን እማኞች በሰው አልባው መንኮራኩር ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው ከተገደሉት መካከል አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው ብለዋል።

 

Ø ባለፈው ታህሣስ ወር በሰሜን ናይጀሪያ 347 የሚሆኑ የሺያ ሙስሊም እምነት ተክታዮች በናይጄሪያ ወታደራዊ ኃይል አባላት በግፍ ከተገደሉ በኋላ በጅምላ መቃብር ውስጥ ተቀብረዋል በማለት አንድ የቀድሞ የአካቢው ባለስልጣን ለመርማሪ ቡድን የሰጡትን ቃል ተከትሎ ሰዎቹ ተቀብረውበታል የተባለው ቦታ ታጥሮ በጥበቃ ስር እንዲቆይና ምርመራ እንዲካሄድበት  የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በመግለጫው ውስጥ በሰሜን ናይጄሪያ ውስጥ የሚገኘው የካዱኑ ግዛት የመንግስት ኃላፊዎች ሚስጥሩን ማውጣቸውን አድንቆ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ለማምጣት እና የሚገባቸውን ቅጣት ለመበየን ገለልተኛ በሆነ ኃይል ጉዳዩ መመርመር አለበት ብሏል። በተያዙበት ጊዜ በደረሰባቸው ድብደባ እና እንግልት አይናችው ጠፍቷል የሚባሉት የእምነቱ ተከታዮች  መሪም ባስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።

 

 

ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም.

Ø የእድገትና የልማት ከበሮ በሚደበድባት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጣራ ደርሷል እየተባለ የሚለፈፍላት ኢትዮጵያ በመረጃ ልማት ሰንጠረዥ የመጨረሻ ሶስተኛ ቦታ ላይ እንደምትገኝ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ግልጽ አድርጓል። የኢንፎርሜሽን ዲቨሎፕመንት ኢንዴክክ ባለፈው ዓመት በ1967 የዓለም አገሮች ያደረገውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ጥናቱ በየአየገሮቹ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ስፋትና ጥራት የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭትና ኔትወርክ የማግኘት አቅም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛትን ለኢንተርኔት የደረሱ ዜጎች ቁጥርን ግምት   ውስጥ ያስገባ እንደነረ ሲታወቅ በውጤቱ በሰንስጠረዥ መጨርሻ 167 ኛ ያወጣቸው ቻድ ስትሆን 166ኛ የሻዕቢያዋ ኤርትራ 165 ኛ ደግሞ ወያኔ በዘረኛንት የሚገዛት ኢትዮጵያ ሆናለች በጥናቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጆ ለዜጎቻቸው በአስተማማኝ መንገድ ብቻ ሳይሆን በጥራት በማቅረብ ኮሪያ ቀዳም ስትሆን ዴንማርክና አይስላንድ አንደ ቅደም ተከተላችው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። በጥፋቱ ሰንጠረዥ ትናንት ነጻነት አገኘሁ ያለችው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ በልጣና ተሽላ መገኘቷዘረኛዎቹ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሸርቡን ደባ ሸርና በግልጽ አሳይቷል

 

Ø በተያያዘ ዜና የወያኔ ቡድን ባለስልጣኖች በከፊል ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ በደቡብ አካባቢ  ለሚገኘው ተጠቃሚ የትዊተር የዋትስ አብፕ ና የሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ዘግቶ የነበረ መሆኑ ብሉመርግ የተባለ የዜና ወኪል አጋልጧል። የወያኔ አገልጋይ የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒከሽን መስሪያ ቤት የአገሪቷን የኢንተርኔት አገልግሎት በሞኖፖል የያዘ ሲሆን ተቀጣጥሎ ከተያያዘው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የኢንተርኔት አገግልጎትን በተለይም የሞባይል አገልግሎት ለመግዛት ማቀደቀዱ ቀደም ብሎ የተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔ ባለስልጣኖች የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆን ነው እንጅ ሆን ተብሎ የተወሰደ የመንግስት እርምጃ አይደለም ብለው በማለት መግለጫ ለመስጠት ቢሞክሩም አፈናው እንቅስቃሴውን ለማዳከም የተጠቀሙበት እርምጃ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑና ብሶት የገፋፋው የሕዝብ አመጽ በማናቸውም ዓይነት አፈና ሊዳከም እንደማይችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

 

Ø የወያኔ አገዛዝ ትውልድ ገዳይ የሆነ የትምህርት ፖሊስ ቀርጾ አንድ ዘርን ብቻ በዕውቀትና በሞራል ኮትኩቶ በማሳደግ ሌላውን ኢትዮጵያ ከንቱና ገልቱ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ ሱስና በጎጂ ባህል የታሰረ በማድረግ ተተኪ ትውልድ ለማሳጣት ጠንከሮ እየሰራ መሆኑ ታውቋል። በትግራይ ውስጥ በትምህርት ቤት አካባቢ መጠጥ መሸጥ ጫት መነገድ በት/ቤት ግቢ ስጋራ ማጤስ የከለከለው የወያኔ የትምህርት ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቱ ግቢ አጥር ተጠግቶ ወይም ተሸንቆ በተሰራ የንግድ ቤት አልኮል መጠጥና ሲጋራ እንዲሸጥ ማድረግ ይፈቅዳል። ለትምህርት ቤቱ ልዩ ገቢ ያስገኛል ተብለው የተከፈቱት የንግድ ሱቆች ከልዩ ልዩ ገቢ ጀምሮ የአልኮል መጠጦችን የሚሸጡ ሲሆን ተማሪዎችና መምህራን በእረፍት ጊዜያቸው ወደ ሱቆቹ ጎራ ማለታቸው እየተዘወተረና በትምህርት ሰዓትም መጠጥ የሚጠጡና ሲጋራ የሚያጨሱ መበርከታቸው ታውቋል። በአዲስ አባባ በደጃጅ ገነሜ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይህ ሁኔታ በግልጽ የሚታይ ሲሆን ወላጆችችና ኅብረተሰብ አንድ ካላሉ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ገበታ መሆናቸው ቀርቶ የሱስ መሸመቻ ይሆናል በማለት የሚያስጠነቅቁ ዜጎች ብዙ ናቸው።

 

Ø በወያኔ ጦር ውስጥ በሚካሄዱት ስብሰባና ግምገማ  ላይ ሕዝባዊና  አገራዊ ጥያቄ ያነሱ ወይንም ሃሳባቸውን በነጻነት የገለጹትን ማስርና ደብዛ ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሲሆን ሰሙኑንም በምስራቅ ዕዝ ውስጥ የተካሄደውን ስብሰባና ግምገማ ተከትሎ ቁጥራቸው ሃያ ሰባት የሚደርስ የበታች መኮንኖችና ወታደሮች ተይዘው መታስራቸው ታውቋል። ወታደሮቹና የበታች መኮንኖቹ የታሰሩት ጦሩን ልታሳምጹ ነው በማለት ሲሆን በወታደር ፖሊስ ተይዘው ለቀናት በሐረር ጦር አካዳሚ ከታስሩ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በድሬደዋ አየር ኃይል ግቢ ውስጥ ታስረው ድብደባና ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታውቋል። የወታደሮቹና የበታች መኮንኖች እስር አሁንም ድረስ ለምስራቅ ዕዝ ጦር አባላት ሚስጥር ተደርጎ መቀመጡ ታውቋል። ወታደራዊ ተመልካቾች የወያኔ መሪዎች ለሥልጣን ማራዘሚያና ለህልውናቸው በየጦሩ ውስጥ የራሳቸውን ዘርና ፓርቲ አባላትን  በአዛዥነት በመሾም ጦሩን ለመቆጣጠር መቻላቸውን በመግለጽ የወያኔ መሪዎች ያስሯቸውን የሕዝብና የሀገር ልጆች ለማስፋፋት የወያኔ የጦር አለቆችን ማገትና መያዝ ከአዛዥነት ማባረርና ለፍርድ ማቅረብ ሊታሰብበትና የሚገባ እርምጃ ነው ይላሉ።

 

Ø ቦኮ ሃራም የተባለው አሸባሪ ቡድን  በአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቅማባቸው ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ። በአሁኑ ወቅት  በአጥፍቶ ጠፊነት ቦምብ ከሚያፈነዱ ሰዎች መካከል ከአምስት አንድ የሚሆኑት አዕምሯቸው በአደንዛዥ ዕጽ የተበከለ ህጻናት መሆናቸው ታውቋል።  የዛሬ ሁለት ዓመት ቦኮ ሃራም በአጥፍቶ ጠፊነት ራሳቸውን እንዲገድሉ ያደረጋቸው ህጻናት 11 ሲሆኑ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ 44 ህጻናትን ቦምብ በማፈንዳት ተጠቅሞባቸዋል። አደንዛዥ ዕጽን በመጠቀም ህጻናትን በዚህ ተግባር ላይ ማሰማራቱ ቡድኑ መዳከሙን ያሳያል የሚሉ ወገኖች ከካሜሩን ከቻድ ካናይጄሪያና ከናይጀር ጠልፎ የወሰዳቸውን ወደ 1.3 ሚሊዮን  የሚደርሱ ሕጻናት በመጠቀም ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

 

Ø ሰኞ ሚያዚያ 03 ቀን 2008 ዓም. ሩዪጊ በሚባለው የብሩንዲ ምስራቃዊ ግዛት  ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በገበያ ቦታ ላይ በተኩሱት የእሩምታ ተኩስ ቢያንስ አምስት ሰዎችን የገድሉ መሆናቸውና ሌሎች ሰባት ሰዎች የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። የእሩምታውን ተኩስ በመተኮስ ጉ በዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱት ታጣቂዎች ቁጥር ሶስት ሲሆን ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ ሳያዙ ያመለጡ መሆናቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል። በብሩንዲ የፖሊቲካ ውጥረት ከተፈጠረ ጀምሮ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን ከ250 ሺ ሰዎች በላይ መሰደዳቸው ይታወቃል። 

 

Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን ቡድን ቃል አቀባይ ሰኞ ሚያዚያ 3 ቀን በሰጠው መግለጫ የደቡብ ሱዳን መንግስት የጸጥታ ኃይሎች 16 የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን አማጽያን አባላትን አስረው ደብድባ ፈጽመውባችዋል ብሎ ከሷል። የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ በሚቀጥለው ሚያዚያ 10 ቀን በዋናዋ ከተማ ጁባ ይገባሉ እየተባለ በሚጠበቅበት  ጊዜና የጸጥታውንም ሁኔታ ለመጠበቅ የተወሰኑ የአማጽያኑ ወታደሮች ጁባ በገቡበት ሁኔታ በሰዎቹ ላይ የተፈጸመው እስርና ድብደባ የሰላሙን ሁኔታ ሊያበላሽ ይችላል የሚል ፍርሃት ፈጥሯል። በተጨማሪም ባህር ዔል ገዛል በተባለው ሰሜናዊ ግዛት የመንግስት ኃይሎች በአማጽያኑ ላይ ያካሄዱትን  አዲስ ወታደራዊ ጥቃት በማውገዘ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሚያዚያ 10 ቀን መግለጫ ሰጥቷል።  መስሪያ ቤቱ የደቡብ ሱዳን ኃይሎች ያከሄዱት ጥቃት የተኩስ አቁሙን ስምምነት የሚጥስ መሆኑን ገልጾ የተጀመረውን የሰላም ሂደት ያደፈርሳል ብሏል።

 

Ø የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ጀንቲሎኒ  ለሊቢያ የአንድነት መንግስት የፖሊቲካና የዲፕሎማሲያዊ እርዳታ ለማድረግ ማክሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓም ትሪፖሊ መግባታቸው ተነገረ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግፊትና አስተባባሪነት የተቋቋመው የአንድነት መንግስት በባህር በኩል ትሪፖሊ ከተማ ከገባ ጀምሮ አንድ የአውሮፓ ባለስልጣን በሊቢያ ጉብኝት ሲያደርግ ጀንቲሎኒ የመጀመሪያ መሆናቸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአንድነት መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚስተር ፋየዝ ሴራጅ ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ አገሮች አዲሱን መንግስት ለመርዳት እና ለማጠናከር ሙሉ በሙሉ የቆረጡ መሆናቸውን ገልጸው ከእሳችው በኋላ በርካታ ባለስልጣኖች ወደሊቢያ በመምጣት የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዋናው ቁልፉ አይሲስ እንዳይጠናከርና እንዲወገድ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ በርካታ የአውሮፓ አገሮች ኢምባሲዎቻቸውን በትሪፖሊ ሊከፍቱ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

 

 

 

 

ሚያዚያ 03 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø የደቡን ሱዳን አማጽያን መሪ ሪክ ማቻር ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ዋናዋ ከተማ ጁባ ይገባሉ ተብሎ ቀደም ብሎ የተነገረ ሲሆን ቀደም ብሎ በተደረገው ስምምነት መሰረት የምክትል ፕሬዚዳንቱና የሌሎች ባለስልጣናትን ደህንነት ለመጠበቅ 1370 የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን አማጽያን ወታደሮችና የፖሊስ አባላት ጁባ ከተማ የገቡ መሆናቸው ተዘግቧል። ወታደሮቹ ወደ ከተማ የገቡት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አውሮፕላን ሲሆን የተመደበላቸውን ቦታ ይዘዋል ተብሏል። በአማጽያኑና በደቡብ ሱዳን መንግስት መካከል ባለፈው ዓመት የተደረገው ስምምነት ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጣ አነስተኛ የወታደርና የፖሊስ ኃይል ብቻ በከተማዋ እንዲኖር የሚወስን ሲሆን ይህኛው የመጀመሪያው ዙር መሆኑ ታውቋል።  የደቡብ ሱዳን አማጽያን ቡድን ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ የደቡብ ሱዳን መንግስት ጁባ ውስጥ የሚገኙትን ወታደሮችና ፖሊሶች በስምምነት መሰረት ያልቀነሰ መሆኑን ገልጾ እንዲያውም የወታደሩ ቁጥር ከነበረብት ጨምሯ የሚል ክስ አሰምቷል።

 

Ø እሁድ ሚያዚያ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በቻድ በኮሞሮ ደሴቶችና እና በሱዳን ዳርፉር ግዛት ምርጫዎች ተካሄደዋል። በቻድ በተካሄደው ምርጫ ከሃያ ስድስት ዓመት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ የወጡት ኢድሪስ ዴቢ እና ሌሎች 12 ግለሰቦችም ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።   በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የማጭበረበር ተግባሮች በየቦታው ተከስተዋል፤ ወታድሮች መራጩ ሕዝብ ድምጹን ለፕሬዚዳንቱ እንዲሰጥ አስገድደድዋል፣ በአንዳንድ ቦታም ድምጾች በገንዘብ ተገዝተዋል የሚሉ ክሶች መንግስቱን ከሚቃውሙ ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል።   የመራጩ ብዛት ከፍተኛ መሆኑ የታየ ሲሆን ታዛቢዎች  ፕሬዚዳንቱ ያሸናፋሉ የሚል  ግምት ሰጥተዋል። ከአስራ ሶስት አመታት በፊት በሀገሪቱ ውስጥ የነዳጅ ምርት ተገኘ ቢባልም  ከአገሪቱ ሕዝብ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ከድህነት እርከን በታች እንደሚኖር ተዘግቧል። ከ10 የቻድ ዜጎች መካከል 7 ቱ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ማሃይማን መሆናቸውም የተመድ ምንጮች ይገልጻሉ። በመንግስት ላይ ያለው ተቃውሞ ከፍተኛ ሲሆን የጽጥታ ኃይሎችም ከፍተኛ አፈና ግድያ በሰፊው እንደሚያካሄዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ አቅርብዋል።

 

 

በኮሞሮ የአሁኑኑ ፕሬዚዳንት ለመተካት የሁለተኛ ምርጫ ሚያዚያ 2 ቀን ተካሄዷል። ምርጫው የተካሄደው በመጀመሪያ ዙር ምርጫ ከፍተኛ ድምጽ ባመጡት በሶስት ተወዳዳሪዎች መካከል ሲሆን ውጤቱ ከረቡዕ በፊት አይታወቅም ተብሏል። በጥር ወር በተካሄደው በመጀመሪያ ዙር ምርጫ 19 ተወዳዳሪዎች ምርጫው ማጭበርበርና ማታለል የበዛበት ነው በማለት መክሰሳችው ይታወሳል።

ለረጅም ጊዜ የእርስ በርስ ጦርነት ሲካሄድበት በቆየው በሱዳን የዳርፉር ግዛትም ለሶስት ቀናት የሚቆየው የውሳኔ ሕዝብ ምርጫ እሁድ ሚያዚያ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጀመሯል። የበሽር መንግስት ዳርፉር በአምስት የግዛት አስተዳደሮች ይከፋፈል ወይስ በአንድ አስተዳደር ስር ይቆይ የሚለውን ሀሳብ ሕዝብ እንዲወስነበት ምርጫውን ያዘጋጀ ሲሆን አንድ የአስተዳድር ግዛት ነው የሚያስፈልጋት የሚሉት ተቃዋሚዎች ሀሳቡን ተቃመው መራጩ እንዳይሳተፍ ጥሪ አድርገዋል፡፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ዳርፉር ውስጥ በሚገኘው የጸጥታ ሁኔታ ትክክለኛ ምርጫ ሊካሄድ አይቻልም ብሏል። እስካሁን ድምጹን ለመስጠት የወጣው ዜጋ በጣም አነስተኛ መሆኑ ሲነገር ብዙዎችም ወደ ምርጫ የወጡት  በወታደሮች እየተጃቡ መሆናቸው ተገልጿል።

 

Ø ሰኞ ሚያዚያ 3 ቀን 2008 በስማሊያ ዋና ከተማ በሞጋዲሹ በአንድ የምግብ ቤት አቅራቢያ የፈነዳው ቦምብ ቢያንስ አምስት ሰዎች የተገደሉ መሆናችው የዓይን እማኞች ገለጹ። ሬስቶራንቱ የሚገኘው ሀመረወይን በሚባለው አካባቢ ከከተማው አስተዳድር አቅራቢያ በመሆኑ የመንግስት ሰራተኞችን ለመጉዳት ሆን ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነው በማለት ታዛቢዎች ግምታቸውን ይሰጣሉ። ለፍንዳታው እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ግለስብ ወይም ቡድን ባይኖርም አለሸባብ እንደሆነ ይገመታል፡፡ የዛሬው የቦምብ ፍንዳታ የደረሰው ቀደም ብሎ ኬኒያ ውስጥ ተይዞ ወደ ሱማሊያ እንዲመጣ የተደረገና ጋዜጠኞች ገድሏል ተብሎ የተፈረደበት አንድ የበጥይት ተደብድቦ ተገድሏል የሚል ይፋ መግለጫ የሱማሌ መንግስት በሰጠ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ነው።

 

 

 

ሚያዚያ 01 ቀን 2008 ዓ.ም

Ø የወያኔ ዘረኛ ቡድን የድከመውንና የተነቃነቀውን አገዛዙን በኃይልና በሽብር ለመቀጠል ግድያ እስርና ድብደባ የቀጠለ መሆኑ ሲታወቅ ተዳፍኖ የነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ በየቦታው በግልጽ መውጣቱ እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ መሪዎች በቤተ ክህነት ውስጥ ያስቀመጧቸውን ካባ ለባሽ ካድሬዎች ማነቃነቅ መጀመራችው ታውቋል። በዚህ መሠረት የወያኔው ቀንደኛ መሪ አባይ ፀሐዬ በሰጠው መመሪያ መሠረት በአባ ማትያስ አስፈጻሚነት ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች የሰላም ጉባዔ በማለት ማደራጀት መጀመራችው ታውቋል። የሰላም ጉባኤው ተደራጅቶ ወደ ምዕመናኑ ሲደርስ የሰላም ጉባዔ ተደረገ ተብሎ መግለጫና ውሳኔ የሚጠበቅ ሲሆን ውሳኔዎቹ የሕዝባዊ ተቃውሞውን ማውገዝ፣ በስደት የሚገኘውን ህጋዊ ሲኖዶስ መርገም፣ ፀረ ወያኔ የሆነውን ትግል ሁሉ በሽብረተኛነት እንዲፈረጁ ማድረግ መሆኑን ከቤተ ክህነት ያፈተለከው መረጃ አመልክቷል። ቤተ ክህነት ሰላምና እርቅን ይቀር ባይነት ማስተማርና ማስፈጸም ሐዋርያዊ ተልእኮዋ ቢሆንም ካባ ለባሽ ካድሬዎቹ ቤተ ክህነትንና የእግዚአብሔር ቤትን ለሁሉም ምዕመናን ሳይሆን ለአንድ ዘረ የበላይነት አገልጋይና ታዛዥ ማድረጋቸው በምድር ወንጀል በሰማይም ሀጢያት መሆኑን ምእመናን ይገልጻሉ።

Ø የአንድ ዘር የበላይነት ያሰፈነውን ዘረኛ አገዛዝ ዕድሜ ለማስቀጠል የወያኔ ቡድን መሪዎች በየወቅቱና በየጊዜው የወታደርና የፖሊስ ኃይል ምልመላ ሲያካሂዱ አንዳንድ ጊዜም በግዳጁና በማጭበርበር ሲፈጽሙ መቆየታቸው ይታወሳል። ሰሞኑን ደግሞ በማናችውም ዕድሜ ክልል ውስጥ ያለ ሰው ደግሞ በሚሊሺያነት ለመመልመል ጥሪ ማቅረባቸው ከባቲ የመጣው መረጃ አመልክቷል። እንደ መረጃው ከሆነ በባቲ አፋር በአካባቢው ከሚገኙ ነዋሪዎች ታጣቂ ሚሊሺያ ምልምሎ ለማሰልጠን እንቅስቃሴ መጀመሩን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። በአካባቢዎቹ የሚኖር ማንኛውም ሰው ለሚልሺያነት መመዝገብ ግዴታ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የሚሊሺያ ምልመላው ለምን እንዳስፈለገ የተገለፀ ነገር የለም። አምባገነን አገዛዞቹ የሥልጣን የመጨረሻ ዘመናቸው ሁሉንም ነገር በጦር ኃይል ለመቆጣጠር በማሰብ ወታደራዊ ቅጥርና የሚሊሺያ ምልመላ የተለመደ ተግባር ነው የሚሉ ታዛቢዎች አገዛዞች እየሳሱና እየላሉ በሄደ ቁጥር ወታደርና ፖሊስ ማብዛት ሚሊሺያ ማስቀጠር ልማዳቸው ነው ይላሉ።

Ø የወያኔ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ያደረገው ስብሰባ ማጠናቀቁ ተገለፀ። የምክር ቤቱ ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ እንደተመለደውና እንደተጠበቀው ባለፈው ስድስት ወራት አመርቂ ውጤቶች ተገኝተዋል ብሏል። ኢኮኖሚው በፈጣን እድገት ላይ ነው፤ ማኑፋክቸሪንግ እየጎለበተ ነው፤ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ወደ ውጭ የሚላከውን በዓይነት በጥራት አጠናክረን እንቀጥላለን ወዘተ…የሚሉ ምኞትን ብቻ የያዙ ቃላትን ቢደረድሩም ሁኔታው ከሚሉት የተለየ መሆኑ ግልጽ ነው። በተጨባጭ የሚታየው ፖሊቲካው እየከረረ ኢኮኖሚው እየቀጨጨ ሲሆን ወያኔ ይህን ለማስታገስ የጋራ መግባቢያ በሚል የያዘውን አዲስ ፈሊጥ በሚዲያው ለማደንቆር የወሰነ ሲሆን በሀገር ውስጥ ምንም ዓይነት ተቃውሞ ለማድረግ የተሳናቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በጋራ ምክር ቤት ውስጥ ብቻ ተሳትፏቸው እንዲያጠናክሩ ጠይቋል። የወያኔው ኢሕአዴግ በመግለጫው ላይ ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ህይወትን እያወከ አለውንንና አደጋው አስጊ ነው በተባለለት ድርቅ ዙሪያ ዕርዳታ እያቀረብኩ ነው ከማለት ሌላ የገለጸው ነገር የለም። ብዙ የፖሊቲካ ታዛቢዎች ግን ወያኔ ዋና የመነጋገርያ አጀንዳ አድርጎት የነበረው በመላ ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞና ቁጣ ለማስቆም ስለሚቻልበት ሁኔታና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ዙሪያ መምከሩን ይናገራሉ።

Ø ህጻናትን አድን (Save the Children) የተባለው መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት አርብ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ህጻናት አስጊ የሆነ የምግብ እጥረት ውስጥ እንዳሉ ገልጿል። የዘንድሮ ድርቅና ረሃብ በጣም ሰፊና 30 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርበትን አካባቢ ያዳረሰ መሆኑን የጠቀሰው የሕጻናቱ አድን ድርጅት  ከዚህ ውስጥ ሢሶው ማለትም አስር ሚሊዮን የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊ መሆኑን ገልጿል። ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ 14 ሺህ በከብት እርባታ የሚተዳደሩ አባወራዎች አካባቢያቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን በመጥቀስ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ርብርብ ካላደረገ አስጊ ና አደገኛ ሁኔታ እንደሚፈጠር በማስጠንቀቅ በተለይ ህጽናት በምግብ እጦትና በውሃ ወለድ በሽታ እየተጠቁ መሆናችውን ገልጿል። የተለያዩ ድርጅቶች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም እልቂት ሊያስከትል የሚችል ሁኔታ እንዳለ ቢነገርም የተፈለገውን ያህል ለጋሽና ረጅ እንዳልተገኘ አስታውቋል።

 

Ø በዚህ ዓመት ህዳር ወር ውስጥ በፓሪስ ከተማ በደረሰውና የብዙ ሰው ህይወት ባጠፋው የቦምብ ጥቃት ቀንደኛ ተሳታፊ የነበረውና እስካሁን ሲፈለግ የነበረው ሙሀመድ አብሪኒ አርብ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ.ም ብራስልስ ውስጥ በቤልጀየም ፖሊሶች የተያዘ መሆኑ ተነገረ። ባለፈው ወር በብራስልስ አውሮፕላን  ማረፊያ በደረሰው  ጥቃት ላይ ተሳትፎ ያመለጠው ሶስተኛው ግለስብ ይኸው ሙሀመድ አብሪኒ መሆኑንና አለመሆኑንም ፖሊሶች ምርመራ እያካሄዱ ነው ተብሏል። የፖሲስ ቃል አቀባይ አብሪኒ ከሌሎች ስማቸው ያልተገለጸ ሁለት ሰዎች ጋር የተያዘ መሆኑን አረጋግጠዋል። የአብሪኒ የጣት አሻራ በብራስልስ ከተማ በሁለት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ እና እንዲሁም የፓሪሱን ሽብር ለማካሄድ  አጥፍቶ ጠፊዎቹ የተጠቀሙበት መኪና ውስት የተገኘ መሆኑ ታውቋል። በተጨማሪም በብራስልስ ከተማ በተካሄዱትና ለስላሳ ሶስት ሰዎች  ህይወት መጥፋት ምክንያት በሆኑት  የቦምብ አደጋዎች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉት ኦሳማ ክራየም የተባለ የስዊድን ዜግነት ያለው ግለሰብ እና ሌሎች ስማቸው ያልተገለጠ ሶስት ሰዎች መጋቢት 30 ቀን በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውም ተነግሯል። ኦሳማ ክራየም በብራሰልስ ማየልቤክ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ቦምቡን በማፈንዳት ራሱን የገደለው የካሊድ ባክራዊ ተባባሪ የነበረ እና ቦምቡ የፈነዳበትን የስፖርት ቦርሳ ከገበያ ቦታ ገዝቶ የሰጠ ነው ተብሏል።

 

Ø ትናትንት መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓም በጂቡቲ በተካሄደው ምርጫ እንደተጠበቀው የስድሳ ስምንት ዓመቱ ፕሬዚዲንት ሚስተር ገሌህ የድምጹን 87 ከመቶ በማግኘት አሸንፈዋል ተብሏል። ሚስተር ገሌህ ላለፉት 17 ዓመታት በስልጣን ላይ የነበሩ ሲሆን ለአራተኛ ጊዜ አልወዳደርም በማለት ቀደም ብለው የሰጡትን ቃል አጥፈው ለውድድር መቅረባችው ይታወሳል። ከምርጫው በፊት በጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ አፈና መደረጉ የተነገረ ሲሆን መገናኚያ ብዙሃኖችም በሚያስገርም ሁኔታ ለገሌህ ድጋፍ ይሰጡ እንደነበር ታይቷል ተብሏል፡፤ በዚህ ምክንያትም ሶስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫው ላይ ሳይሳተፉ ቀርተዋል። አሜሪካ ጂቡቲ ውስጥ ቋሚ ወታደራዊ ካምፕ በመመስረቷ እና የአገሪቱ ስትራቴጂያዊ ቦታ ለአውሮፓ አገሮች የኢኮኖሚ እና የጸጥታ ጥቅም ከፍተኛ አስተዋጾ ያለው በመሆኑ  ሚስተር ጉሌህ ሲያካሂዱ የቆዩትን  አፈናና የትናንቱን የይስሙላ ምርጫ በዝምታ እንዳለፉት ተስተውሏል።

 

Ø ከጥቂት ቀናት በፊት ካይሮ ውስጥ ተገድሎ ሬሳው ተጥሎ የተገኘውን የጣሊያኑን ተወላጅ የጁሊዮ ሬጂኒ  ጉዳይ አስመልክቶ  የግብጽ የጸጥታ ቡድን ወደ ሮም ዘልቆ ከጣሊያን መንግስት ባለስልጣኖች ሲያካሄድ የነበረው ውይይት ውጤት አልባ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ጣሊያን በግብጽ ያለው አምባሳደሯን ለውይይት በሚል ባስቸኳይ የጠራች መሆኑ ተገልጿል። የጁሊዮ ገዳዮች በአሰሳ የተገደሉት የሽብረተኛ ቡድን አባሎች ናቸው  በማለት የግብጽ መንግስት ያቀረበውን ማስረጃ ቡድኑ ጁሊዮን ለመግደሉ የሚያረጋግጥ መረጃ አልተገኘም በሚል  የጣሊያን መንግስት ውድቅ ያደረገው መሆኑ ታውቋል።  የግብጽ የጸጥታ ኃይሎች ጁሊዮን በቁጥትር ስር ካደረጉ በኋላ በምርመራ አካሉን ጎድተው ሬሳውን ጥለውታል የሚለው ጥርጣሬ ከበድ እያለ በመምጣቱ የጣሊያን መንግስት እና የግብጽ መንግስት ግንኙነት እየተበላሸ ይሄዳል የሚል ስጋት አለ።

 

Ø ዛሬ ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ዓም በሱማሊያ ዋና ከተማ ሁለት የአልሸባብ አባላት  በተወሰነባቸው ፍርድ በጥይት ተደብደበው ሞተዋል። ሁለቱ የአልሸባብ አባላት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ባለፈው ታኅሳሥ ወር በመኪና ላይ ፈንጅ በማጥመድ ሂንዲዮ ሃጅ መሀመድ የተባለውን የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ገድለዋል በሚል ነው። ሱማሊያ ለጋዜጠኞች ስራ አደገኛ የሆነች አገር ስትሆን የፕሬስ ነጻነትም ዝቀተኛ ከሆኑባቸው የዓለም አገሮች ውስጥ አንዷ ነች። የድንበር የለሽ ጋዘጠኞች ድርጅት በ2002 ባካሄደው ጥናት  በፕሬስ ነጻነት ሱማሊያ ከ176 አገሮች 172ኛ መሆኗን አመልክቷል።

 

Ø የዳርፉርን ግዛት በአምስት የአስተዳድር ክልሎች ከፋፍሎ ለማስተዳደር ከበሽር መንግስት የቀረበውን ሀሳብ ህዝብ በውሳኔ ሕዝብ እንዲያጸድቀው ከሰኞ ጀምሮ ለሶስት ቀና ዳርፉር ውስጥ ሕዝቡ ድምጽ እንዲሰጥ ይደረጋል ተብሏል። በዳርፉር የሚገኙ አማጽያን ኃይሎች በጦርነት ቀጠና ውስጥ ባለ አካባቢ ነጻና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የድምጽ አሰጣጡ ተግባር ስለማይፈጸም ሕዝቡ በምርጫው እንዳይሳተፍ እየቀሰቀሱ ይገኛሉ። የአስተዳድሩ በአምስት ክልሎች መከፋፈል በተገቢው መንገድ ለማስተዳደርም ሆነ የኢኮኖሚ እድገት ለማግኘት አስፈላጊ መሆኑ የበሽር መንግስት እየገለጸ ሲሆን የአስተዳድር ክልሉን ክሶስት ወደ አምስት ከፍ ያደረገው የበሽብር አገዛዝ ዳርፉር ላይ ያለው ቁጥጥር ከፍ እንዲል ለማድረገ ነው ይላሉ””

Ø በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች አርብ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓም በጋራ ባወጡት መግለጫ ፕሬዚዳንት ዙማ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ጠየቁ። የሃይማኖት አባቶቹ በሰጡት መግለጫ የፕሬዚዳንት ዙማ የሙስና ተግባር የሞራል የበላይነትን ያሳጣቸው ስለሆነ አገር ለመምራት ብቃት የላቸውም ብለዋል።  የሃይማኖት መሪዎቹ ቀደም  ከገዥው ፓርቲ አባላት ጋር ውይይት ያደረጉ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን የውይይቱ ውጤት ምን እንደነበር ግን ለማወቅ አልተቻለም። የፕሬዚዳንት ዙማ ልጅ በከፊል ባለቤት በሆነበት ኩባንያ ከኃላፊነት ቦታዎች ራሱን ማግለሉን ያስታወቀ ሲሆን ጉብታ የሚባለው የህንዱ ቤተሰብ አባላትም እንዲሁ ከኩባንያው ኃላፊነት ቦታዎች ራሳቸውን ያነሱ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።

 

 

 

 

 

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም.

Ø ተጨማሪ የቤት እስራዔሎች ቤተሰቦች በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሊመጡ ስለሚችሉበት ሁኔታ የእስራዔል ገዥ ፓርቲ ከአጋሮቹ ጋር ስምምነት የደረሰ መሆኑን ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ገልጿል። በዚህ 1300 የሚሆኑት እንዲመጡ የተፈቀደ ሲሆን ወደፊት ቁጥሩ  ከዚህ በላይ ሊጨምር የሚችል መሆኑን ተገልጿል። ባለፈው ወር በእስራዔል አገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው ወደ እስራኤል እንዲመጡ በመጠየቅ ከፍተኛ ትዕየንተ ሕዝብ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የእስራዔል መንግስት ነገሩን ችላ በማለት ኢትዮጵያውያኑን  የፈቃዱን ውሳኔ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ባለፉት ጥቂት ቀናት አንዳንድ የፓርላማ አባላት ባደረጉ ጥረትና እንዲሁም ተቃውሞውና አድማው የጋራ መንግስቱን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ስለገባው  ገዥው ፓርቲ ሀሳቡን ቀይሮ ቤተእስራኤሎቹ ወደ እእስራኤል እንዲመጡ ፈቅዷል።

 

Ø በጂቡቲ ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓም  ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የጂቡቲው ፕሬዚዳንት አሸናፊ ሆነው እንድሚቀርቡ አስቀድሞ ታውቋል። ስድስት ተወዳዳሪዎች ለምርጫው ቢቀርቡም ላለፉት 17 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት አሸናፊ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም በማለት ታዛቢዎች ይተቻሉ። ከተቃዋሚዎች ውስጥ የተወሰኑት በምርጫው ላለመሳተፍ የወሰኑ ሲሆን ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት ደግሞ የፖሊሶች አፈና መጠናከሩንና የመገናኚያ ብዙሃን አድላዊነትን በመግለጽ ክስ እያሰሙ ይገኛሉ። ድምጹን የሚሰጠው  የጂቡቲ ሕዝብ ቁጥር አነስተኛ ነው የተባለ ሲሆን ፕሬዚዳንት ጉሌህ ከየመን የመጡ ስደተኞችን አስመዝገበው ድምጽ እንዲሰጡ እያደረጉ ነው ተብሏል። የተቃዋሚዎች መከፋፈል ጉሌህን ሊጠቅም ችሏል የሚሉ አልጠፉም። ከሶስት አመት በፊት የጉሌህ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎች ትብብር ቢፈጥሩም ጉሌህ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ የሚችል አንድ የጋራ ተወዳዳሪ ማውጣት ላይ ሊስማሙ አልቻሉም።  የምዕራብ አገሮች ጂቡቲ ውስጥ ባላቸው ጥቅም ምክንያት ስለምርጫው አስተያየት ሲሰጡ አይሰማም።

 

 

Ø በሊቢያ የአይሲስ አባላት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋም አዛዥ ተናገሩ። አዛዡ ላለፉት 12 እስከ 18 ወራት ባሉት ጊዚያት ወደሊቢያ የገቡት የአይሲስ አባላት ቁጥር ከ4 ሺ ወደ 6 ሺ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸው አሸባሪዎቹ በብዛት ሊገቡ የቻሉት በአገሪቷ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ እና የጸጥታ አለመረጋጋት ተጠቅመው ነው ብለዋል። አብዛኞቹ ከውጭ የመጡ በመሆናቸውና አገር በቀል የሆኑ አባሎች አነሰተኛ በመሆናቸው እንደ ኢራክና እንደ ሶሪያ የተወሰነ ክልል ይዘው ለመቆጣጠር አይችሉም የሚል አስተያያት አዛዡ ጨምረው ገልጸዋል። በሊቢያ የሚገኙት ልዩ ልዩ የሚሊሺያ ቡድኖች በየቦታው ከአይሲስ ኃይሎች ጋር እየተጋጩ ስለሆነ በራሳቸው የሚጠናከሩበት ሁኔታ አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ።

 

Ø የሴየራ ሊዮን ፕሬዚዳንት በአገራቸው የኢቦላ በሽታ የታደከመ መሆኑን ገልጸው የአገሪቷ ኢኮኖሚ ከወደቀበት ቦታ እንዲያንሰራራ ለማደረግ የውጭ አገር መዋእለ ንዋይ እንደሚያስፈልግ ተናገሩ። ከምዕራብ አፍሪካ አገሮች 11 ሺ ዜጎችን የገደለው የኢቦላ በሽታ የሲየራ ሊዮንን ኢኮኖሚ በተለይም የእርሻውን መስክ ክፉኛ ያጠቃው በመሆኑ የውጭ አገር ሀብታሞች ገንዘባቸውን በልዩ ልዩ የስራ መስክ ላይ በማዋል ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ እንዲያደርጉ ተማጽነዋል። ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ቱርክ ውስጥ  በሚደረገው የእስላማውያን አገሮች አመታዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ተመሳሳይ ልመና የሚያቀርቡ መሆናችውን ገልጸዋል። 

 

Ø የሞሮኮ መንግስት 8 የውጭ አገር ዜጎችን ከአገሩ ያባረረ መሆኑን ገለጸ። ተባረሩ የተባሉት ግለሰቦች ሁለት የፈረንሳይ አንድ የቤልጂክ እና አምስት የስፔይን ዜጎች ሲሆኑ ለመባረራቸው ምክንያት የሆነው በእስር ላይ ለሚገኙት የምዕራብ ሳህራ ዜጎች እርዳታና ትብብር አድርገዋል የሚል ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ግድም ኢዚክ (Gdem Izik) በሚባለው በምዕራብ ሳህራ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የተቀጣጠለው ዓመጽ  ከሞሮኮ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት 11 ፖሊሶችና ሁለት ሰላማዊ ሰዎች መገደላችው አይዘነጋም። ፖሊስ  አመጹን ለማስቆም  ካምፑ እንዲፈርስ ያደረገ ሲሆን በርካታ ሰዎችን ወስዶ ማስሩ ይታወቃል። ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት ባለፈው ህዳር ወር ተይዘው የሚገኙት የምዕራብ ሳህራ ዜጎች እንዲፈቱ መጠየቁ ይታወሳል።

 

 

Ø በዳርፉር አካባቢ የሽብር ተግባር ፈጽመዋል በሚል ክስ አንድ የሱዳን ፍርድ ቤት በ22 የደቡብ ሱዳን ዜጎች ላይ የሞት እና የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት የበየነ መሆኑ ተገልጿል። ክስ የቀረበባቸው 22 ሰዎች ጀስቲስ ኤንድ ኢኩዋሊቲ ሙቭመንት የሚባለው የዳርፉ አማጽያን ቡድን አባላት ሲሆኑ ድርጅቱ ከሶስት አመት በፊት ከሱዳን መንግስት ጋር የእርቅ ስምምነት ፈርሞ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ማቆሙ ይታወቃል። ባለፈው ጥር ወር 22 የደቡብ ሱዳን ዜጎች የአማጽያኑ ድርጅት አባል ሆነው መንቀሳቀሳቸው በመጋለጡ የውጭ አገር ዜጎች በመሆናችው ብቻ በቁጥጥር ስር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ ተደርጓል። ባሁኑ ጊዜ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ ዝቅተኛ ሆኖ የሚታይበት ሲሆን በሰዎቹ ላይ የተበየነው የፍርድ ውሳኔ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ሊያሻክረው እንደሚችል ተገምቷል። የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት በፕሬዚዳንት በሽር ላይ የወንጀለኛነት ክስ ለመመስረት ምክንያት በሆነው በዳርፉር ጦርነት 300 ሺ ሰው ያህል ህይወቱ ሲጠፋ ከ2.5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ ስደተኛ መሆኑ ይታወቃል።

 

 

 

መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በሱሉልታ ከተማ በወያኔ ወታደሮችና በከተማዋ ወጣቶች መካከል ፍጥጫና ውጥረት መፈጠሩ ታወቀ። ፍትጫው የተነሳው በሱልልታ ከተማ የሚገኝ አንድ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር መፈንዳቱን ተከትሎ የወያኔ ፖሊሶችና ጦር የከተማዋን ጥበቃ በማጠናከራቸው ሲሆን ወጣቶቹ ተቃውሞ በማሰማታቸው የወያኔ ፖሊስና ጦር ስትተኩስ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ከፍተኛ የዱላ ድብደባም መፈጸማቸው ታውቋል። የወጣቶቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሚደግበት ወቅት የወያኔ የንግድ ሸሪክ የሆነው የመሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ 3 መኪኖች ሲያልፉ በድንጋይ ተደብድበዋል።

 

Ø በሐረር ዓለማያ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች መኝታ ቤት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ስለደረሰበት ተማሪዎች ትምሀርት አቋርጠው ወደ ቤተ ሰቦቻቸው ለመሄድ የተገደዱ መሆናቸው ከዓለማያ የመጣው መረጃ ያመለክታል። የእሳቱ አደጋ እንዴት እንደተቀሰቀሰና ለምን ሳይጠፋ ረጅም ሰዓት እንደቆየ የታወቀ ነገር ባይኖርም የዓለማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ግን የወያኔ ደህንነት ኃይሎች የተማሪዎቹን መኝታ ክፍሎች ሆን ብለው በማቃጠል ያነጣጠሩባቸው ተማሪዎችንን መምህራንን በሽብረተኛነት ለመክሰስ በማሰብ ነው በማለት ይናገራሉ።

 

 

Ø 10 አመት በፊት በጋምቤላ ከ400 በላይ አኙዋኮች ግድያን ተከትሎ ከወያኔ ጋር ሆድና ጀርባ በመሆን ከሀገር ወጥቶ በኖርዌይ በጥገኝነት ይኖር የነበረው ኦኬሎ አኳይ በወያኔው ፖለቲካ ፍርድ ቤት በሽብረተኛነት ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ሲሆን ከሶስት ሳምንት በኋላ የቅጣቱ ብይን እንደሚሰጠው ተገልጿል። ኦኬሎ አኳይ በአኝዋኮች ፍጅት ወቅት የጋምቤላ ፕሬዚዳንት የነበረ ሲሆን በጋምቤላ የአኙዋኮችንና የኑዌር ግጭትን ወያኔዎች እንደቀሰቀሱት እና የአኙዋኮቹ ፍጅት በወቅቱ የወያኔ መሪ በነበረው በመለሰ ዜናዊ ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ቀደም ሲል አስታውቆ የነበረ ሲሆን አሁንም በወያኔው የፖሊቲካ ፍርድ ቤት ደግሞታል። የወያኔ ወታደሮች 400 አኙዋኮችን ገድለው 60 ብቻ ነው የሞቱት የሚል ማስተባበያ ኦኬሎ እንዲሰጥ አስገድደውት እንደነበርና አዲሱ ለገሰ በረከት ስምኦንና ገብረአብ ባርናባስ የወያኔው ትዕዛዝ በማስፈጸም እጃቸው እንዳለበት ገልጿል። አኮሌ አኳይ ከዓመታት በፊት ወደ ደቡብ ሱዳን በሄደበት ወቅት የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣኖች ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሳጠር ከጁባ ጠልፈውት ወደ አዲስ አበባ እንደመለሱትና በሽብረተኛነት ክስ እንደመሰረቱበት ይታወሳል።

 

Ø በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን ተቀምጠው እጅግ አስነዋሪ ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ የወያኔ ካባ ለባሽ ካድሬዎች ከስልጣናቸው መባረር መጀመራቸውና ዋና ጠባቂው አቡነ ማትያስም ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው ለማባረር መገደዳቸው ታውቋል። የአቡነ ማትያስ ቀኝ እጅ የነበረውና የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ስራ አሲያጅ የነበረው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከየቤተክርስቲያኑና ገዳማቱ ያለውን ንብረት መዝረፉ ብቻ ሳይሆን ለልጁ መታከሚያ በሚል ሰበብ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከቤተ ክርስቲያኗ ካዝና በመሰብሰቡ ከስልጣኑ የተባረረ ሲሆን በእርሱ ምትክ ሌላው ካባ ለባሽ ካድሬ ጎይቶም ያይኔ ተተክቷል። ከየማነ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ኃላፊዎችም ተባረዋል። የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያሉ ማንኛውም ከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲያዝ ባወጣው መመሪያ መሠርት በመንፈሳዊና ሐዋርያዊ ስራ በምትሰራው ቤት ክርስቲያን ውስጥ የዘር መድልዎን በማምጣት ቤተ ክርስትያኗን እያመሳት መሆኑ ምዕመናኑን ካህናቱ በጀመሩት ግፊት ካባ ለባሽ ካድሬዎች ቢነሱም ሌላ ዘረኛ ካባ ለባሽ መተካት ውጤት ስለሌለው ቤተ ክርስቲያኗን ከዘረኛ ካድሬ ቄስና መነኩሴ ማጽዳት የዛሬ ሰራ ነው የሚሉ ምዕመናን ብዙ ናቸው።  

 

 

Ø በአስመራ ከተማ በግድ ታፍሰው በካሚዮን ተጭነው ወደ ጦር ማሰልጠኛ ሲወሰዱ የነበሩ ወጣቶች ከተሳፈሩባቸው መኪናዎች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በሻዕቢያ ወታደሮች በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። የተገደሉትና እና ምን ያህል እንደሆኑ ለጊዜው ባይታወቅም ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም  ካሚዮኖቹ የሚሄዱበትን መንገዶ በአውቶቡስ አማካይነት  ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ የወጣቶቹ ዘመዶችና ጓደኞች በሙሉ በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። የሻዕቢያ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ የሰጠው መግለጫ የለም። በሻዕቢያ ውስጥ የወታደራዊ አገልግሎት የጊዜ ወሰን የሌለው መሆኑ ሲታወቅ አብዛኛዎቹ እድሜ ልካቸውን ሲያገለግሉ የሚቆዩ መሆናቸውና  የኑሮው ሁኔታቸውም በጣም አሰቃቂ እንደሆነ ይነገራል። ይህ አሰቃቂ የኑሮ ሁኔታና የሻዕቢያን አፈና ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገሮች እና ወደ አውሮፓ መሰደዳቸው በየጊዜው የተገለጸ መሆኑ ሲታወቅ የሻዕቢያ አገዛዝ ከፍተኛ አፈናና ጭፍጨፋ ከሚያካሄዱ የአለም አገሮች ውስጥ ዋነኛው ነው በማለት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ድምጻቸው በተደጋጋሚ ሲያሰሙ ቆይተዋል።

 

Ø በሊቢያ በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበረሰባዊ መገናናዎች አማካይነት በድብቅ የሚካሄድ የመሳሪያ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ እየደራ መምጣቱን ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን ይሰራጫል የተባለ አንድ ጥናታዊ ዘገባ አመለከተ። ለአርባ ዓመት ሊቢያን ሲገዛ የቆየው የኮሎኔል ጋዳፊ አገዛዝ በየጊዜው ያከማቸው መሳሪያ አገዛዙ ሲወድቅ በተለያዩ አማጽያን እጅ የገባው መሳሪያ ዛሬ በጥቁር ገበያ በሰፊው እየተሸጠ መሆኑን ጥናቱ ይዘረዝራል። በፌስ ቡክ፣ በኢንስታግራም፣ በዋትስ አፕ፣ እና በቴሌግራም አማካይነት በብዛት እየተሸጡ ያሉት መሳሪያዎች እንደሽጉጥና ካላሽንኮቭ የመሳሰሉት የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ሲሆኑ ለሽብርተኞች መገልገያ የሆኑ በትከሻ ላይ ሆነው የሚተኩሱ ጸረ አውሮፕላንና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችም የሚሸጡ መሆናቸውም ተጠቁሟል። አንድ ካላሽንኮፍ መሳሪያ እስከ 1800 ዶላር ሲያወጣ በተለይ የመጓጓዣ አውሮፕላንን ሊመታ የሚችል ጸረ አውሮፕላን መሳሪያ ደግሞ እስከ 62 ሺ የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸጥ ዘገባው ይገልጻል። የመሳሪያ ሽያጮቹ የሚከናውኑት በአብዛኛው እንደ ትሪፖሊ፣ ቤንጋዚ እና ሳብራታ በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች ሲሆን ንግዱ የሚካሄደው ወጣቶች በሆኑ የተለያዩ የሚሊሺያ አባላት መካከል መሆኑም ተድርሶበታል።  የፌስ ቡክ ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ ይህን የመሰለ ንግድ በፌስ ቡክ አማካይነት መካሄዱ ወንጀል ገልጾ መረጃውን እየፌስ ቡክ አገግሎቱን እንዘጋዋለን ብሏል። የአውሮፓ ባለስልጣናትም ጉዳዩ ያሳሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፤

    በተያያዘ ዜና ትሪፖሊን መሰረት አድርጎ ሲንቀሳቀስ  የነበረው የመንግስት አካል በትናንተናው ዕለት ደም መፋሰስን ለማስወገድ ከስልጣን ወርጃለሁ የሚል መግለጫ በፍርድ ሚኒስቴሩ አማካይነት መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን የዚሁ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሚስተር ካሊፋ ገውሊ  ደግሞ በድረ ገጻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ ቀደም ብሎ የወጣውን መግለጫ መቃወማችውን ገልጸዋል። መግለጫ  ማንም ሚኒስቴር ሆነ ሌላ ኃላፊነት የተሰጠው ግለስብ በተመድ ከተሰየመው የአንድነት መንግስት ጋር እንዳይተባበር የሚያሳስብ ሲሆን ተባባሪ ሆኖ ከተገኘ ከፍተኛ እርምጃ እንደሚወሰድበት ይገልጻል። ሚስተር ካሊፋ ገውሊ በተመድ የተቋቋመውን የአንድነት መንግስት በጽኑ ከሚቃወሙ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆናችው የሚታወቅ ሲሆን መግለጫቸው በሌሎች ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው ለጊዜው ለማወቅ አልተቻለም። በአሁኑ ወቅት ሚስተር ካሊፋ ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ የገፋፋቸው ምክንያቶች ለጊዜው ግልጽ ባይሆኑም በቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ ክፍፍል መኖሩን ያሳያል በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ።

Ø የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር ለቢቢሲ ጋዘጠኛ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአሁኑ የስልጣን ዘመናቸው በ2013 ዓም ሲያልቅ ስልጣናቸውን የሚያስረክቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስልጣን የሚለቁ መሆናቸውን በመግለጽ የገቡትን ቃል በተደጋጋሚ ሲያጥፉ የነበሩ በመሆናቸው እለቃለሁ ብለው መናገራቸው የተለመደው ማጭበርበር ነው  የሚሉ በርካታ ናቸው። ፕሬዚዳንቱ በቃለ ምልልስ ወቅት በዳርፉር ከ10 ሺ በላይ ዜጎች ቤታቸው ጥለው ተሰደዋል፤ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በካምፕ ውስጥ ይኖራሉ  በሚል ተመድ ያሰራጨው መረጃ የተጋነነ ነው ከማለታቸውም በላይ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በዳርፉር የሚቆዩበት ምንም ምክንያት ስለሌለ ባስቸኳይ መውጣት አለባቸው ብለዋል። የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለፖሊቲካ ማራመጃ ተብሎ የተቋቋመ መሆኑን በመግለጽ በአገራቸው ሕዝብ ተወዳጅነት ስላላቸው የተመሰረተባችውን ክስ እንደማይቀበሉት በቃለ ምልልሱ ገልጸዋል።

 

·        በተያያዘ ዜና ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ከሳልቫ ኪር ጋር ከጥቂት ወራት በፊት እርቅ የተፈራረሙት  ሪክ ማቻር በሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም ጁባ የሚገቡ መሆናቸውንና በዚያም ከሳልቫ ኬር ጋር በመሆን የአንድነነቱን የሽግግር መንግስት እንደሚያቋቁሙ ገልጸዋል። ባሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ቦታዎች የሚደረጉት ጦርነቶች ሙሉ በሙሉ ያልቆሙ በመሆናቸው ስምምነት የተደረገበት የአንድነት መንግስት ስራ አለመጀመሩ ብዙዎችን ሲያሳስብ ቆይቷል። በሌላ በኩል በደቡብ ሱዳን  መድኃኒት እና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መሳሪያዎች ከፍተኛ እጥረት በመፈጠሩ ርዳታ ፈላጊዎችን ለመርዳት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ድንበር የለሽ ሃኪሞች የተባለው ድርጅት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ ገልጿል። መግለጫው የእርዳታ ድርጅቶችና ሌሎች የአለም አቀፍ ተቋሞች ይህን ከፍተኛ የሆነ እጥረት ለማሟላት ባለመቻላቸው የብዙ ሰዎች ህይወት አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ ችሏል ብሏል።  የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የዓለም አቀፉ የእርሻ እና የምግብ ድርጅት ማክሰኞ መጋቢት 27 በሰጡት መግለጫ በደቡብ ሱዳን የእርዳታ እህል እጥረት በመኖሩ ከፍተኛ ረሃብ እየተከሰተ መሆኑን የገለጹ መሆናቸው ይታወሳል።

 

 

 

መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በሊቢያ የትሪፖሊ ከተማን ማዕከል አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ራሱን መንግስት ነኝ ብሎ ሲጠራ የቆየው አካል ስልጣን የለቀቀ መሆኑን የፍርድ ሚኒስትሩ ባሰራጨው መግለጫ አሳታውቋል። መንግስቱ በመግለጫው ላይ ይህንን እርምጃ የወሰደው በአገሪቱ ውስጥ ተጨማሪ ደም መፋሰስን ለማስቀረት ነው ብሏል። የመንግስት ማህተም ያለበትና በማን እንደተፈረመ የስም ዝርዝር የማያሳየው በይፋ የተሰራጨው መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ ፕሬዚዳንቱም ሆኑ ሚኒስትሮቹ ስራ መስራት ያቆሙ መሆናቸውን ገልጿል። ባለፈው ረቡዕ ትሪፖሊ ወደብ የገባው በተመድ አስተባባሪነት የተቋቋመው የሊቢያ የአንድነት መንግስት ተወካዮች ቡድን ከባህር ኃይል ቅጥር ግቢ ውስጥ ስራውን እያካሄደ መሆኑና ከአንዳንድ ክፍሎች ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ የተነገረ ቢሆንም  በርከት ያሉ የመንግስት መዋቅር አባላትና የሚሊሺያ መሪዎች አሁን ድረስ ተቃውሞ እያሰሙ በመሆናቸው በምን ያህል ጊዜና በምን ዓይነት ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቶ አገሪቱ ሊያረጋጋ እንደሚችል እስካሁን ግልጽ አይደለም።

 

Ø የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሚስተር ዙማ በወንጀል ተከሰው ከስልጣን እንዲወገዱ የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ተወያቶ እንዲወስንበት በተቃዋሚ ክፍሎች የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንደተጠበቀው ውድቅ መደረጉ ታውቋል። የፕሬዚዳንቱ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ አብላጫውን መቀመጫ የያዘበት የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ 233 የምክር ቤት አባላት ድምጽ በመስጠት የውሳኔ ሀሳቡን ውድቅ አድርገውታል። የውሳኔ ሀሳቡን የደገፉት የተቀዋሚ ድርጅቶች አባላት ቁጥር 143 ብቻ ነበር። የውሳኔ ሀሳቡ ሊያልፍ የሚችለው ከምክር ቤቱ መቀመጫዎች ሁለት ሶስተኛው ከደገፈው ብቻ ነው የሚል ሕግ በመኖሩ የውሳኔ ሃሳቡ ውድቅ ሆኗል። ፕሬዚዳንቱ በሙሥና በመዘፈቃቸውና የዝምድና ስራ በማስፋፋታቸው ምክንያት የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ ከፍተኛ ጥላቻና ጥርጣሬ እያሳየ ባለበት ሁኔታ የአፍሪካ ብሔራዊ  ኮንግሬስ እሳቸውን ለመደገፍ ሙሉ ድምጽ መስጠቱ ፓርቲው በሚቀጥለው ምርጫ ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዳይሆን ሊያግደው ይችላል የሚሉ ታዛቢዎች አልጠፉም። ፕሬዚዳንቱን የሚቃወሙ ድምጾችም እየበረከቱ መጥተዋል። ትሬቨር ማኑዔል የተባሉት የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር እና አህመድ ካትራዳ የተባሉት የኔልሰን ማንዴላ የእስር ጓደኛ ፕሬዚዳንቱ በግላቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠይቀዋል። የሃይማኖት፤ የምሁራንና የሌሎች የብዙኅን ማህበራት ድርጅቶች አባላት ፕሬዚዳንቱ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ለመግፋት ተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድርግ ዝግጅት እያደረጉ ነው።

Ø የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ባካሄደው ተከታታይ ወታደራዊ እርምጃ 11 ሺ 595 ሰዎችን ከቡድኑ ጥቃትና ቁጥጥር ነጻ ያወጣ መሆኑን ገልጾ የተያዙትንም ሆነ በነጻ እጃቸውን የሚሰጡትን የቦኮሃራም ታጣቂዎች ወደሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ የማስተማሪያና የማሰልጠኛ ካምፖች ያቋቋመ መሆኑን ገልጿል። ግለሰቦች ራሳቸውን ችለው በህብረተስብ ውስጥ ድርሻቸውን እንዲወጡ በካምፑ ውስጥ ልዩ ልዩ የሞያ ትምህርቶች የሚሰጡ መሆናቸውም ተገልጿል። እስካሁን ድረስ እጃውን ሰጥተው ወደ ካምፑ የገቡ የቦኮሃራም ታጣቂዎች ምን ያህል እንደሆኑ ባይታወቅም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቡድኑ ወደተሸሸገባቸው ቦታዎች ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች እንዳይደርሱ መንግዶች በመዘጋታቸው በረሃብ የተጠቁ በርካታ የቦኮሃራም አባላት እጃቸውን የሰጡ መሆናችው ተዘግቧል። የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቦኮ ሃራምን ለመደምሰስ ጫካውን ሁሉ ለማጠርና ለመቆጣጠር አቅም ባይኖረውም የምግብና መሰል ቁሳቁሶች የሚጓጓዙበትን መስመር መዝጋቱ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል ተብሏል።

 

Ø የፓናማ ሰነድ የሚል መጠሪያ ያገኘው በድብቅ የተለቀቀው መረጃ ከሚያጋልጣቸው ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ታቃቂ ግለሰቦች መካከል የአፍሪካ ባለስልጣናት እንደሚገኙበት ታወቀ። ሞሳክ ፎንሴካ የተባለው የፓናማ የሕግ ኩባንያ የንግድ ግንኙነት ከመሰረታቸው ታዋቂ የአፍሪካ ግለሰቦች መካከል ክላይቭ ኩሉቡሴ ዙማ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት  የወንድም ልጅ፤ ካልፓና ራዋል የኬኒያ ምክትል የፍርድ ሚኒስትር፤ ጆን አድዶ ኩፎር የቀድም የጋና ፕሬዚዳንት ልጅ፤ ማማዲ ቱሬ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ባለቤት፣ ሙኒር ማጃዲ የሞሮኮ ንጉስ የግል ጸሐፊ፣ ጆዜ ቫስኮንሴሎስ የአንጎላ የነዳጅ ሚኒስትር፤ ኢያን ከርቡ የቦትስዋና የይግባኝ ፍርድ ቤት ኃላፊ፤ ጃኔት ካቢላ የኮንጎው ፕሬዚዳንት ካቢላ እህት፤  ኮጆ አናን የቀደሞ የተመድ ዋና ጸሐፊ የኮፊ አናን ልጅ ይገኙባቸዋል። እስካሁን የተጋለጡት እነዚህ ሲሆኑ ስም አይዘርዘር እንጅ ከኢትዮጵያውም ሰዎች እንዳሉበት ተጠቁሟል። ብዛታቸው 1.5 ሚሊዮን የሆነው እነዚህ ልዩ ልዩ ሰነዶች ምርመራቸው ሲያበቃ በርካታ ሰዎች ይጋለጣሉ የሚል ግምት ተወስዷል።

 

 

 

 

 

መጋቢት 27 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø የወያኔ ቀኝ እጅ እና ጉዳይ ፈጻሚ የሆነው ኢሕአዴግ መደበኛ የምክር ቤት ጉባዔ የተባለለትን ስብስባ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2008 ዓም ጀምሯል። ስብሰባው ነገ መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓም ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉባኤው በይፋ ያለፉትን ስድስት ወሮች የስራ ሂደት ይገመግማል ተብሎ ቢነገርም በዋናነት ግን በመላ ኢትዮጵያ ስለተቀጣጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ የድህረ ገጾች ግንኙነት መደናቀፍና የቴሌኮም መረጃ መለዋወጥ ላይ የተፈጠረውን ችግር ይመክርበታል ተብሏል። ለወያኔ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ኢሕአዴግ ምክር ቤት ወያኔ በኦህዴድ ላይ ስለሾማቸው ሰዎችና ታፍነው ስለተወሰዱ ሰዎች ውሳኔ የሚሰጡ ሲሆን ፍትህ ሚኒስትርን አፈርሰው ጠቃላይ አቃቤ ህግ ስለሚለው ህግና ማሪሚያ ቤት ለዓቃቤ ህግ ተጠሪ ስለሚሆንንበት ጉዳይ እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ የተባለው ተቋም  ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ስለሚያዘው ህግና የወያኔ ድርጅት ሰዎች የድህንነት ከለላና በተመለከተ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል።

 

Ø ስግብግብነት፣ አልጠግብ ባይነትና  ነጥቆ መውሰድ መለያቸው የሆነው የወያኔ ባለስልጣናት ጥቅም የሚገኝበትንና ገንዘብ አትራፊ የሆነውን ሁሉ መጠቀሚያ ማድረግ ባህሪያቸው ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ ኢንተርኔትን በመጠቅም ከማንኛውም የዓለም ክፍል ጋር በነጻ ስልክ መገናኛ የነበሩትን ቫይበርና ዋትስ አፕን በክፍያ እንዲሰሩ ለማድረግ ያቀደ  ከውጭ አገር የሚገቡ  ስልኮችም ለክፍያ እንዲያመቹ ልዩ ቁጥጥር ተደርጎባቸው ከውጭ የሚገቡ የግለሰስብ ስልክ ቁጥሮች ላይ ቀረጥ ይጣላል ተብሏል።፡ወያኔ ተጨማሪ ክፍያ መጠየቁ ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ የቀረጥ ገቢም ለማግኘት ጭምር አዲሱን መመሪያ ማውጣቱ ተገልጿል። በዘመናዊ የዲጂታል ዘመን ዜጎች የቴክኖሎጂው ውጤትን ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የገንዘብ ክፍያ መጠየቁም ሆነ ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎች ላይ ቀረጥ ለመጣል ማቀዱ የወያኔ አገዛዝ ቴክኖሎጂውን ሰው እንዳይጠቀምበት እያደረገ ያለ ሲሆን ከተጠቀመም ውድ ዋጋ በማስከፈል ሕዝብን ከማኅበራዊ ጎዳናና ከሶሻል ሚዲያ በማራቅ ደህንነቱን ለመጠበቅ ሆን ብሎ የተጠቀመበት ዘዴም መሆኑን ብዙ ዜጎች ይናገራሉ።

 

Ø የወያኔ ዘረኛና አምባገነን አገዛ በሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሰራቸው ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱና ቁጥራቸውን አለመግለጹ ይታወቃል። ጉዳዩን በደንብ የተከታተሉና መረጃ ያሰባሰቡ ወገኖች እንደገለጹት ከሆነ ደብዛቸው የጠፋ እስረኞችን ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እንደተወስዱና በጦር ካምፕ ውስጥ ከፍተኛ እንግልት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ጉዳዩን የተከታተሉ ወገኖች በአሁኑ ጊዜ ከ2800 በላይ ሰዎች በጦላይ እንደሚገኙና ከሀረር የመጡ የሰባት ልጆች እናትም እንደሚገኙበት አስታወቀዋል። ለወያኔ ታማኝ በመሆን የጦር ካምፑን የሚመሩና የእስረኞቹን ሁኔታ የሚከታተሉ በዙ ዋቅቤላ፤ ቀንአ ያደታ፣ ተሾመ ዱጋሳ ፤ ጸሐይ ነጋሽና የወያኔው ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን መሆናቸው ሲታወቅ የወያኔ መሪዎችንና ኃላፊዎች ከእነዚህ ተላላኪ ግለሰቦች ጀርባ ሁኔታዎችን የሚዘወሩ መሆናቸው ተገልጿል። በጦር ካምፑ ውስጥ በተለይ የኦሮሞ ወጣቶች በብዛት ይኑሩ እንጅ ከመላ ኢትዮጵያ የተሰበስውና በወያኔ ላይ ተቃውሞና ቁጣ ያሰሙ የሕዝብ ልጆች የታጎሩበት የጦር ማሰልጠኛ መሆኑ ተብራርቷል።

 

 

Ø አንጋፋው የዘመናዊ ሙዚቃ የሳክሲፎን ተጫዋን ጌታቸው መኩሪያ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ከቆየ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሙዚቀኛው ጌታቸው መኩሪያ ዘመናዊ ሙዚቃን በኢትዮጵያ ስር እንዲሰድ ካደረጉና ሳክሲፎን መጫወት ከጀመሩ ኢትዮጵያውያን የመጀመሪያዎቹ ተርታ የሚቀመጥ እንደነበረና በብሔራዊ ቲያትር በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ ውስጥ ከሙዚቃ ተጫዋችነት እስከ ዋና መምህር በመሆን ለዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ የተወጣ ሙዚቀኛ ነበር። ሙዚቀኛ ጌታቸው መኩሪያ በሳክሲፎን አጨዋወቱና የሙዚቃን መሳሪያ እንደልብ ማዘዝ በመቻሉ የሳክሲፎን ንጉስ የሚል ቅጽል ከሙዚቃ አፍቃሪዎች የተቸረ የተዋጣለት የሙዚቃ ባለሙያ ነበር። ሙዚቀኛ ጌታቸው መኩሪያ የዘጠኝ ልጆች አባትና የ81 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የነበረ ነው። የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ በዚህ ታላቅ የሙዚቃ ሰው ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፤ ለዘመዶቹ ለወዳጆቹ እና ለአድናቂዎቹ ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።

 

Ø ሞሳክ ፎንሴካ ከተባለ የፓናማ የሕግ ስራ ኩባንያ በድብቁ የወጡ 11.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ልዩ ልዩ ሰነዶች የተለያዩ መሪዎችና ታላላቅ ሰዎች ታክስ ባለመክፈል እና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ገንዘቦችን በማስተላለፍ በኩል የሰሩትን ወንጀል ያጋለጡ መሆናቸው ተገለጸ። ምንጫቸው ካልታወቀ በአንድ የጀርመን የጋዜጣ ተቋም መጀመሪያ ተሰራጭቶ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ተመራማሪ ጋዜጠኞች ተሳትፈውበት የወጣውና በርካታዎችን የሚያጋልጠው ዘገባ በወንጀሉ ውስጥ 140 የሚሆኑ ታላላቅ የፖሊቲካ ሰዎች 12 የወቅቱና የቀደሞ የአገር መሪዎችን ያጋልጣል። ከእነዚህም ውስጥ የአሁኑ የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዘመዶች፤ የራሺያው የሚስተር ፑቲን የቅርብ ረዳቶች፤ የአይሳላንዱ ጠቃላይ ሚኒስትር፤ ሟቹ የእንግሊዙ መሪ የሚስተር ካምሪን አባት፤ የዩክሬኑ መሪ ፖሮሼንኮ፤ የሳኡዲ አረቢያ ንጉስ ተጠቅሰዋል። ከዚህ በተረፈ ለአርባ አመታት ያክል በኩባንያው የተስተናገዱ 214 ሺ የውጭ ኩባንያዎችን የሚያጋልጥ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የሰሜን ኮሪያ የሶሪያ ኩባንያዎች፤ በእንግሊዙ HSBC በስዊዘርላንዱ Credit swiss በፈረንሳዩ ሶስይቴ ጄኔራል የተቋቋሙ ኩባንያዎች ከሞሳክ ፎንሴካ ጋር መስራታቸው ተጋልጧል።  የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት መልስ ለዚህ ዓይነት መሰረተ ቢስ ክስ የምንለው የለም ሲሉ የክሪምሊን ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ ደግሞ ሰነዱን አወጡት የተባሉት ብዙዎቹ ጋዜጠኞች የቀድሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የሲአይ ኤ እና የልዩ አገግሎት ሰራተኞች መሆናቸውን ገልጾ ይህ በሩሲያ ውስጥ አለመረጋጋት እንዲፈጠር የተደረገ  የአሜሪካ ሴራ ነው ብሎታል። የአይስላንድ ጠቅላይ ሚኒስትርም ስልጣን እንዲለቁ ከፍተኛ ግፊት የተደረገባቸው ሲሆን ፓርላማው ፈርሶ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ  እንዲያፈርሱ ፕሬዚዳንቱን ጠይቀዋል ተብሏል። አውስትራሊያ ፈረንሳይና ኒዘርላንድ ጉዳዩን እንመረምራለን ብለዋል።

  

Ø በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተሰማርተው የነበሩና ህጻናትን አስገድደው በመድፈር የተከሰሱ ሶስት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ወታደሮች እስር ቤት እንዳሉ በአንድ ወታደራዊ  ፍርድ ቤት ላይ የቀረቡ መሆናቸው ተነገረ። ሁለቱ ህጻናትን አስገደደው ደፍረዋል የሚል ክስ የቀረባባቸው ሲሆን አንደኛው ለመድፈር ሙከራ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበታል። ሶስቱም የቀረበባቸውን ክስ ሀሰት ነው በማለት ክደዋል። በማዕከላዊ አፍሪካ ረፐብሊክ በተሰማሩ የተመድ እና የፈረንሳይ ወታደሮች ተፈጽማዋል የተባሉና ከተበደሉ ዜጎች አቤቱታ የቀረበባቸው ህጻናትን ጨምሮ ሴቶችን አስገድዶ የመድፈር ወንጀሎች ከ100 በላይ የደረሱ ሲሆን ከእነዚህ ተከሳሾች ውስጥ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ለፍርድ ሲቀርቡ ይህኛው እስካሁን የመጀመሪያ መሆኑ ነው። የፈረንሳይ ወታደሮች በአዲስ መልክ የቀረበባቸውን ክስ እየመረመሩ መሆናቸው ኤኤፍ ፒ የተባለው የዜና ወኪል ቢያስታውቅም ከዚህ በፊት ለቀረቡት የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩ ይታወቃል። በሌላ በኩል በኮንጎ ዴሞክራቲክ ተሰማርተው የነበሩና አስገድዶ በመድፈር አቤቱታ የቀረበባቸው የታንዛኒያ ወታደሮች ልጆች ያስወለዱ መሆናቸውንም ተጎጅዎች ክስ አቅርበዋል። ክስ የቀረበባችው አስራ አንድ ወታደሮች ሲሆኑ 4 ቱ በቅርቡ የተሰማሩ የተቀሩት ሰባቱ ደግሞ ቀደሞ ባለው ስምሪት ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል። ባለፈው ዓመት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 69 የሚሆኑ ሰዎች በደል የተፈጸማብቸው መሆኑን ሲያመለክቱ ወንጀሉን የፈጸሙት ከ10 አገሮች የተውጣጡ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት መሆናቸው ተነግሯል። በዚህ ወር ውስጥ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት አቤቱታ የቀረባባቸው የሰላም አስከባሪ ኃይል ቡድኖች ሁሉ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ይታወሳል። አንድ ገለልተኛ የሆነ የጥናት ቡድን የተመድ ኃይላፊዎች ጉዳዩን በሚገባ አለመከታተላቸውና ለችግሩ መፍተሄ በመስጠት በኩል ከፍተኛ ድክመት ያሳየ መሆኑ መግለጹ የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወርም በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተመድ ቋሚ መልክተኛ የሆኑት ከኃይላፊነት እንዲነሱ የተደረገ መሆኑ ይታወሳል።

 

Ø በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የአፍሪካ ህብረተ የሰላም አሰከባሪ ኃይል አባላትና የሱማሌ መንግስት ወታደሮች በጋራ ባካሄዱት የጥቃት እርምጃ ስድስት የአልሸባብ መሪዎችን የገደሉ መሆናችውን ገልጸዋል። ከተገደሉት መካከል አንዱ በዜግነት የመናዊ የሆነና ቦምብ በመስራት በኩል የተካነ ነው የተባለ ሲሆን ሌላኛው በስልጠና ስራ ላይ የተሰማራ ኬኒያዊ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያም አንድ ሌላ ወታደራዊ መሪ መገደሉ የተገለጸ መሆኑ ይታወሳል። አልሸባብ እስካሁን ለመግለጫው የሰጠው መልስ የለም።

 

Ø በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዑክ ሚስተር ማርቲን ኮብለር ወደ ሊቢያ ተጉዘው በቅርቡ ከተመሰረተውና ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ወደሊቢያ ከገባው የአንድነት መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር መነጋገራቸው ተገልጿል።  የአንድነት መንግስቱ በሊቢያ ውስጥ  ተቀባይነት እንዲኖረው ከፍተኛ ጥረት በሚደረግበት ወቅት  ሚስተር ኮብለር ወደ ዚያ ሄደው መገናኘት መቻላቸው ሁኔታዎችን በማመቻቸት በኩል አጋዥ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ባለፈው ወር ኮብለር ወደ ትሪፖሊ ለመግባት ጠይቀው በባለስልጣኖች የተከለከሉ መሆናቸው ይታወሳል። ባለፈው ረቡዕ ትሪፖሊ የገባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የአንድነት መንግስት ተወካዮች ቡድን እስከአሁን ድረስ በወደቡ አካባቢ በሚገኘው የባህር ኃይል ወታደራዊ ካምፕ ውስጥም በመሆኑ ለመስራት እየሞከረ  ሲሆን በተለያዩ የሊቢያ ክፍሎች ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ ይነገራል። የሊቢያ የኢንቬስትመንት ባለስልጣን፤ የሊቢያ የነዳጅ ኮርፖሬሽን እና የሊቢያ ማዕከላዊ ባንክ የአንድነት መንግስቱን የደገፉት ሲሆን 10 የሚሆኑ የሊቢያ የወደብ ከተሞችም የተለያዩ የሚሊሺያ ቡድኖች ድጋፋቸውን የሰጡት መሆኑ ተገልጿል፡፡

 

Ø ቦካ ሃራም ላይ ለመዝመት የተቋቋመው የጋራ ኃይል ለሶስት ቀናት ያህል በናይጀሪያ በካሜሩንና በቻድ ወሰን አካባቢ ባካሄደው አሰሳ 300 የሚሆኑ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ያደረገ መሆኑና ከ 2000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አስሮ የፈታ መሆኑን በጋራው ኃይል ውስጥ የካሜሩን  ወታደራዊ ኃይል  አዛዥ የሆኑት ግለሰብ ማክሰኞ መጋቢት 27 ቀን በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።  ዘመቻ የተካሄደው ኩምሸ ከምትባለው የሰሜን ናይጄሪያ ከተማ 35 ኪሎሜትር ላይ ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ መሆኑንና  በአሰሳውም የቦኮ ሃራም የማስልጠኛ ተቋሞችና ልዩ ልዩ መገልገያ መሳሪያዎች የተደመሰሱ መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል። ቦኮ ሃራምን ለመደምሰስ ካሜሩን ናይጄሪያ እና ቻድ በጋር 9000 አባላት ማቋቋማቸው አይዘነጋም፡፤  

 

 

 

 

መጋቢት 26  ቀን 2008 ዓ.ም

 

 

Ø በኢትዮጵያ ያለውን ድርቅና ረሃብ ለማስወገድ ከውጭ መንግስታት በእርድታና በልገሳ የተገኘ እህልና ምግብ የጂቡቲ ወደብ በመጨናነቁ ምክንያት የእርዳታ እህል ለማራገፍ ያልተቻለ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። የወያኔ ቡድን መሪዎች የእርዳታ እህል በጂቡቲ ወደብ ለማራገፍ ባለመቻሉ በሱዳንና በበርበራ ወደብ ለመጠቀም መወሰኑን የወያኔ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የኢትዮጵያ ድርቅን ረሃብ አሳሳቢነት ወደ አስጊነት ደረጃ በደረሰበትና  የተረጀው ቁጥር እየጨመረ ነው በሚባልበት ሰዓት በሱዳን ወደብ በኩል የወያኔ መሪዎች የሚገግዱትን 100 ሺ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ለማስገባት ውል ሲፈራረሙ ለተራቡና በድርቅ ለተገጎዱ ወግኖች ደግሞ በሱማሊያ በርበራ ወድብ በኩል 25 ሺ ሜትሪክ ቶን የእርዳታ እህል ለማስገባት ወስኗል። ድርቅና ረሃብ በበረታበትና የዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ለእርዳታ በሚረባረቡበት ሰዓት የወያኔ መሪዎች በንግድ ድርጅቶቻቸው አማኝነት ያስመጡትን ማዳበሪያ ከእርዳታ እህል ይልቅ ቅድሚያ መስጠታቸው የአገዛዙ ሆነ የመሪዎቹ አረመኔትን በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል። በረሃብ የተጠበሰው ወገን  የሚቀምሰውና የሚልሰው አጥቶ የእርዳታ እህል በየወደብ የሚያራግፈውና የሚያነሳው ባጣበት ሰዓት የወያኔ መሪዎች በየቀኑ 10 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ከሱዳን ወደብ እያነሱ ሲሆን የጭነት መኪናዎችም ቅድሚያ የወያኔን ማዳበሪያ እንዲያነሱ መታዘዛቸው ታውቋል።

 

Ø የወያኔ መሪዎች የነፍስ አድን ዕርዳታውን ከማስገባት ይልቅ  የንግድ ማዳበሪያዎችን ቅድሚያ ሰጥቶ በማስነሳት በረሃብተኛው ሕዝብና በድርቅ ጉዳተኞች ህይወት ቁማር ሲጫወቱ በመሃል ሀገር የወያኔ ካድሬዎችና ሹማምንት የዕርዳታ እህልና አልሚ ምግቦችን ከተራቡ ወገኖች ጉሮሮ በመንጠቅና በመስረቅ እየሸጡ መሆናቸው ታውቋል። በስልጢ ወረዳ የወያኔ መሪዎች የመደቧቸው ባለሥልጣናት በረሃብና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እንዲፋፈል የተመደበውን 500 ኩንታል አልሚ ምግብ ማለትም ወተት ዘይትና በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን በቀጥታ ወደ ገበያ በመውሰድ እየቸበቸቡት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።  እነዚህ የአካባቢው  ባለሥልጣኖች ከወያኔ መሪዎች ጋር በመመሳጠር የእርዳታ እህሉንና አልሚ ምግብን ገበያ ማውጣታቸው የግለሰቦቹ ጭካኔና ስግብግብነት ብቻ ሳይሆን የወያኔ መሪዎችን ችላ ባይነትም አጋልጧል። የወያኔ መሪዎች ጫካ በነበሩበት ወቅት በድርቅና በረሃብ መነገድ የዘወትር ተግባራቸው የነበረ ሲሆን ስልጣን ከያዙ ወዲህም የእርዳታ እህልን እንደ ፖሊቲካ መሳሪያ በመጠቀምና በመሸጥ የግል ኪሳቸው ሲያደልቡ መቆየታቸው ይታወቃል። በኢትዮጵያ ከ450 ሺ በላይ ሕጻናትና አልሚ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ስልጢ ወረዳ ውስጥ ከ26 ሺ በላይ  እርዳታ ፈላጊዎች ናቸው።

 

 

Ø ማኅበረ ቅዱሳን ከመጋቢት 15 ቀን 2008 ዓም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማዕከል ሊያካሂድ አቅዶት የነበረውን ዐውደ ራዕይ በልዩ ልዩ ተልካሻ ምክንያትና ሰበብ እንዳይካሄዱ ካደረገ  ወዲህ ማኅበሩ ጉዳዩን በቅርብ በመከታተል ባደረገው ጥረት ዐውደ ራዕይ እንዲካሄድ ወያኔ የፈቀደ መሆኑ ተገልጿል። ፈቃዱ እንደገና ተሰጥቷል ይባል  እንጅ በተባለበት ቀንና ጊዜ ለምን እንደተከለከለና ማን እንደከለለከለ ወያኔ የሰጠው ምንም ዓይነት መግለጫ የለም። የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች አሁን ፈቃድ መገኘቱን ይናገሩ እንጅ ዕውደ ራዕዩ መቼና የት እንደሚካሄድ ገና በንግግር ላይ መሆናቸውን አልሸሸጉም።  የማኅበረ ቅዱሳን ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምሮትን  ድርሻችንን እንወቅ በሚል ርዕስ ዐውደ ጥናት አዘጋጆችን ዝግጁነቱን አጠናቆ ባለበት ሰዓት በወያኔ መሪዎችና ከፓትርያርኩ ጽ/ቤት ባሉ ሰዎች አማካኝነት መታገዱን በማስታወስ አሁንም የማኅበሩን ዓላማ ተሳክቶ ዐውደ ራዕዩ ተግባራዊ እስካልሆን ድረስ የወያኔ ሸርና የካባ ለባሽ ካድሬዎቹ ተንኮልን በተጠንቀቅ መጠበቅ ይገባናል ይላሉ።

 

 

Ø ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓም በኮንጎ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ በብራዛቪል ከፍተኛ የጥይትና የከባድ መሳሪያ ድምጽ ሲሰማ መቆየቱን ነዋሪዎች ለዜና ምንጮች ካስተላለፉት መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ማከለከሌ በተባለው ቀበሌ አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ ክፍሎች በአንድ የፖሊስ ጣቢያና በአንድ የመንግስት ህንጻ ላይ ጥቃት የፈጸሙ መሆናቸው ተነግሯል። የሬውተር የዜና ምንጭ በዘገባው እንደገለጸው የተቃዋሚ ደጋፊዎች የሆኑ ወጣቶች በአንዳንድ ቦታዎች “ ሳሱ ሥልጣን ልቀቅ” የሚል መፈክር ደጋግመው ሲያሰሙ እንደነበር ገልጿል።  ከ1971 ዓም ጀምሮ በሥልጣን ላይ የነበሩት ዴኒስ ሳሱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአገሪቱ በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ በድጋሚ ለሌላ አምስት ዓመታት የስልጣን ዘመን መመረጣቸውና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ አይደለም  በማለት መቃወማቸው ይታወቃል። በዛሬው ግጭት ፖሊሶች  ከታጠቁ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ የነበሩ መሆናቸው የዜና ምንጮች የዘገቡ ሲሆን ይኸው ታጣቂ ቡድን የኒንጃ ሚሊሺያ ቡድን ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ይሰጣሉ።

 

Ø 16 000 አባላት ያሉት የደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ሠራዊት ማህበር ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንቱ የሠራዊቱ ጠቅላይ አዛዥ ለመሆን ብቃት ስለሌላቸው ስልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው ብሎ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት የማህበሩን ውሳኔ በመቃወም የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይል አዛዥ ውሳኔው ለእርስ በርስ ግጭት የሚጋብዝ ከመሆኑም በላይ ህገወጥ ነው ብለውታል። ተቃዋሚዎች የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሚስተር ዙማ በስልጣን መባለግ ተከሰው ከስልጣን እንዲወገዱ ያቀረቡት ጥያቄ ማክሰኞ መጋቢት 27 ቀን በምክር ቤቱ ላይ ቀርቦ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ ፓርቲ አብዛኛውን መቀመጫ በመያዙ በተቃዋሚዎች የቀረበው ሀሳብ ውድቅ ይሆናል ተብሎ ተገምቷታል። በሌላ በኩል የጸረ አፓርታይድ ትግል መሪና ከሚስተር ኔልሰን ማንዴላ ጋር በሮበን ደሴት ታስረው የነበሩት እውቁ አህመድ ካታራዳ ሚስተር ዙማ ከስልጣን መልቀቅ አለባቸው ብለዋል። ባለፈው ሳምንት ሚስተር ዙማ የተፈጸመው ስህተት ሆን ተብሎ የተደረገ አለመሆኑን ጠቅሰው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል።

 

Ø ከአልካይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለውና አንሳሩ እየተባለ የሚጠራውን የጂሃዲስት ድርጅት ይመራ የነበረና በአሜሪካ መንግስት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈለግ የቆየው ካሊድ አል ባርናዊ የሚባለው ግለሰብ በናይጄሪያ ውስጥ የተያዘ መሆኑ ተነገረ። ከአራት ዓመት በፊት አሜሪካ ግለሰቡን ዋና አሸባሪ ብሎ የሰየመ ሲሆን ግለሰቡን ለያዘ ወይም ለገደለ አምስት ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መዘጋጀቱን  ገልጾ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ከቦኮ ሃራም የተገነጠለውን ድርጅት አንሳሩን ይመራ የነበረው ካሊድ ባርናዊ በተለያዩ ጊዜያት በርከት ያሉ የውጭ አገር ሰዎችን በመግደል የሚጠረጠር ሲሆን ከአራት ዓመት በፊት በናይጀሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ውስጥ ባለው ዋና እስር ቤት ላይ የተደረገውን ጥቃት አስተባበሮ በርካታ እስረኞች ያስፈታ መሆኑ ይነገርለታል።

 

Ø የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ትናንት መጋቢት 25 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ በሱዳን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በዚህ ዓመት ወደ 400 000 (አራት መቶ ሺ) የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልጿል። ድርቁ የተከሰተባችው አካባቢዎች ምስራቅ ሱዳን በምስራቅ ዳርፉር እና  በመካከለኛው ኮርዶፋን ግዛት ሲሆን በድርቁ የተጎዳው በጠቅላላው 3.8 ሚሊዮን ሕዝብ የተለያየ እርዳታ ሲደርግለት መቆየቱ ተነገርዋል። የምግብ እርዳታው በዚህ ዓመት በጠቅላላው 12.5 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑ ቃል አቀባዩ ገልጾ በጦርነት የተፈናቀሉትን ከመርዳቱ ጋር ተዳምሮ የበጀት ችግር ሊገጥም እንደሚችል ጠቁሟል።     

  

 

 

 

መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓም

 

Ø ዘረኛነትና አድልዎ ታማኝነትና ቡድናዊ አሠራር በተለመደበት የወያኔ ሥርዓት ውስጥ ለትግራይ ተወላጆች ልዩ እንክብካቤና ጥቅም እንዲያገኙ መደረጉ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል። በቅርብ ከሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. እስከ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ድረስ ባህርዳር ከተማ ለሚደረገው የጣና ፎረም የአፍሪካ እምባገነን መሪዎችና የታዋቂ ግለሰቦች ስብሰባ የወያኔው ደህንነት መስሪያ ቤቱ ለጥበቃ የትግራይ ተወላጆችን በብዛት መምረጡ ታውቋል። ይህ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ይደረጋል በተባለው ስብሰባ ለጥበቃ የሚሰማሩ አባላት ጠቀም ያለ ገንዘብና አበል የሚከፋል በመሆኑ የትግራይ ደህነነት አባላት በብዛት ተመርጠዋል። የድህንነት ምንጮች የትግራይ ተወላጆቹ በብዛት የተመረጡት ጥቅም እንዲያገኙ ብቻ ሳይሆን የአማራና የኦሮሞ ደህንነት አባላት ታማኝነታቸው አጠራጣሪ በመሆኑ ነው። የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ያሉበትን የጣና ፎረም ስብሰባን የቀደሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሲንጎ ኦባሳንጆ ይመሩታል ተብሏል።

 

Ø በአዲስ አበባ ከተማ የስራ አጥነት ማስረጃ ለማግኘት የአምስት ቀን ስልጠና መውሰድ ግዴታ ነው ተባለ። ማስረጃውን የሚሰጠው የሚኖሩበት ቀበሌ ሲሆን እስከ ዛሬ ይሰራበት ከነበረው አሠራር የተለየ መሆኑንና ስራ አጡ ስራ ካገኘ በሰለጠነበት ካልሆነ አትሰራም ተብሎ እንደሚከለክልና እሰራለሁ ካለ ከቀበሌው ማስረጃ እንዲያቀርብ ይጠየቃል። ይህ የስራ አጥ ስልጠና የተባለውን ለወያኔ የገንዘብ መሰብሰብያ ድርጅቶች ስራ የፈጠረ ከመሆን ውጭ ለአዲስ አበባ ስራ አጦች የፈየደው ነገር አለመኖሩንም እንዲያውም የሥራ ዕድሉ ያገኙ ወጣቶች አንተ በዚህ ሙያ አለሰለጠንክም አንተ ለዚህ አትመጥንም እየተባሉ የሥራ ዕድሉን ከማጥበብ ውጭ የሰጠው ጠቀሜታ እንደሌለ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በከተሞች ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥ ቁጥር ያለ ሲሆን ወያኔ በሚከተለው ዘረኛና አምባገነን አድላዊ አገዛዝ ምክንያት ስራ የማግኘት ዕድል በእጅጉ እንደጠበበባ ተወላጅነትና የፖለቲካ ታማኝነት ዋና መስፈሪያ መሆኑ ይታወቃል።

 

Ø በአባይ ወንዝ አጠቃቀምና በአባይ ግድብ ዙሪያ ወያኔና ግብጽ ያላቸውን ልዩነት ለማቻቻል ተደጋጋሚ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እየገለጸ ባለበት ሰዓት የወያኔ አገዛዝ የዓባይ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ 6000 ሜጋ ሞት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመርቱና 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሃ ሊይዝ እንደሚችል እየገለጹ ነው። የወያኔ መሪዎች ግድብ ሲጀመር 5250 ሚጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመርታል ይበሉ እንጅ አሁን ቁጥሩን ከ6000 በላይ ማለታቸው ታውቋል። ግድብ ከኃይል ማመንጫነት በተጨማሪ ለመስኖ ለዓሣ እርባታና ለትራንስፖርት ይውላል ይበሉ እንጅ የግብፅ መንግስት ግድብ አሁንም በታሪካዊ የዓባይ ወንዝ ውሃ አጠቃቃሜ ላይ ችግር ይፈጥራል በማለት ተቃውሟውን በማሰማት ላይ ይገኛል። የቀድሞዎቹ የግብጽ ፕሬዚዳንቶች በአባይ ግድብ ላይ ወታደራዊ ኃይል መጠቀም እንደአማራጭ እንደሚወስዱት መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ግብጽ መሪዎች የበለጠ ለዲፕሎማሲ ለሕግና ለቴክኒካል ኮሚቴ ጥናት ጊዜ ይሰጡ እንጅ የከረረ ፍትጫ ውስጥ እንደሚገባ የማይቀር መሆኑ ይነገራል። ወያኔ ስለ አባይ ግድብ ተጨማሪ ፕሮፓጋንዳ ለመንዛትና በተለይ ከውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵይውያን ገንዝብ ለመሰበብ ግድብ የተጀመረበት አምስተኛ ዓመት በማለት ስብሰባ ለመጥራት ማቀዱ ተገልጧል።

 

 

Ø በሶማሊያና በኬኒያ ወሰን አካባቢ  ጂብ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የአሜሪካው ወታደራዊ ተቋም  ሰው አልባ መንኮራኩርን በመጠቀም  ሶስት የአልሸባብ መሪዎችን ይዟል የተባለ ተሽከርካሪን በማጥቃት የደመሰሰ መሆኑን አንድ የፔንታጎን ቃል አቀባይ ገልጿል። በተሽርካሪው ውስጥ ነበረበት ተብሎ የሚጠረጠረውና ለመግደል ኢላማ የተደረገው ሃሰን አሊ ዳሁር የተባለው የአልሸባብ መሪ ሲሆን ግለሰቡ በቅርቡ በሱማሊያ ውስጥ አሜሪካውያንን ጨምሮ በርከት ያሉ ሰዎች የገደሉትን  የቦምብ ጥቃቶች ሲያደራጀና ሲያስተባብር  የቆየ ነው ተብሏል። የተወሰደው እርምጃ  ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ቃል አቀባዩ  ገልጾ  ግምገማ እያካሄደ መሆኑን አብራርቷል።

 

Ø በተያያዘ ዜና ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓም  በኬኒያ ከአንደ ዓመት በፊት በጋሪሳ ዪኒቨርስቲ በአልሸባብ  ታጣቂዎች የተገድሉትን 148 ተማሪዎች ሌሎች ሰራተኞች ለማስታወስ የተለያዩ ስነስርዓቶች ሲደረጉ ውለዋል። በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰብስበው የሞቱትን ያስታወሱ  ሲሆን  በኬኒያ ዋና ከተማ በናይሮቢ የተገደሉትን ለማስታወስ የጸሎትና የሻማ መብራት ሥነ ስርዓቶች የተካሄዱ መሆናቸው ታውቋል።

 

Ø የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ትናንት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓም በቴሌቪዥን አማካይነት ለሕዝቡ ባደረጉት ንግግር በቅርቡ የግል መኖሪያ ቤታቸውን ለማሻሻል የተደረገው ግንባታ  በርካታ ውዝግብ ማስነሳቱን ገልጸው ለተፈጠረው ሁኔታ በይፋ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋል። የደቡብ አፍሪካ የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ የሚቀበሉ መሆኑን ገልጸው ለመዋኛ ቦታና ለቲያትር መመልከቻው ሕንጻ የወጣውን ወጭ እንደሚከፍሉ ቃል ገብተዋል። ለዚህ ጉዳይ የተቋቋመ አንድ የጸረ ሙስና ተቋም የተጠቁስትን ሕንጻዎች ለመገንባት ከመንግስት ካዝና 23 ሚሊዮን ዶላር የወጣ መሆኑን ገልጾ ሚስተር ዙማ ይህንን ገንዘብ መክፈል ያለባቸው መሆኑን በማስረገጥ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወቃል።  በሚስተር ዙማ በኩል ገንዘቡን ለመክፈል ፈቃደኛነት ባለመገኘቱ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ የደቡብ አፍሪካ የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት  ባለፈው ሐሙስ ሚስተር ዙማ የተጠቀሰውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። በሌላ በኩልም ሁለት ዋና ዋና የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምክር ቤቱ ሚስተር ዙማ በስልጣን መባለግ ክስ ወንጅሎ ከስልጣን እንዲያባርራቸው አጀንዳ አስይዘው ውይይት እየተካሄደበት ነው። የሚስተር ዙማ የቴሌቪዥን ንግግር  ስልጣኔ በፈቃዴ ለቅቄያለሁ ሲሉ ለመስማት ጠብቆ የነበረውን ክፍል ያበሳጨ ቢሆንም ሚስተር ዙማ አሁንም ቢሆን ለምን ያህል ጊዜ በሥልጣን ይቆያሉ የሚለው ጥያቄ አሁንም አነጋጋሪ ሆኗል። ገሚሱ ሚስተር ዙማ በማጭበርበርና በማሳዘን የሕዝብን አስተያየት በማስቀየር በኩል የተካኑበት መሆኑን በተደጋጋሚ ያሳዩ በመሆናቸው በቅርቡ የተፈጠረውን ሁኔታ በተመሳሳይ መልክ ይወጡታል ሲል በአሁኑ ወቅት በፕሬዚዳንት እየተካሄደ ያለው ሙስናና ዓይን ያወጣ የዘመድ ስራ ይፋ በመውጣቱ ከዚህ ችግር የሚወጡበት መንገድ ጠባብ ነው የሚል ግምት የሚሰጡ በርካታ ናቸው።  ክፍሎች

 

Ø በኮንጎ በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ተመድበው የሚሰሩት የታንዛኒያ ወታደሮች በእድሜ አነስተኛ የሆኑ ህጻናትን አስገድደው ደፍረዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው መሆኑ ተገልጿል። ወንጀሉን ፈጽመዋል የተባሉት  ማቪቪ በተባለው መንደር አካባቢ የተሰማሩ የታንዛኒያ ወታደሮች ሲሆኑ ክሱ የተረጋገጠ ከሆነ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ለታንዛኒያ እና ለኮንጎ መንግስት ባለስልጣኖች መረጃው መተላለፉን የተመድ ቃል አቀባይ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ከካምፕ እንዳይወጡ የተደረገ ሲሆን በደል ለደረሰባቸው ህጻናትም የስነ ልቡናና የማህበረሰባዎች ርዳታዎች እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል። የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና በኮንጎ ተመሳሳይ ክሶች ሲቀርቡባቸው መቆየቱ አይዘነጋም።

 

Ø በትናንትናው ዕለት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓም ሲካትሴሬ በተባለችው የናይጄሪያ ሰሜናዊ ግዛት ከተማ ከሶስት ወር በላይ አለምንም ፍርድ በግፍ የታሰሩት የሺያ ሃይማኖት ተከታይ መሪ ሚስተር ዛክዛኪ ከእስር እንዲፈቱ ሰላማዊ ስልፈኞች አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት አንድ  የኮሎኔልነት ማዕረግ ያለው የናይጀሪያ ወታደራዊ መኮንን  በሺያ ሃይማኖት ተከታዮች ቡድን ተጠልፎ ከተወሰደ በኋላ ተገድሏል የሚለውን ክስ  ቡድኑ መካዱ ይታወቃል። የሺያ ሃይማኖት መሪ በቁጥጥር ስር የዋሉት በዚህ ዓመት ታህሣር ወር ውስጥ ሲሆን ለመታሰራቸው ምክንያት የሆነው የእምነቱ ተከታዮች አንድ የናይጄሪያ ጄኔራል ጠልፎ ለመያዝ መከራ አድርገዋል በሚል ነው። በወቅቱ በአካባቢው የነበረው የናይጄሪያ ወታደር ሶስት የሺያ መስጊዶችን  የደመሰሰ ሲሆን መሪውን ዛክሳኪን በሥስት ጥይት አቁሰለው ከመያዛቸውም በላይ የዛክዛኪን ልጆች ጨምሮ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ይታወቃል። የናይጄሪያ ፍርድ ቤት አንድ ተጠርጣሪ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት ብሎ ቢያዝም ከሶስት ወር በላይ የተቀመጡ መሆናቸው ታውቋል። ዛክዛኪ ከ 37 ዓመት በፊት ከኢራን ጎብኝተው ሲመለሱ የመሰረቱት የሺያ ሙስሊም ሃይማኖት በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታዮች ቢኖሩትም በአካባቢው ከሚኖሩ የሱኒ ሙስሊም አባሎች ጋር ሲወዳደር በቁጥር አነስተኛ በመሆናቸው ከፍተኛ በደል የደረሰባቸው መሆኑ ይታወቃል። ባለፈው ሳምንት የሺያ ሃይማኖት እንቅስቃሴ የሚባለው ድርጅት በአካባቢው ከ 1000 ሰዎች በላይ ሰዎች በመገደላቸው በዐለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

 

 

 

 

መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø በትናንትናው ዕለት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓም ደብረ ዘይት ውስጥ አዋሽ በተባለ ሆቴል ውስጥ የተወረወረ የእጅ ቦምብ አንድ ሕጻን ገድሎ ሌሎች አራት ሰዎችን በጽኑ ማቁሰሉ ታውቋል። የቦምቡን ፍንዳታው ተከትሎ የወያኔ ጸጥታ ኃይሎችና ወታደሮች ደብረዘይትን አስጨንቀዋት እንደሚገኙ ተገልጿል። የዓይን ምስክሮች የእጁ ቦምብ አንድ ግለሰብ እንደወረወረውና እነደተሰወረ ሲገልጹ ለፍንዳታው ኃላፊነትን የወሰደ ግለሰብም ሆነ ቡድን የለም። ብዙ ሀገር ወዳድ ዜጎች ግን በመላ ኢትዮጵያ ከተሞች በደብረዘይትም ጭምር ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ጋር በተያያዘ የወያኔ የፀጥታና የደህንነት ኃይሎች የጣሉት አደጋ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ድርጊቱን የፈጸሙትም የሕዝብ ወገንና ልጆችን ለማሰር የተሸረበ ሴራ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ግምትና ጥርጣሬ እንዳላቸው ይናገራሉ። የወያኔ ባለሥልጣናትም ሆነ የደብረ ዘይት ከተማ ሹማምንት የቦምብ አደጋውን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት የሰጡት መግለጫ አለተመዘገበም።

 

Ø መቀመጫውን እንግሊዝ አገር ያደረገው ላንሴት የህክምና ጆርናል የዘንድሮውን የሰውነት ክብደትና ይዘት መለኪያ (Body Mass Index) ይፋ አድርጓል። ሰንጠረዡ እንደሚያሳየው የዓለም ሕዝብ ውፍረት በአስደንጋጭ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን ገልጿል። በ1967 በተደረገው ተመሳሳይ ጥናት 105 ሚሊዮን ሕዝብ ወፍራም ተብሎ እንደተፈረጀና ባለፈው ዓመት የተጠናቀቀው ና በ200 አገሮች በተካሄደው ጥናት 647 ሚሊዮን ሕዝብ ወፍራም መሆናቸው አስደንጋጭ ነው ተብሏል። ወፍራም የተባሉት አብዛኞቹ የሚገኙት በበለፀጉና ሀብታም በተባሉ አገሮች ውስጥ ሲሆን አሜሪካ ወፍራሞችን በብዛት በማስመዝገብ ቀዳሚነቱን ስታሳይ ጃፓን ደግሞ የበለጸገችና ሀብታም ሆና የወፍራሞችን ቁጥር አነስተኛ ቁጥር አነስተኛ የሆኑባት አገር ሆናለች። ከአሜሪካ ቀጥሎ አውስትራሊያ፣ ካናዳ ፣አየር ላንድ፣ኒውዚላንድና ብሪታኒያ ወፍራሞችን በብዛት እንደቅድመ ተከተላቸው ያስመዘገቡ ሲሆን በቀጫጫነት ደግሞ ምስራቅ ቲሞር ኢትዮጵያና የሻዕቢያዋ ኤርትራ አነስተኛ ቁጥር ያለው ወፍራሞችን አስመዝግበዋል፡፤ የሕክምና ባለሙያዎች ወፍራምነትን ተከትለው የሚመጡ በርካታ የጤና ችግሮች መኖራቸውን በመግለጽ ተመጣጣኝ የሰውነት አቋም  ከክብደትና ከቁመት ጋር እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አነስተኛ ክብደት መኖርም ለጤንነት አስጊ መሆኑን ይገልጻሉ። የሰውነት ክብደት የሚያሰጋቸው ሰዎች ከመጡበት አካባቢና ከኑሮ ደረጃቸው ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችልም ይገመታል።

 

Ø የወያኔ ቡድን ጠፍጥፎ የሠራው ብአዴን የተባለው ቡድን እወክለዋለሁ በሚለው የአማራ ሕዝብ ላይ በየወቅቱና በየጊዜው አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊቶችን ሲፈጽም መቆየቱ ይታወቃል። ሰሞኑን ደግሞ የወልቃይት ሕዝብ ለማንነቱና ለመብቱ ያነሳውን ጥያቄ በግድያ በአፈናና በእስር ምላሽ እየሰጠ ባለበት ሰዓት በሁመራ የሃይማኖት አባቶች የተባሉት የወልቃይትን ነዋሪ ሃሳብ እንዲቃወሙ ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል። የሃይማኖት አባት የተባሉት ስብሰባ የተጠሩት የወልቃይት ሕዝብን እንዲያወግዙ መሆኑ ተገልጿል። የወያኔው ተላላኪ ብአዴን ለወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ የወያኔን ነፍሰ ገዳይ ጦር አግአዚ በመጥራት የጥይት ምላሽ ሲሰጥ የውግዘትና የተቃውሞ ድምጻቸውን ያላሰሙት የሃይማኖት አባት የተባሉት ዛሬ ከወያኔ ጋር በመሆን ለውግዘት መሰልፋቸው የሃይማኖት አባት የሀገር ሽማግሌ ሳይሆኑ ተራ ተላላኪ መሆናቸውን አሳይተዋል። የጎንደር ነዋሪዎች የሃይማኖት አባቶቹ ከወያኔ ጎን በመቆም ይህን ዓይነት ወራዳና ሕዝብ የሚጎዳ ተግባር መፈጸማቸው ከሃይማኖት አባት የማይጠበቅ የተራ ቀበሌ ካድሬ ስራ ነው በማለት ለመብትና ለማንነት የሚደርገው ትግል ይቀጥላል ይላሉ።

 

Ø የወያኔው የንግድ ሸሪክ የሆነው መሀመድ አላሙዲን ቤት ከዓመታት በፊት ግዥ የፈጸመባቸውን የንግድና የእርሻ ድርጅቶች ክፍያን በወቅቱ ባለመፈጸሙ ወደ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ብር እንዲከፍል በወያኔው ፍርድ ተፈርዶበታል። ወያኔ የመንግስትና የሕዝብ ሀብት የነበሩትን ጎጀብ  እርሻ ልማትን፤ አዲስ ጎማን የሊሙና የበበቃ የቡና እርሻን ለመሀመድ አላሙዲ ሜድሮክ ኩባንያ መሸጡ ይታወሳል። መሀመድ አላሙዲ የልማት እርሻዎቹን ሆርዘን ፕላንቴሽን በማለት ስያሜ ሰጥቶ ክፍያ ግን ባለመፈጸሙ ጊዜ ቢሰጠውም በገንዘብ ቀውስ ሊከፍል አለመቻሉ ታውቋል። የወያኔው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ችሎት ጉዳዩን ለወራት መርምሮ የልማት እርሻዎቹ ባለንብረት መሀመድ አላሙዲን ድርጅቶቹ ያላቸውን አጠቃላይ ዕዳ 433 ሚሊዮን 571 ሺህ 241 ብር በጊዜ ገደብ እንዲከፍል ካልከፈለ ከነወለዱ እንዲከፍል ወስኗል። የፖሊካ ተመልካቾች የወያኔ የፖለቲካ ፍርድ ቤት በወያኔ የንግድ ሸሪካ ላይ ይህን ውሳኔ የጣለው በቱጃሩና በውያኔ መካከል ያለው ፍቅር አልቆ ነው ወይስ ስግብግብና አልለጠግብ ባይ የሆኑት የወያኔ መሪዎች ውትሮችም በዘዴና በስልት የሰጡትን የሀገርና የሕዝብ ንብረት በህግና በፍርድ ቤት ስም ሊቀበሉት በማሰብ ነው በማለት ይጠይቃሉ።

 

 

Ø በህንድ አገር ካልከታ ከተማ ውስጥ ከመንገድ በላይ የተሰራ አንድ ድልድይ በመደርመሱ ከ 24 ሰዎች በላይ ሞተው በርካታ የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል። ከተደመረሰው ድልድይ ስር ያሉትን ሰዎች ለማውጣት አስቸጋሪ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ሊሞቱ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆኑ እንደሚችል ተሰግቷል። እስከ ዛሬ ድረስ 90 የሚሆኑ ሰዎችን ከተደረመሰው ድልድይ ስር በማውጣት ለማዳን የተቻለ ሲሆን አብዛኞቹ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተልከዋል።  2 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ድልድይ ከተጀመሩ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የተደረመሰው በግምባታ ጥራት ጉድለት ነው ይባላል። ፖሊስ ድልድዩን ሲሰራ የነበረው ኩባንያ ኃይላፊዎችን በቁጥጥር ያደረገ ሲሆን በወንጀል ክስ የሚመሰርትባቸው መሆኑን ገልጿል። በአገራችንም አብዛኞቹ መንገዶች ድልድዮችና ህንጻዎች የሚሰሩት ጥራታቸውን ባልጠበቀ ሲሚንቶና ሌሎች የህንጻ መሳሪያዎች መሆኑን በመናገር እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ዓይነት ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች  ከተከሰቱ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ለጉዳዩ እውቀት ያላቸው በርካታ መሀንዲሶች መምከር ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል።

 

Ø የሊቢያ የአንድነት መንግስት ተቀባይነት አግኝቶ ሁኔታውን መቆጣጠር ከቻለ ሊቢያ የተያዘባት የአገሪቱ ገንዘብ ወዲያውኑ ሊለቀቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። ላለፉት አምስት አመታት 67 ቢሊዮን ዶላር የአገሪቱ ገንዝብ እንዳይነቃነቅ በተመድ የተያዘ መሆኑ ይታወቃል። ባለፈው ረቡዕ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓም ትሪፖሊ ወደብ የገባው በተመድ ግፊት የተቋቋመው የሊቢያ የአንድነት መንግስት በከተማው ውስጥ ተኩሶች በመበርከታቸው እና የጸጥታው ሁኔታ ያልተረጋጋ በመሆኑ ምክንያት  ከወደቡ አካባቢ በመውጣት ወደ ሌሎች የከተማዋ ክፍሎች ያልተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል።  በትሪፖሊ የራሱን መንግስት ያቋቋመው አካል  መሪ ካሊፋ ገዊል በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ የውጭ መንግስት አስጠባቂና ሰርጎ ገብ የሆነው የአንድነት መንግስት የሚባለው አካል በእኛ አካባቢ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። አያይዘውም ወደ ትሪፖሊ የገቡት የአንድነት መንግስት የልኡካን ቡድን አባሎች ወይ እጃቸውን ለእኛ በሰላም ይስጡ ካለበለዚያም ይመለሱ የሚል መግልጫ ሰጥተዋል። በትሪፖሊም የአንድነት መንግስቱን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄደዋል።  ከአምስት ዓመት በፊት የጋዳፊ መንግስት ከተገለበጠ ጀምሮ በሊቢያ ምስራቅና ምዕራብ ሁለት ራሳቸውን መንግስት ነን ብለው የሚጠሩ የታጠቁ ክፍሎች መመስረታችው ይታወቃል። ባለፈው ታኅሳስ ወር በተመድ አማካይነት ከሁሉም የተውጣጣ መንግስት ለማቋቋም የተጠነሰሰው ሀሳብ በአንዳንድ ክፍሎች ስምምነት እንዲቋቋም ቢደረግም በምስራቅም ሆነ በምዕራብ የአንድነት መንግስቱን መቋቋም የሚቃወሙ ክፍሎች በማየላቸው መንግስቱ ተመስርቶ ሊንቀሳቀስ አልቻለም። ሰሞኑን ከዚህ ጋር በተያያዘ የአንድነት መንግስቱ እንዳይንቀሳቀስ እንቅፋት ሆነዋል ብሎ በሰየማቸው ሶስት የሊቢያ ባለስልጣኖች ላይ  የአውሮፓው ህብረት ማዕቀብ የጣለ መሆኑ ገልጿል። ማዕቀብ የተጣለባቸው ግለሰቦች አጊላህ ሳላህ በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘው መንግስት የፓርላማ መሪ፤ ካሊፋ ገዊል የትሪፖሊ መንግስት መሪ እና አቡ ሳህማን የጠቅላላ ብሔራዊ ኮንግሬስ መሪ መሆናቸውም ተነግሯል።  ሶስቱ ግለስቦች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ የተከለከሉ ሲሆን በአውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ገንዘብና ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ተጥሎበታል። የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት የአሁኑን የሊቢያን ሁኔታ ፈጥሯል የሚል አስተያየት የሚሰጡ  ወገኖች የጋራ ስምምነት እስከሌለ ድረስ የሊቢያ ቀውስ ይቀጥላል በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ።

 

Ø ከአስራ ሰባት ዓመት የስልጣን ጊዜ በኋላ የጅቡቲው ገለህ በሚቀጥለው ሳምንት መጋቢት 30 ቀን 2008  በሚካሄደው ምርጫ የሚመረጡ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው በማለት በርካታ ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ። የዛሬ ስድስት ዓመት ፓርላማው የጂቡቲን ሕገ መንግስት በመቀየሩ ምክንያት ገለህ ለሶስተኛ ጊዜ የተመረጡ ሲሆን የአሁኑ አራተኛው የስልጣን ዘመናቸው ይሆናል።  የተቃዋሚዎች ህብረት በአንድ ላይ ለመቆም ችግር ያለበት ቢሆንም ከሰባት ተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል ሶስቱ የታቀደው ምርጫ መሰረታዊ የሆነ የነጻና ፍትሃዊ ምርጫ መመዘኛዎች ያላሟላ የይስሙላ ምርጫ  ስለሚሆን አንሳተፍም ብለዋል። ነጻና ገለልተኛ የሆነ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ እንዲቋቋም የቀረበውን ጥያቄ የገለህ መንግስት ውድቅ አድርጎታል። ጅቡቲ ውስጥ አሜሪካ በየመን፤ በሶማሊያና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጸረ ሽብር ጥቃቶችን የምታስተባብርበት የጦር ማዕከል ሲኖራት ፈረንሳይ፤ ጃፓን እና ቻይናም ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች የመሰረቱ መሆናቸው ይታወቃል። አገሪቱ ባለፉት አመታት የኢኮኖሚ እድገት አሳይታለች ተብሎ ብዙ ቢወራላትም በአግሪቱ ውስጥ የስራ አጡ ቁጥር 60 ከመቶ የደረሰ ከመሆኑም በላይ ቢያንስ አንድ አራተኛ የሚሆነው የጂቡቲ ሕዝብ በከፍተኛ ድህነት ክልል እንደሚኖር ይታወቃል።  

 

Ø ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓም የተባበሩት መንግስት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት 100 የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይል አባላት  በብሩንዲ ስላም ለማስከበር ስለሚሰማሩበት ሁኔታ በፈረሳይ መንግስት በቀረበው ረቂቅ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጥበታል ተባለ። ቁጥራቸው ከ100 የማይበልጥ ፖሊሶች ወደ ጅቡቲ ተልከው በብሩንዲ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር ስለሚቻልበት ሁኔታ እርዳታ ያደርጋሉ ተብሏል። በብሩንዲ የእርስ በርስ ግጭት ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎች በገፍ የሚገደሉበት፤ የሚያዙበትና ተይዘውም በምርመራ ከፍተኛ ስየል የሚካሄድባቸው የዜና ምንጮችና የተመድ ባለስልጣኖች በየጊዜው መግለጻቸው ይታወቃል።  በቀረበው ሀሳብ መሰረት 100 ፖሊሶችን ለመላክ የታቀደ ሲሆን ጸጥታን ለማስከበር ቁጥሩን እንደማይበቃ ብዙዎች ይናገራሉ። የብሩንዲ ችግር በጀመረ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ400 በላይ የብሩንዲ ዜጎች ሲገደሉ ከ12 000 ሰዎች በላይ እንደተሰደዱ ተዘግቧል። 

 

 

 

 

መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø በኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች ውስጥ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ ዛሬም በልዩ ልዩ ከተሞች በተለያየ ማዕዘናት ውስጥ ውስጡን እንደቀጠለ መሆኑን ከየአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በምዕራብ ሐረርጌ ፈዲስ ወረዳ አሁንም ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ እየፋመ ሲሆን የወረዳ ገዥ የተባለውን ሕዝብ አባሮታል። በአርሲ በተለያዩ ከተሞች የተማሪዎች ተቃውሞ እንደ አዲስ የተቀሰቀሰ ሲሆን የወያኔ ቡድን መሪዎች ነፍስ ገዳይ ጦራቸውን አግአዚንም ቢልኩ ሞት ያልፈሩ ወጣቶችና ሕዝብ በመጋፈጣቸው ውጥረቱ ከፍተኛ ሆኗል። በኢሊባቦርም ሕዝቡና ተማሪዎች በአንድ ላይ በመሆን የታሰሩት እንዲፈቱ የወያኔ ነፍሰ ገዳይ ጦር ከከተሞችና ከገጠር ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ተቃውሟቸውን በአደባባይ እየገለጹ መሆናቸው ታውቋል። የወያኔ ቡድን የሚዘሯቸው መገናኛ ብዙኀን የሕዝብ ተቃውሞና ቁጣ ወያኔ በሰጠው መልስ ተደስቶ ተቃውሞ ጠፍቷል፤ በርዷል በማለት ራሳቸውን ብቻ የሚያሞኝ ፕሮፓጋናዳ ይንዙ እንጅ የተቃውሞ ትግሉ በየአቅጣጫውና በየማዕዘኑ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

 

Ø የያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ከማለቁ በፊት የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከሀገሩ እንደሚያባርር አስታውቋል። የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ 11 ሺ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለማባረር ማቀዱን የገለጸ ሲሆን ስደተኞቹን ለማባረር የሚያስተባብርና የሚያቀናብር አዲስ የሚመጡትንም የሚቀበልና የሚያስተናግድ ግብረ ኃይልም አቋቁሟል። የፈረንሳይ መንግስት ለጊዜው ከሶሪያ ከኢራቅና ከሻዕቢያ ኤርትራ የሚመጡ ስደተኞችን ብቻ ለመቀበል መወሰኑ ታውቋል። በኢትዮጵያ የኦስትርያ አምባሳደር APA ለተባለ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለ ምልልስ በአውሮፓ ጥገኝነት ከጠየቁ ኤርትራውያን ውስጥ 40 ከመቶ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተናግረዋል። አምባስደሩ አያይዘውም በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ አረቢያና ደቡብ አፍሪካ እንደሚገቡ ገልጸው ወደ አውሮፓ የሚመጡ ስደተኞች ግን የፖለቲካ ጥገኛነት ለማግኘት የተሻለ ዕድል እንዲያገኙ ኤርትራውያን ነን እንደሚሉ ተናግረዋል። ማንም ብዙ ያላወራለት በዓመት ከ 100 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ መካከለኛ ምስራቅ መሄዳቸውንም ገልፀዋል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስደተኛ የተቃዋሚ ፖሊቲከኛ በአውሮፓ ጥገኛነት እንደማይሰጠው አምባሰደሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያውያን መከራና ስቃይ የሚያውቅና የሚቀበል እየጠፋ መምጣቱ የሚያሳየው መከራና ስቃይ በስደት የሚከተል ከሆነ በሀገር ውስጥ የመከራና የስቃይ ምንጩን የወያኔ አገዛዝን መታገል ብቸኛ መፍትሔ ነው የሚሉ ወገኖች በዙ ናቸው።

 

 

Ø የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የሰብዓዊ መብት፣ የዴሞክራሲና የሠራተኛ ጉዳይ ረዳት ኃላፊ የሆኑት ቶም ማሊኖውስኪ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል። ረዳት ኃላፊው ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓም በአዲስ አበባ መግባታቸው ሲታወቅ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ በሩዋንዳ ብሩንዲና ኬኒያ እንደሚያደርጉ ከወያኔ መሪዎችና ባለሥልጣናት ጋርም እንደተነጋገሩ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ከሲቪክ ድርጅት መሪዎች ጋርም ንግግርና ምክክር ማድረጋቸው ታውቋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ረዳት ኃላፊ የኢትዮጵያ ጉብኝት ባለፈው ሐምሌ ወር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ አቦማ በኢትዮጵያ ካደረጉት ጉብኝት ጋር የተያያዘና ቀጣይነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ተነግሯል።

 

Ø የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሚስተር ዙማ ከጥቂት ዓመታት በፊት በገጠር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የመዋኚያ ቦታ እና ሲኒማ የመመልከቻ ትልቅ አዳራሽ እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስፈልጉ  ግንባታዎች ለመስራት  የተጠቀሙበትን የመንግስት ገንዘብ ባለመመለሳቸው የሕገ  መንግስቱን ደንብ ጥሰዋል በማለት የአገሪቱ የመጨረሻው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈረደ መሆኑ ተገልጿል።  ፍርድ ቤቱ ቢያንስ የተወሰነውን ገንዘብ ፕሬዚዳንቱ መመለስ ያለባቸው መሆኑን የተጠቀሰ ሲሆን ምን ያህል መክፈል እንዳለባቸው የአገሪቱ ግምጃ ቤት እስከሚቀጥለው ሁለት ወራት ድረስ ወስኖ እንዲያስታውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከሁለት ዓመት በፊት የደቡብ አፍሪካ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ፕሬዚዳንቱ የገጠር ቤታቸውን ለማሻሻል የተጠቀሙት ገንዘብ 23 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን ገልጾ ቢያንስ የተወሰነውን ገንዘብ ለመንግስት መመለስ እንዳለባቸው መውሰኑ ይታወሳል። ክሱን የመሰረቱት ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተደሰቱ መሆኑን ገልጸው በምክር ቤቱ ላይ ፕሬዚዳንቱ ክስ ቀርቦባቸው ከሥልጣን እንዲነሱ ለማድረግ ጥረታቸውን የሚቀጥሉ መሆኑን  ገልጸዋል።

 

Ø በብሩንዲ ታስረው የነበሩት የቀድሞ የሩዋንዳ ሚኒስትር እና አምባሳደር በእስር ላይ እንዳሉ መሞታቸው ተገለጸ። ስለአማሟታቸው ከብሩንዲ መንግስት በኩል የተሰጠ ይፋ መግለጫ ባይኖርም  ግለስቡ የሞቱት በእስር ቤት ውስጥ ባለው ሆስፒታል በደረሱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ መሆኑን በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ተናግረዋል።  የብሩንዲ የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር እና አምባሳደር የነበሩት እኚህ ግለሰብ ከሩዋንዳው እልቂት በፊት በብሩንዲ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን ከዚያ በኋላ በየጊዜው ወደ ብሩንዲ ይመላለሱ እንደነበር ይታወቃል። ባለፈው ታህሣስ ወር በስለላ ጉዳይ ተጠርጥረው ከተያዙ በኋላ ጉዳዮቸው ወደፍርድ ቤት አለመቅረቡ ብዙ ወገኖችን ሲያሳስብ ቆይቷል። ሩዋንዳ የብሩንዲ መንግስት አማጽያንን ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠች ወደ ብሩንድ ትልካለች የሚል ክስ የብሩንዲ መንግስት በተደጋጋሚ ካቀረበ በኋላ በሩዋንዳና በብሩንዲ መካከል ያለው ግንኙነት እየተበላሸ መጥቷል። የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ለዜና ምንጮች በሰጠው መግለጫ ግለሰቡ ቀደም ብሎ የተያዙትም ከህግ ውጭ ሲሆን አሁን በድንገት መሞታቸውም ብዙ ጥያቄዎችን የሚያነሳ መሆኑና የብሩንዲ መንግስት ባስቸኳይ መልስ መስጠት ያለበት መሆኑን ገልጿል።

 

v ረቡዕ መጋቢት 21 ቀን 2008 በናይጀርና በናይጄሪያ ወሰን አካባቢ ቦኮ ሃራም ባካሄደው የደፈጣ ውጊያ 6 የናይጀር ወታድሮች የተገደሉ መሆኑ ተገልጿል። ደፈጣው የተደረገው ዲፋ በተባለቸው የወሰን ከተማ አቅራቢያ መሆኑና ሌሎች  ሶስት ወታደሮች መቁሰላቸው በተጨማሪ ተነግሯል።  ደፈጣውን ያካሄዱት የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰባቸው አልታወቀም። ከጥቂት ቀናት በፊት በአገሪቷ ላይ በተካሄደው ምርጫው ሚስተር ኢሱፉ በፕሬዚዳንት አሸንፈዋል ተብሎ በምርጫ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ውሳኔ በመቀበል ትናንት ረቡዕ መጋቢት 21 ቀን  የናይጀር የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት  ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑ ታውቋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫውን እንደማይቀበሉ ቀደም ብለው አስታውቀዋል።

 

Ø ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓም ጋልካዮ በተባለ የሱማሊያ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ  የአልሸባብ አባል የሆነ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳው ቦምብ ከራሱ ሌላ ቢያንስ 9 ሰዎች የገደለ መሆኑና ከ10 በላይ ሰዎች ያቆሰለ መሆኑ ተዘግቧል። በማዕከላዊ የሶማሌ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ጋልካዩ የተባለው ከተማ  ለሁለት የተከፈለ ሲሆን  ከፊሉ ከተማ በፑንታላንድ አስተዳደር ስር ሲሆን የተቀረውን የከተማዋን ክፍል በሞጋዲሹ ያለው የሶማሊያ መንግስት ያስተዳድረዋል። ለቦምቡ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደው አልሸባብ የጥቃቱ ኢላማ የፑንትላንድ ባለስልጣኖች ነበሩ ብሏል።

በተያያዘ ዜና በትናንትናው ዕለት በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞጋዲሾ ውስጥ የአልሸባብ ታጣቂዎች መኪና ላይ ሆነው ባካሄዱት የጥይት እሩምታ ሁለት የቱርክ ዶክተሮችን ጨምሮ በጠቅላላው 6  ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። የዛሬ አራት አመት አልሸባብ ከዋና ከተማዋ እንዲወጣ ቢደረግም አሁንም ሰፊ የሆነውን የገጠር ቦታ እንደሚቆጣጠር ይነገራል።

 

Ø በተመድ አማካይነት የተመሰረተው የሊቢያ የአንድነት መንግስት አባሎች ትናንት ረቡዕ መጋቢት 21 ቀን 2008  በመርከብ ትሪፖሊ የገቡ መሆናቸው ታውቋል። ቀደም ብሎ የአንድነት መንግስት በአውሮፕላን ወደ ትሪፖሊ ለመግባት ያቀረበውን ጥያቄ ትሪፖሊ ላይ መሰረት ያደረገው ራሱን መንግስት ነኝ ብሎ የሰየመው ቡድን እንደማይቀብለው በተደጋጋሚ የገለጸ ሲሆን ይህን ባለመቀበል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚገኙበት የሰባት ሰዎች የልኡካን ቡድን የአንድነት መንግስቱን በመወከል በመርከብ ትሪፖሊ የደረሰ መሆኑ የደረሰ መሆኑ መነገሩ ብዙዎችን አስገርሟል። ልዑኩ ወደ ትሪፖሊ የመጣው ከአካባቢ ከሚገኙ  የባህር ኃይል አባሎች ከፖሊስ አካላትና ከሌሎች ታጣቂ ኃይሎች ጋር ተነጋግሮና ተስማምቶ እንደሆነ ቢገልጽም በተለያዩ የሚሊሺያ ኃይሎች ሲደገፍ የቆየው የትሪፖሊው መንግስት ባለስልጣኖች የቡድኑን መገኘት በጽኑ ተቃውመዋል። የአንድነት መንግስት የልኡካን ቡድን አባላት  በሰላም እጃቸውን እንዲስጡ  አለበለዚያም በሰላም ወደ መጡበት እንዲመለሱ አስጠንቀቅዋል። በከተማው አንዳንድ ቦታዎች የመንገድ መዘጋት ከመታየታቸውና አልፎ አልፎ የጥይት ድምጽ ከመሰማቱ በስተቀር እስካሁን ብዙም ችግር እንዳልተፈጠር ነዋሪዎች ያወራሉ። በትናንትናው ምሽት መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን የሰጠውን መግለጫ ያስተላልፍ የነበረ አንድ የራዲያና የቴሌቪዥን ጣቢያ በአካባቢው ሚሊሺያዎች ተወርሮ መዘጋቱ ተሰምቷል። ከበድ ያለ የእርስ በርስ ግጭት ይኖራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ስጋት እስካሁን አለመከሰቱ እና ሰላም መውረዱ በሊቢያ ላለው አካል ድጋፋቸውን ሲሰጡ የነበሩት የተለያዩ የሚሊሺያ ኃይሎች አሁን ድጋፋቸውን ወደ አንድነቱ መንግስት ማዞራቸውን ያሳያል   የሚሉ ታዛቢዎች አልጠፉም። ትናንት ትሪፖሊ የገቡት የአንድነት መንግስት ልኡካን አባላት እርቅና ስምምነትን ፈጥረው ሰላም ለማስፈን ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የሚፈጠረው ሁኔታ የአገሪቱን የወደፊት እድል ይወስናል በሚል ታዛቢዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።  

 

 

 

መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም.

 

Ø ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ማክሰኞ ዕለት እንዳስታወቀው ከእርስ በርስ ጦርነት የምትዳክረው የመን 485 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን  ከቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ማስወጣቱን ገልጿል። ስደተኞቹ በመርከብ ወደ ጅቡቲ ከተሻገሩ በኋላ ከጅቡቲ በአውቶቡስ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከየምን ከተመልሱ ስደተኞች ውስጥ 122ቱ ሴቶች ሲሆኑ 261 ወንዶችና 101 ደግሞ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ መሆናቸው ታውቋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከዚህ ቀደም 4222 ኢትዮጵያውያንን ከየመን ያስወጣ ሲሆን ባለፈው ዓመት መስከረም ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት ምክንያት ስደተኞችን መመለስ ማቆሙ ይታወሳል። ይኽው የተመድ የስደተኛ ጉዳይ ድርጅት አሁን በያዘው ፕሮጀክት 1212 ስደተኞችን ለመመለስ ማቀዱ ታውቋል። ተመላሽ ስደተኞች በአስራጊዎቹና ስደተኞችን በመያዣ በሚይዙ ወንጀለኞች የከፋ ስቃይና እንዲሁም ግድያ ይገጥማቸው እንደነበር ተናግረዋል። የመን እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚጎርፉባት አገር መሆኗ የሚረጋገጠው የተመድ ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ሪፖርት ባለፈው ዓመት 92 ሺ ስደተኞች የመን እንደገቡና ከነዚህ ውስጥ 89 ከመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን መግልጹ ነው። ስደተኞቹ  በጦርነት አረንቋ ውስጥ ወደምትዳክረው የመን  መሄዳቸው  ዘረኛ የሆነው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ቅጥ ያጣው ድህነት አስከፊነቱ በጣም  ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን  ያሳያል የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው።

Ø የወያኔ ቡድን መሪዎች በኢትዮጵያ የዘረጉትን የአንድ ዘር የበላይነትን ዘላለማዊ ለማደረግና የአምባገነናዊ አገዛዛቸውን ለማስቀጠል የፖሊስ ቅጥር ማስታወቂያ ማውጣቸው ታወቀ። ይህ ለወያኔ 18ኛ ዙር የፖሊስ ቅጥር ጥሪ የተባለለት ማስታወቂያ ከመጋቢት 20 ቀን 2008 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረሰ የሚከናወን ይሆናል ተብሏል።  ለ 18ኛው ዙር የፖሊስ ምልመላ የተቀጥሩ ወጣቶች የአንድ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ብር ደመወዝና አራት መቶ አምሳ ብር አበል እንደሚከፍሉ የተገለጸ ሲሆን ማስታወቂያውም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል እንዲሰራጭ የተደረገ መሆኑም ታውቋል። ለፖሊስና ለወታደር ምልመላ ወያኔ አዲስ አበባን ትቶ መቆየቱና  ትኩረቱን  ወደ ተለያዩ ክፍለ ሀገሮች አድርጎ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን   አሁን በአዲስ አበባ ምልምል ፖሊሶችን ለመቅጠር የወጣው ማስታወቂያ በእርግጥ ለፖሊስነት መሆኑ የሚጠራጠሩ ወገኖች  በፖሊስነት ስም  ለውትድርና ምልመላ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ።   

Ø የወያኔ ቀንደኛ መሪ የተባለውና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ በአማካሪነት ስም የኃይለማርያም ደሳለ አዛዥ የሆኔው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለፓርላማው ባቀረበው ሪፖርት ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ በተቀሰሰበት ወቅት በኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች ውስጥ የወያኔ ድህረ ገጾች ተሰብረው እንደነበር ገልጿል። ደብረጽዮን የወያኔ የመገናኚያና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የተባለ ተጨማሪ ማዕረግ እንዳለውም ይታወቃል። የወያኔ ድህረ ገጾች ሰበራ በአብዛኛው ያትኮሩት በወረዳ ላይ ባሉ ኔትዎርኮች ላይ ሲሆኑ ወረዳዎቹ ለወያኔ መሪዎች የሚያቀርቡት የጸጥታና የድህንነት ሪፖርቶች ሁሉ ይወሰዱ እንደነበር ገልጾ ለማስቆም ጥረት መደረጉን ተናግረሯል። በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል መጥፋትና መቆራረጥ በቴሌ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መምጣቱን ገልጾ ቴሌ በኤሌክትርክ  አሁን ግን ቴሌ የራሱ የኃይል አማራጭ ይኖረዋል ይበል እንጅ በኢትዮጵያ መፍተኄው ስለጠፋለት የኤሌክትሪክ መቋረጥና መጥፋት የተነፈሰው ነገር የለም።  ደብረጽዮን ቴሌ በአሁኑ ጊዜ 42.3 ሚሊዮን የሞባይል ደንበኛ፤ 890 ሺ የመደበኛ የስልክ ደንበኞች እንዲሁም 12.4 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዳለውና ገልጾ ይህም  ከአፍሪካ ሁለተኛ ነው ይበል እንጅ ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ብዛት አኳያ የተጠቃሚው ቁጥር ከአፍሪካ የመጨረሻዎቹ አገሮች ናት ተብላ መመደቧ ይታወቃል። ደሃ የሆነውችውና ጦርነት ያላባራባት ሶማሊያ እንኳ ከሕዝቧ 90 ከመቶ የሆነው የሞባይልና የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆኑ ይነገራል።    

 

Ø በያዝነው የፈረንጆቹ የፈረንሳይ ወታደሮች ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፕብሊክ ዓመት ጨርሰው የሚወጡ መሃናቸውን የፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትር ኤኤፍፒ ለተባለው የዜና ወኪል በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ጨምረው እንደገለጹት ምንም እንኳ ሁሉም የአገሪቱ ችግሮች የተፈቱ ባይሆንም  የፈረንሳይ ወታደሮች ተልዕኮ ግቡን ስለመታ ጣልቃ ገብነቱ በዚህ ዓመት ያበቃል ብለዋል። ከሶስት ዓመት በፊት የታጠቁ አማጽያን  በወቅቱ የነበረውን የፕሬዚዳንት ፍራንስዋ ቦዚዜን መንግስት ሲገለብጡ ፈረንሳይ ሁኔታውን ለማረጋጋት በሚል ምክንያት  ወደ አገሪቱ ጦሯን መላኳ አይዘነጋም። በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ሚስተር ቱዋዴራ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል።

 

Ø በጊኒ የኑሮ ውድነት እየጨመረ በመሄዱና መንግስቱም የነዳጅ ዋጋ እንዲቀንስ የቀረበለትን ጥያቄ ባለመቀበሉ ሕዝቡ ለሁለት ቀናት ጠቅላላ አድማ እንዲያደርግ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥሪ አድርገዋል። የተቃዋሚ ኃይሎች መሪዎች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ዜጋ ለሁለት ቀናት በቤት ውስጥ በመቀመጥ አድማ እንዲያካሂድ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ዘረፋና ሌሎች የወንጀል ተግባራት እንዳይከናውኑ በጥብቅ ተማጽነዋል። የጊኒ መንግስት በሕዝቡ ላይ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት መቆጣጠር ያልቻለ ሲሆን በኢቦላ በሽታ ምክንያት የአገሪቱ ኢኮኖሚ መናጋቱን በመግለጽ የነዳጅ ዋጋ እንዲቀንስ የቀረበውን ጥያቄ አንቀበልም ብሏል። 

 

Ø በትናንትናው ዕለት አንድ የግብጽ የመንገደኞች አውሮፕላንን ጠልፎ ወደ ቆጵሮስ የወሰደው መሀመድ ሙስጠፋ የሚባለው የ58 ዓመቱ ግብጻዊ ዛሬ መጋቢት 21 ቀን ፍርድ ቤት መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን ለሚቀጥለው ስምንት ቀን  በዕስር ላይ ሆኖ ምርመራው እንዲቀጥል ዳኛው የፈቀደ መሆኑ ታውቋል። መሀመድ ሙስጠፋ አውሮፕላኑን አስገድዶ ወደ ቆጵሮስ እንዲሄድ ያደረገው የሀሰት ቦምብ ታጥቄያለሁ ብሎ  በማስፈራራት ሲሆን ይህን እርምጃ የወሰደው በቆጵሮስ የምትገኘውን የቀድሞ ሚስቱንና የልጆቹን እናት ለማየት ነው ተብሏል። የአይምሮ በሽተኛ ነው የተባለው  መሀመድ ሙስጠፋን  በጠለፋ እና በሽብር ወንጀሎች ሊከሰስ እንደሚችል ተጠቁሟል።

 

Ø የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓም ይፋ ባደረገው ዘገባ በማሊ የሚገኘው የጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገልጾ የማሊ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እየተባለሸ ወደ ሚገኝበት ወደ ሰሜን ማሊ ባስቸኳይ ወታደሮቹን እንዲልክ ጠይቋል። በትናንትናው ዕለት በተመድ ዋና ጸሐፊ አማካይነት ለጸጥታው ምክር ቤት የቀረበው ይኸው ልዩ ዘገባ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በተጻራሪ ኃይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም አክራሪና አሸባሪ ኃይሎች በሰሜን እና በመሀል ማሊ ጸጥታውን ለማደፍረስ እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ ሁኔታው አሳሳቢ ሆኗል ብሏል።   ከአራት ዓመት በፊት በማሊ የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቅም የሰሜን ማሊን ግዛት ይዘው የነበሩት አማጽያን በፈረንሳይ ወታደሮች እርዳታ ከአካባቢው ቢወገዱም የሰሜንና የማዕከላዊ ማሊ ግዛቶች ጸጥታቸው ሲደፈርስ መቆየቱ ይታወቃል። ከጥቂት ወራት በፊት በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ላይ አማጽያን ባካሄዱት ጥቃት ሰባት ወታደሮች እና ሁለት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም በዋና ከተማ በሚገኘው በራዲስን ሆቴል የተካሄደው የአሸባሪዎች ጥቃት በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል። አሸባሪዎች በማሊ በአይቮሪ ኮስት እና በቡርኪና ፋሶ ጥቃታቸውን እያስተባበሩ መሆኑን ዘገባው ጠቅሶ ሁኔታውን ለመቋቋም የማሊ መንግስት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች በተጨማሪ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል መጠናከር አለበት ብሏል። ባሁኑ ወቅት በማሊ 10 700 የሚሆን የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት ያሉ ቢሆንም አንድ ልዩ የተዋጊ ኃይል 134 ወታደራዊ ካሚዮኖች አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተርን ሌሎች ለወታደራዊ ስራ የሚያገለግሉ ሄሊኮፕተሮች ያስፈልጉታል ተብሏል።     

 

 

 

 

መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም.